Bisrat garedew

Bisrat garedew

Share

11/06/2025

ሼር
የመጨረሻዋ ቦታ 😍 "አዎ ጌታ ኢየሱስ ይመጣል"

ከልጅነቴ ጀምሮ አለምን የመጓዝ ፍላጎቴን እግዚአብሔር ፈቅዶ ጉዞ ከጀመርኩ ጀምሮ ከህፃንነቴ እሰማው አነበው የነበሩ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ቦታዎችን በአካል ማየቴ እጅግ ያስደስተኛል።

ይህ በምስሉ የምታዩት ቦታ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያርግ እግሮቹ ረግጠውት የነበረው የመጨረሻው ቦታ ነው ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 24 ከቁጥር 49 ጀምሮ አንደተፃፈው " እናንተ ግን ከላይ ሀይል እስክትቀበሉ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ ። እስከ ቢታኒያ አወጣቸው እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ምስጋና ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።"

ይህ ቦታ ዛሬ ከለላ ተሰርቶለት ከኢየሩሳሌም ፊት ለፊት በሚገኘው ደብረዘይት ተራራ አናት ላይ ይገኛል። የመጨረሻ ጌታ ረግጧት የነበረችው ቦታ በድንጋይ ተከቦ ተለይቷል። ጌታ ኢየሱስ እንደተናገረ ተነስቷል በክብርም አርጓል ቦታው ዛሬም ህያው ምስክር ሆኖ ታሪክን ለትውልድ ይናገራል።

እኔም በመጨረሻ እንዲህ ልበል " እንሆ አለም ይስማ እንደተናገረ የተነሳው ጌታ ኢየሱስ ዳግም ይመጣል ቀኑ ቀርቧል ኢየሱስ ይመጣል ጌታ ይመጣል ይፈርዳል ማንም ቀኑን አያውቅም በድንገት ይመጣል ተዘጋጅታችሁ ቆዩ እንዳለው ጌታ በርግጥም ይመጣል እናምናለን ጌታ ኢየሱስ ይመጣል"

አቤል ብርሀኑ የወይኗ ልጅ
ሼር

በአትሌት ገለቴ ቡርቃ ዙሪያ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የሰጠው መግለጫ |ስለሽ ስህን | መሰረት ደፋር ETV | EBC | EBCDOTSTREAM 10/06/2025

https://youtube.com/watch?v=wILTj5_mUrE&si=nTz251xJ5OLmIJCI

በአትሌት ገለቴ ቡርቃ ዙሪያ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን የሰጠው መግለጫ |ስለሽ ስህን | መሰረት ደፋር ETV | EBC | EBCDOTSTREAM አትሌቶችን ከጥቃት የሚከላከል ኢንስቲትዩት ሊቋቋም ነው #ኢቢሲ #ኢቲቪ #ስለሽስህን #መሰረትደፋር #ገለ...

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa