Vet Agro

Vet Agro

Share

🩺 የእንስሳት ሕክምና | 🐄 ዘመናዊ እርባታ | 🐟 አሳ እርባታ | 🌱 ሳይንሳዊ ግብርና

በዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያ የሚመራ፣ በሳይንሳዊ መረጃ የታገዘ ምርታማነትን በመፍጠር የአርቢውን ሕይወት ለመለወጥ የተቋቋመ ገጽ።

"Vet Agro — Information Backed by Science!"

Photos from Vet Agro's post 04/03/2026

የዶሮ አይን እብጠትና የመተንፈሻ አካል በሽታዎች መፍትሄ 🐔💊

በኮሜንት ላነሳችሁት ጥያቄ አጭር ምላሽ፤ የአይን እብጠትና ፈሳሽ በአብዛኛው የባክቴሪያ ኢንፌክሽን (እንደ ኮራይዛ ወይም CRD) ምልክት በመሆኑ የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ያስፈልጋል፦

1. ዋና ዋና መድኃኒቶች (በባለሙያ ትዕዛዝ የሚሰጡ)፦

Tylosin (ታይሎሲን)፦ ለመተንፈሻ አካል ችግሮች በጣም ውጤታማ ነው።

Oxytetracycline (ኦክሲቴትራሳይክሊን)፦ በውኃ/በመኖ የሚቀላቀል ዱቄት ወይም በመርፌ የሚሰጥ።

Doxycycline (ዶክሲሳይክሊን)፦ ለከፋ የመተንፈሻ አካል ኢንፌክሽን ያገለግላል።

2. መደረግ ያለባቸው አስቸኳይ እርምጃዎች፦

መነጠል፦ የታመሙትን ዶሮዎች ወዲያውኑ ለይቶ ማከም (በሽታው ተላላፊ ስለሆነ)።

ንጽህና፦ የቤቱን አየር ማናፈሻ ማስተካከልና የኩስ ሽታ (Ammonia) እንዳይከማች ማድረግ።

ቫይታሚን፦ በሽታ የመቋቋም አቅማቸውን ለመጨመር Multivitamin በውኃ ውስጥ ቀላቅሎ መስጠት።

⚠️ ማሳሰቢያ፦ ትክክለኛውን የመድኃኒት መጠን (Dosage) ለማወቅና ሌላ ተጓዳኝ በሽታ እንዳይኖር በአቅራቢያዎ የሚገኝ የእንስሳት ሕክምና ክሊኒክ ማማከርን አይዘንጉ።

#የዶሮእርባታ #የእንስሳትጤና

ምንጭ ፦Volunteer Vet Care 🙏

Want your practice to be the top-listed Clinic in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Addis Ababa