GebetaTube
21/03/2026
ሽመልስ አብዲሳ በጠና ታመዋል በሚል እየተጋሩ ያሉ መረጃና ምስሎች ሐሰተኛ ናቸው
በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ‘’የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በገጠማቸዉ የጤና መታወክ ምክንያት በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች፣ አቡ ዳቢ በሚገኝ ሆስፒታል ህክምና ላይ ናቸው ‘’በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ አረጋግጧል።
በአንድ የህክምና ማዕከል ሲታከሙ የሚያሳዩ ምስሎችም በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ።
እየተሰራጩ ያሉ ምስሎችን በተመለከተ በሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI)ን በመጠቀም ባደረግነው የመረጃ ማጣራት በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ እንዲሁም በፌስቡክ የተጋሩ ምስሎች በGoogle AI /ጉግል ኤ አይ /የተፈበረኩ እንደሆነ ማረጋገጥ ችለናል።
በዚህም መሰረት ህብረተሰቡ መሰል የተሳሳቱ መረጃዎችን ሳይደናገር ፣ መረጃዎችን ከሚያዛቡ አካላት በመጠበቅ መረጃን ከምንጩ መውሰድ እንዳለበት የፕሬስ መረጃ ማጣሪያ አሳስቧል።
በሀና እጅጋየሁ
Want your establishment to be the top-listed Arts & Entertainment in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa