Federal Civil Service Commission

Federal Civil Service Commission

Share

Photos from Federal Civil Service Commission's post 24/05/2026

ለፌዴራል ተቋማትና ለዩኒቨርሲቲዎች የኢስሚስ ሥርዓት አጠቃቀም የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ::
*************
አዲስ አበባ | ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመንና የዲጂታል ሪፎርሙን ለማፋጠን ሲያከናውን የቆየው ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ አንድ ምዕራፍ መሻገሩም ተጠቁሟል።

የሰራተኞችን መረጃ ወደ ስማርት የሰው ሀብት አስተዳደር አስሚስ አጠቃቀም እና መረጃ ሥርዓት ለማስገባት በአዳማ ከተማ ለተከታታይ አምስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና በስኬት ተጠናቋል።

በዚህ ስልጠና ላይ ከተለያዩ የፌዴራል መንግሥት ተቋማት እና ከሀገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች) የተውጣጡ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) እና የሰው ሀብት (HR) ልማት ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ መርሃ-ግብር ላይ በመገኘት የቀጣይ የሥራ አቅጣጫ የሰጡት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሽብሩ አባዲማ እንደገለጹት፤ ሀገሪቱ የጀመረችው ሁለንተናዊ የዲጂታል ሪፎርም ዋና ዓላማ የህዝብን እንግልት መቀነስ ነው ብለዋል።

ም/ኮሚሽነሩ የሪፎርሙ ዋና ግብ የመንግሥት አገልግሎቶችን ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ለተገልጋዩ ማህበረሰብ ምቹ ማድረግ መሆኑን ገልፀው የባለሙያዎች ኃላፊነት ሰልጣኞች ወደየ ተቋሞቻቸው ሲመለሱ የተማሩትን ቲዎሪ ብቻ ሳይሆን በተግባር በመተርጎም የለውጥ መሪ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ባህላዊ አሰራርን ማስቀረት በሰው ሀብት መረጃ አያያዝ ዙሪያ የሚታዩ ሰነዶችን የማጥፋት፣ የማጭበርበር እና የቢሮክራሲ መዘግየቶችን በቴክኖሎጂው ሙሉ በሙሉ ማስቀረት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ም/ኮሚሽነሩ አክለውም አሁን ከዚህ የወሰዳችሁትን ስልጠና ወደ ተቋማችሁ ስትመለሱ በተግባር ማሳየት ይኖርባችኋል በማለት በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን በመዘርጋት በአገልግሎት አሰጣጥ እንግልት የሚደርስበትን ህዝባችንን ልንታደገው እንደሚገባ አሳስበዋል::

በተጨማሪም በፌዴራል ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የኢስሚስ ሥርዓት የመንግሥት ሠራተኞችን መረጃ ከቅጥር እስከ ጡረታ ባለው ሂደት በዲጂታል መንገድ ለመቆጣጠርና ለማደራጀት የተዘረጋ ሲሆን የሚሰጠው ፋይዳ የደመወዝ፣ የበጀትና የሠራተኛ ስምሪት መረጃዎችን ትክክለኛነት ያረጋግጣል እንዲሁም መንግሥት ስለ ሲቪል ሰርቪሱ አጠቃላይ ቁጥርና አቅም ትክክለኛ መረጃ አግኝቶ ፈጣን ውሳኔ እንዲያስተላልፍ ይረዳል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት ስልጠናቸውን ያጠናቀቁት የአይሲቲ እና የሰው ሀብት ባለሙያዎች በቀጣይነት በየተቋማቸው የሚገኙ የሠራተኞችን ዝርዝር መረጃ (Profile) ወደ ሲስተሙ የማስገባት ሥራን በቀጥታ ስራ እንደምጀምሩ ተገልፆዋል::

በመጨረሻም ም/ ኮሚሽነሩ በየመስሪያ ቤቶቻቸው ላሉ ሌሎች የሥራ ባልደረቦቻቸው ያገኙትን እውቀት በማካፈል የቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የስርዓቱን ትግበራ ሂደት በቅርበት ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግበት ታውቋል።
#የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ

Photos from Federal Civil Service Commission's post 21/05/2026

የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንና የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎትን ጎበኙ፡፡
*******************
ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም፣ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ አዲስ አበባ
በተከበሩ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራርና ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሀላፊ የተመራው የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት የስራ ሀላፊዎች ቡድን በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን በፌዴራል በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፤ የመሶብ አገልግሎት በተመለከተ በፌዴራል መሶብ አገልግሎት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል፡፡

ከኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ጋርም ምክክር አካሂደዋል፡፡ በምክክር መድረኩ ላይ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የደረሰበት ደረጃ በክቡር ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌና በክብርት ወ/ሮ አልማዝ መሰለ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ማብራሪያዎች ቀርበዋል፡፡

ሪፎርሙ አሁን የደረሰበት ደረጃ ከቀረበ በኋላ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ውይይቱን የመሩት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌና የተከበሩ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር የብልጽግና ፓርቲ ዋና መስሪያ ቤት የስትራቴጂክ ስራ አመራርና ኢ.ኮ.ቴ. ዘርፍ ሀላፊ ናቸው፡፡ የኮሚሽኑ የካውንስል አባላትም በውይይቱ ላይ ታድመዋል፡፡

በመድረኩ ላይ በአሁኑ ወቅት የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርሙን ሊመሩና ሊሸከሙ የሚችሉ የተሟሉ የህግ ማእቀፎችና፣ ማስፈጸሚያ ሰትራቴጂዎች የተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የልኡካን ቡድኑ አባላትም የተሰራውን ስራ አድንቀው በውይይቱ የተነሱና በጋራ ሊሰሩ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ መስራት እንደሚቻል ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡
#የውጭ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ

Photos from Federal Civil Service Commission's post 01/05/2026

ዓለም አቀፍ የላብአደሮች ቀን በኢትዮጵያና በዓለም ዙሪያ እየተከበረ ነው: 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
+++++
አዲስ አበባ ሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም (May 1, 2026) የላብአደሮች ቀን ወይም ዓለም አቀፍ የሰራተኞች ቀን በኢትዮጵያና በመላው ዓለም በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

የዕለቱ ታሪክ የሚጀምረው በፈረንጆቹ 1886 በአሜሪካ ቺካጎ ከተማ በወቅቱ ሰራተኞች በቀን እስከ 16 ሰዓት ያለ ዕረፍት እንዲሠሩ በሚገደዱበት ወቅት ነበር።

ይህንንም ግፍ የተቃወሙ የቺካጎ ሰራተኞች "8 ሰዓት ለሥራ፣ 8 ሰዓት ለዕረፍት፣ 8 ሰዓት ለራሳችን" በሚል መሪ ቃል በሄይማርኬት አደባባይ ተቃውሟቸውን በማሰማታቸው ዓለምን የሚቀይር አዲስ የሥራ ሕግ እንዲረቀቅ መሠረት ጣሉ።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በየዓመቱ የሰራተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ይከበር ጀመር።

በኢትዮጵያ ላለፉት 51 ዓመታት በየዓመቱ ሚያዚያ 23 (በፈረንጆቹ ግንቦት 1) የኢትዮጵያ ሰራተኞች የሀገር ግንባታ ምሰሶ መሆናቸውን በማስታወስ፣ የሰራተኛ ማኅበራት መብታቸውን የሚያስከብሩበትና ድምፃቸውን የሚያሰሙበት ታላቅ ዕለት በማድረግ በዓሉ ሲከበር ቆይቷል።

ዛሬ ላይ ይህንን ዕለት ስናከብር ከታሪክ ባለፈ የነገውን ተስፋ እያለምን ነው።
#የውጭ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Bole Road, Kirkos S. City Woreda 09 Around Flamingo Restaurant
Addis Ababa
1082

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 02:30 - 17:30
Wednesday 02:30 - 17:30
Thursday 02:30 - 17:30
Friday 02:30 - 17:30