ROC Spaces

ROC Spaces

Share

16/03/2023

HAPPY INTERNATIONAL WOMEN'S MONTH!!!
-From all the Women at ROC Spaces!
Check out our article:
https://linkedin.com/pulse/women-roc-spaces-rocspaces

Photos from ROC Spaces's post 08/03/2023

እንኳን ለዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ!!! March 8ን አስመልክቶ በድርጅታችን ውስጥ የሰው ሃይል አስተዳደር ወ/ሪት ራሔል ጌትነት ጋር ያደረግነውን ቆይታ እነሆ!

ጥያቄ፡ በቅድሚያ ሙሉ ስምሽን እና የስራ ኃላፊነትሽን ብትነግሪን?
ራሔል፡ አስቀድሜ ይህንን ዕድል ስላገኘሁ በጣም አመሰግናለሁ። ራሔል ጌትነት እባላለሁ። በሮክ ስፔስስ (National Asset Management PLC) ውስጥ የሰው ሃይል አስተዳደር ነኝ።

ጥያቄ፡ ምን ያህል ጊዜ ሆነሽ እዚህ ድርጅት ውስጥ ስትሰሪ?
ራሔል፡ 1 ዓመት ከ4 ወር አካባቢ ይሆነኛል።

ጥያቄ፡ ወደ 16 ወራት አካባቢ ማለት ነው…እስቲ ስለ ሮክ ስፔስስ ጥቂት ብትነግሪን? እንደሚታወቀው ድርጅቱ ስራ ከጀመረ 5 ዓመታት አካባቢ አስቆጥሯል…አንቺ ደግሞ ድርጀቱ ውስጥ እንደመቆየትሽ አንዳንድ ነገሮችን ብታጫውቺን…
ራሔል፡ ሮክ ስፔስስ የሕንጻ አስተዳደር ድርጅት ነው። የኖህ ሪል ስቴት እህት ኩባንያ እንደመሆኑ መጠን በኖህ ሪል ስቴት የተገነቡ ሕንጻዎችን ያስተዳድራል። ከዚያ በተጨማሪም የሌሎች ኩባንያዎችንም ሆነ የግለሰብ ህንጻዎችን የሚያስተዳድር ድርጅት ነው። ከስሙ መረዳት እንደምንችለውም R- Residential (የመኖሪያ)፣ O- Office Units (የቢሮ)፣ እንዲሁም C- Commercial Units (የንግድ ሱቆች እንዲሁም የመጋዘን ቦታዎችን) ያስተዳድራል። የሕንጻ አስተዳደር ብዙ ነገሮችን ያካትታል። ያው የመጀመሪያው ነገር የሚከራይ ቦታ ከሆነ ተከራዮችን እና አከራዮችን የማገናኘት ስራ ነው። የተከራዮችን ተአማኒነት በማጥናት፣ መልካም ተከራዮችን ከህንጻ ባለቤቶች ጋር የማገናኘት ስራ ነው የምንሰራው። ከዚያ በመቀጠል ደግሞ የተከራይ-አከራይ ውል አፈራርሞ የኪራይ ገቢን በተገቢው ጊዜ እና አግባብ መሰብሰብ ዋነኛ የስራ ድርሻችን ነው። ከዚህ ባለፈ ደግሞ የህንጻውን ህልውና የመጠበቅ ድርሻን የጽዳት፣ የጥበቃ፣ እንዲሁም ቀለል ያሉ የቴክኒክ ስራዎችን ጨምሮ በኃላፊነት ወስዶ ያከናውናል።

ጥያቄ፡ እስቲ ወደኋላ ትንሽ እንመለስና…ሮክ ስፔስስን ከመቀላቀልሽ በፊት የትምህርት ቆይታሽን እንዲሁም እንዴት ወደዚህ ሰራ እንደመጣሽ ብትነግሪን…
ራሔል፡ እንግዲህ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ በሎጅስቲክስ እና ሰፕላይ ማኔጅመንት ነው የተመረቅሁት። ዩኒቨርሲቲ የተቀላቀልኩበት ዓመት ትንሽ ከባድ ነበር። ያው ከቤትሰብ ርቆ ከመሄዱ በተጨማሪ የተመደብኩበት የትምህርት መስክ አዲስ መሆኑ ሁኔታውን አስቸጋሪ አድርጎት ነበር። ከመጀመሪያው ሴሚስተር በኋላ ግን ብዙ ነገሮችን በመልመድ አሁን ላይ እንኳን የሚያጋጥሙኝን ከባድ የሚባሉ ጊዜያትን ተቋቁሜ እንዳልፍ በጣም ረድቶኛል።
እኔ ወደ ሮክ ስፔስስ ስመጣ…እውነቱን ለመናገር ስለህንጻ አስተዳደር ጥልቅ የሚባል እውቀት አልነበረኝም። እንደዚህ አይነት አገልግሎቶችን የሚሰጥ ድርጅትም አዲስ አበባ ላይ ነው እንጂ ሌሎች ቦታዎች ላይ የተለመደ አይመስለኝም። እንደዛም ሆኖ ስራው በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ለመረዳት እምብዛም ጊዜ አልፈጀብኝም። እንዲያውም እንደ ድርጅት በደንብ አስፋፍተን፣ በመላው ኢትዮጵያ ሊሰራበት የሚገባ የስራ ዘርፍ ይመስለኛል።…ያው ይህንን ስራ እንደአጋጣሚ ቢሆንም የጀመርኩት አሁን ላይ ግን የስራውን ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታዎች በማየቴ በጣም እድለኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል።

ጥያቄ፡ እስቲ የሰው ሃይል አስተዳደር የስራ መደብ ምን ምን ያካትታል? ከዚያው ጋር አያይዘሽ ደግሞ ከስራሽ በጣም የሚያስደስትሽን ነገር ብታጫውቺን…
ራሔል፡ የሰው ሃይል አስተዳደር ማለት እንግዲህ የድርጅት የልብ ምት ነው። የድርጅቱን የውስጥም ብሎም የውጪ ግንኙነቶች አመጣጥኖ ዘላቂነት ባለው መልኩ ማስተዳደርን ይጠይቃል። ይህ እንዳለ ሆኖ ይሄ የእኔ የስራ ድርሻ አይደለም ብዬ የምተወው ነገር የለም። አንዳንድ ጊዜ ወጣ ብለሽ የምታደርጊያቸው ነገሮችም ሊኖሩ ይችላሉ። ለዚያም ይመስለኛል…ከምንም በላይ የደንበኛ ጥያቄ ተስተናግዶ ሳይ፣ ሠራተኞች ቅሬታቸው ተፈትቶ ስመለከት…ለእኔ ትልቅ እርካታ የሚሰጠኝ።

ጥይቄ፡ ከስራው ጋር ተያይዘው ያሉ ፈተናዎች ወይም አስቸጋሪ የሚባሉ የስራ አጋጣሚዎችን ብታወጊን፤ ከዚሁ ጋር አያይዘሽ ደግሞ እነዚህ ጊዜያት በግልም ሆነ እንደ አጠቃላይ ምን አይነት ተጽዕኖ እንደነበራቸው ብትነግሪን
ራሔል፡ ያው የመጀመሪያው ነገር…አብዛኛው ሰው እንደሚነግረኝ ከሆነ ስራው እንደእኔ በ20ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ባለ ሰው የሚሰራ አይደለም። አብዛኛውን ጊዜ በዕድሜ ገፋ ያሉ ሰዎች የሚሰሩት ስራ ከመሆኑም አንጻር፤ ከዚያም ባሻገር ደግሞ ስራው ከብዙ ሰው ጋር ስለሚያገናኝ፤ ብዙ አይነት ባህሪ እንዲሁም የተለያየ የስራ ድርሻ ካላቸው ሰዎች ጋር በተለያየ መልኩ ማስተናገድን ይጠበቃል። ይሄ እንዳለ ሆኖ ደግሞ አንዳንድ ግዜ ሠራተኛ ድንገት ይለቃል። በዚያ ምክንያት የሰው ኃይል እጥረት ሲያጋጥም በጣም ያስጨንቃል። ነገር ግን ይሄ ፈተና ብቻ ሳይሆን የጥንካሬ ምስጢርም እንድሆነ እረዳለሁ። ምናልባት ስራውን ወድጄው ስለምሰራውም ሊሆን ይችላል በጣም ጠንካራ እንድሆን አድርጎኛል። ሁለንተናዊ በሚባል መልኩ አብዛኛውን ማንነቴን ሰርቶታል። ይሄ ደግሞ ነገ የተሻለ ሰው እንደሚያደርገኝ ሳስብ በጣም ያስደስተኛል።

ጥያቄ፡ ስራሽ በሴቶች ዘንድ የተለመደ ነው ብለሽ ታስቢያለሽ? ከሆነ ለምን ይመስልሻል?
ራሔል፡ ስራው በእርግጥ ጾታ አይለይም፤ በሴት/በወንድ ብቻ የሚባል ነገር የለውም። አብዛኛውን ጊዜ ሴቶች የሚሆኑበት ምክንያት ግን ስራው ከሚጠይቃቸው ብዙ ኃላፊነቶች፣ ቆራጥ የሆኑ ውሳኔዎች፣ እንዲሁም ደግሞ ከታማኝነት ጋርም ተያይዞ ይመስለኛል። ይሄ ደግሞ ለእኔ ኩራት ነው እንጂ የተለየ ተጽዕኖ አድርጌ አላየውም።

ጥይቄ፡ እስቲ በዚህ መስሪያ ቤት ውስጥ ሮል ሞዴል/አርዓያ ሆኖኛል የምትዪው ሰው ካለ?
ራሔል፡ ያለምንም ጥርጥር አለቃዬን ወ/ሮ ዮዲት ተሾመ፤ አርዓያ ብቻ ሳይሆን በብዙ ነገር እንድበረታ፤ ከዚያ ባለፈ ደግሞ የስራ ስነምግባሬን እንዳሳድግ በጣም ስለረዳችኝ…በዚህ አጋጣሚ እንዲያውም በጣም ላመሰግናት እወዳለሁ።

ጥያቄ፡ ከዚህ ጋር አያይዘሽ…በሴቶች የሚመራ ድርጅት ምን እንደሚመስል ብትነግሪን?
ራሔል፡ በጣም የሚያስደስት ነገር ነው። ለእኔ አለቃዬ አለቃ ብቻ አይደለችም። እንደ እናትም ነች። አብሬ የምሰራቸው የስራ ባልደረቦቼ ደግሞ ጓደኞቼ…ያው እንደ ቤተሰብ በዪው ያለንን ቅርበት…እንደዚህ መሆኑ ደግሞ በጣም ያስደስተኛል።

ጥያቄ፡ ከአመራር ጋር የተገናኘ ሚና እንዳላት ሴት፣ በአመራር (leadership) ላይ መስራት ለሚፈልጉ ወጣት ሴቶች የምትዪው ነገር ካለሽ?
ራሔል፡ ሚዛናዊነት የስራው ዋና መርህ እንደመሆኑ ፈሪሃ-እግዚአብሔር ኖሯቸው፣ ፍትሓዊ የሆነ ማንነትን ይዘው እንዲያድጉ በአጽንኦት መናገር እፈልጋለሁ። እንደዛ ከሆነ ደግሞ የትኛውም ስራ ቀላል እንደሚሆን አምናለሁ።

ጥያቄ፡ በግልሽ በጣም የምታደንቂያት ስኬታማ ሴት…በጣም የምትወጂው አባባል ካለ?
ራሔል፡ እናቴ ወ/ሮ ሃናን በጣም ነው የማደንቃት። አብዛኛውን የህይወት መመሪያዎችን ያስተማረችኝ እሷ ናት…ከሁሉም የማልረሳው ደግሞ “የሰው ልጅ ሲሰራ እንደባርያ፣ ሲወጣ ደግሞ እንደ ፈረንጅ” ትለናለች…(ሳቅ)...በጣም ቀላል ነገር ሊመስል ቢችልም፤ ጠንክሮ መስራትን እንደመርህ እንድይዝ አድርጎኛል ብዬ አምናለሁ።

ጥያቄ፡ በጣም ደስ ይላል…እስኪ በመጨረሻ ዓለምአቀፍ የሴቶች ቀን እንደመሆኑ፣ የምታስተላልፊው መልዕክት ካለ…ከዚያው ጋር አያይዘሽ ማመስገን የምትፈልጊያቸው ሰዎች ካሉ?
ራሔል፡ እንኳን አደረሳችሁ ማለት እፈልጋለሁ… ለመላው ሴቶች ፣ እናቶች፣ እህቶች፣ እንዲሁም ህጻናትን እንኳን ሳይቀር እንኳን ለዚህ ቀን አደረሳችሁ ማለት እፈልጋለሁ። በመቀጠል ከምንም በላይ ፈጣሪዬን ለማመስገን እወዳለሁ። ከፈጣሪ ቀጥሎ ደግሞ እዚህ ስኬት ላይ እንድደርስ ስለረዳችኝ እናቴን በጣም ላመሰግን እፈልጋለሁ።
ጥያቄ፡ ስለነበርን ቆይታ በጣም አመሰግናለሁ። ለቀረው የስራ ዘመንሽ ደግሞ መልካም ዕድልን እመኝልሻለሁ!
ራሔል፡ እኔም በጣም አመሰግናለሁ!

24/02/2023

With ownership is made easier!!!

Want your business to be the top-listed Realtor/realty Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Bole Medhaniyalem, Abyssinia Plaza, 3rd Floor
Addis Ababa
4654

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 18:30