ETHOP

ETHOP

Share

Photos from Breaking News In Ethiopia "  ሰበር ዜና "'s post 13/02/2023
15/12/2022

እስከ ህዳር ድረስ ወደ ትግራይ ክልል 82 ሽህ 2 መቶ ሽህ 19 ነጥብ 8 ሜትሪ ቶን ያልተገደበ ሰብዓዊ ድጋፍ መጓጓዙን የአደጋ ሥጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታዉቋል፡፡

በመንግስት በኩል ድጋፍ የተደረገ 13 ሽህ 6 መቶ 86 ሜትሪክ ቶን ፣ መድሃኒት 12 ሽህ 2 መቶ 27 ሜትሪክ ቶን ፣ምግብ ነክ ያልሆነ 7 ሽህ 6 መቶ 51 ሜትሪክ ቶን መጓጓዙን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ዘዉዴ ተናግረዋል፡፡

በጎንደር 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን እና በአፋር ከ7 ሽህ በላይ ተፈናቃይ ለሆኑ ዜጎች በሶስት በተከፈሉ ቡድን ባለሙያ በማሰማራት እየተሰራ መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዉ አክለዉ ገልጸዋል፡፡

24/11/2022

የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ አማጺ ቡድን ትህነግ የሰላም ንግግር ታሪካዊ ዘገባ፡፡

21/11/2022

የጫካ ሳተላይት ከተማ ፕሮጀክት

የጫካ ፕሮጀክት ከእንግሊዝ ኤንባሲ ጀርባ ያለውን ተረራማ ጫካ ይዞ ፣ እንጦጦን አካሎ ፣ የሱሉልታን ግርጌ ይዞ ፣ ጣፎ ደርሶ ወዲህ የሚመለስ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው።

የቦታው ስፋት በጠቅላላ 3,700 ሄክታር ሲሆን ይህም ማለት ደግሞ የልደታ ክፍለ ከተማን አራት ያህል እጥፍ ማለት ነው - ልደታ ክፍለ ከተማ 800 ሄክታር ገደማ እንደሆነ ልብ ይሏል።

በዚህ የጫካ ሳተላይት ከተማ ውስጥ ቤተመንግስት ፣ መኖሪያ ቤቶች ፣ የንግድ ማዕከላት ፣ ግድብ ፣ትላልቅ ሰው ሰራሽ ሐይቅ ፣ የኬብል ትራንስፖርት፣ ከተማን ከተማ የሚያሰኙ መዝናኛና አገልግሎት መስጫ ግንባታዎችን ያካተተ ነው።

ከአመት በፊት የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ባወጣው የግንባታ ተሳትፎ ፍላጎት ጥሪ 11 ኩባንያዎች ቀርበው ነበር። ከነዚህ ውስጥ የተወሰኑት እያንዳንዳቸው ከአስር ሄክታር ያላነሰ ቦታ ተረክበው በሚሰጣቸው ዲዛይን መኖሪያ አፓርትመንቶችን ለመገንባት ተንቀሳቅሰዋል።

የቤተመንግስቱም ግንባታ እየተፋጠነ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ። የቤተመንግስት ግንባታው ብቻ የየወቅቱን የኮንስትራክሽን ዋጋ ጨምሮ እስከ 80 ቢሊዮን ብር እንደሚፈጅ ፤ አጠቃላይ ሳተላይት ከተማውን ለማጠናቀቅ ደግሞ አንድ ትሪሊዮን ብር ድረስ ሊፈጅ እንደሚችል ለፕሮጀክቱ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ይናገራሉ ።

አዲሱ-አዲስ አበባ ውብ እና በየቀኑ ብዙ ገንዘብ ማመንጨት የሚችል እንደሆነ በባለሙያዎች ታምኖበታል ። ባለሙያዎች እንደሚሉት የጫካው ከተማ ሌሎች ከተሞች ሲገነቡ የተሠሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ እድል ይሰጣል። ሰው እና ተፈጥሮም የሚገናኙበት ውብ ስፍራም ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (phd) ለፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ ፕሮጀክቱን ‘’የአፍሪካ ኩራት’’ ብለውታል ።

ፕሮጀክቱ በርካታ ኮንትራክተሮችን የሚያሳትፍ ፣ ብዙ የስራ ዕድል የሚፈጥር - አዳዲስ እና ዘመናዊ የአገነባብ ስልቶችን የሚያቀዳጅ በመሆኑ ለኢንዱስትሪው ተዋንያን መልካም ዜናም ጭምር ነው።

አዲሱ እየሩሳሌም -አሮጌው እየሩሳሌም ፤ አዲሱ ፓሪስ አሮጌው ፓሪስ እንደሚባለው ሁሉ አሮጌው አዲስ አበባ ፣ አዲሱ አዲስ አበባ - ይባል ዘንድ ጊዜው ፈቅዷል።

ምንጭ፡- WZ news

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
27