EthioPost

EthioPost

Share

05/04/2020

በኮሮና ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው የ60 ዓመት እናት : -ነብስ ይማር ->> RIP

Photos from EthioPost's post 05/04/2020

ሟቿ የጋዜጠኛዋ አክስት ነበሩ!
----------------------
->>የኮሮና ሟች ኑዛዜ " የሃገሬ ህዝቦች ሆይ እራሳችሁን ከአስከፊው ቫይረ ስጠብቁ "
•••••
በአሁኑ ስዓት በኦሮሚያ ቴሌቭዥን ውስጥ እየሰራች የምትገኘው ጋዜጠኛ ቢሊሴ ኢሬና የ60 ዓመት አዛውንት አክስቷ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የኮሮና ቫይረስ ሟች መሆኗን ተከትሎ በፌስቡክ ገጿ የሚከተለውን አስፍራለች።

“Biyya France turtee gara biyyaati Kan deebite adaadaankoo dhukuba koronaan qabamtee biyya keessati yaalamaa erga turtee booda hara boqoteetii. Waan jeenuu hinqabnuu nagaan boqodhu.
Yaalamiikoo maaloo dhukuba kanairraa of eegaa.”

"ፈረንሳይ ሐገር ቆይታ በቅርቡ ወደ ሐገር ቤት የተመለሰችው አክስቴ በኮሮና ቫይረስ ተይዛ የህክምና ርዳታ ሲደረግላት ከቆዬች በኋላ በዛሬው እለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። ሰዎች ሆይ እባካችሁ ከዚህ ገዳይ ቫይረስ ራሳችሁን ጠብቁ"

Photos from EthioPost's post 05/04/2020

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት ተመዘገበ ->>ሁለት ሰዎች ዛሬ ተቀበሩ->>43 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘው አይሲዩ ውስጥ ናቸው
*******************
የጤና ሚኒስቴርና ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮና በሽታ (ኮቪድ-19) በቻይና ውሃን ከተማ ከተቀሰቀሰበት ግዜ አንስቶ ወደ ሀገራችን ቫይረሱ እንዳይገባ እንዲሁም ከገባ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እያደረጉ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ቫይረሱ ወደ ሀገራችን ከገባ ጀምሮ ህብረተሰቡ የጥንቃቄ እርምጃዎችን ተግባራዊ እንዲያደርግ ቅስቀሳዎችን እያደረገና የተጠቂዎችን ቁጥርና የጤና ሁኔታቸው እያሳወቀ ነው፡፡ አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 ፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል፡፡

ህብረተሰቡ በዚህ ሳይደናገጥ ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን (ቢያነስ አንድ ሜትር) ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ስርጭት እንዲከላከል በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

05/04/2020

በኮሮና አይሲዩ(ICU) ውስጥ የገባው የመጀመሪያው ከብት
ምንጭ:- ፌክ ኒውስ አለርት ፣ከአለርት ሆስፒታል

Photos from EthioPost's post 02/04/2020

ስለኮሮና ጥንቃቄ ምክር የለገሰው ግለሰብ ደመ ከልብ ሆነ

♦ መሸለም የነበረባቸውን ሰው ደበደቡት !!!

ያሬድ አማረ ፦ ሰፈሩ ብሔረ ጽጌ አካባቢ ሲሆን ፤ በትላንትናው ዕለት ሰፈሩ አካባቢ ሲንቀሳቀስ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ባሉ መጠጥ ቤቶች ተሰባስበው፣ ሳይራራቁ ሲጠጡ በማየቱና ለሁሉም ስጋት የሆነው ኮሮናን ለማስተላለፍ ምቹ መሆናቸውን በማየትና በመታዘብ ፤ ይሄ ድርጊት መታረምም እንዳለበት በማኅበራዊ ሚዲያ በራሱ ገጽ ላይ በመግለጽ ፣ እንዲሁም የሚመለከተው አካል የመፍትኄ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አስተላልፉ ነበር።

ይሁን እንጂ ፤ ጠዋት ላይ ከዚህ በፊት የሚያውቃቸው ሁለት ወጣቶች ዛቻና ማስፈራሪያ አድርሰውበት የሄዱ ሲሆን ፤ አመሻሽ ላይ ደግሞ በድጋሚ መጥተው ደብድበውት ሄደዋል። እሱም የደረሰበትን በደል አካባቢው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ አመልክቷል ።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa