Nigat

Nigat

Share

04/01/2023

መልካም የልደት በዓል!!!

ዋና ዋና የኢየሱስ አስተምህሮዎች 04/11/2015

ክፍል 3 - በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው! በዮሐንስ ወንጌል በተጻፈልን የምዕራፎች ቅደም ተከተል መሠረት ጌታ ኢየሱስ ኒቆዲሞስን ማስተማር ከጀመረበት ከምዕራፍ 3 አንስቶ እስከ ምዕራፍ 17 ድረስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስለ ዘላለም ሕይወት ያልተናገረባቸው ምዕራፎች ቢኖሩ አራት ምዕራፎች (9፣ 13፣ 15 እና 16) ብቻ ናቸው፡፡ ታዲያ በሌሎቹ 11 ምዕራፎች ውስጥ ስለ ዘላለም ሕይወት ማስተማሩን ስናይ እርሱ የመጣበት ዓላማ ምን እንደ ሆነና ዓላማውንም ከግቡ ለማድረስ ምን ያህል ትኩረት ሰጥቶ እንደ ሠራ የሚያስገነዝብ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ የጌታችንን የማስተማር ሂደት ልዩ ከሚያደርጉት ነገሮች መካከል አንዱ ለሚጠየቀው ጥያቄ ነው ወይም አይደለም የሚል መልስ በመስጠት ፋንታ ጥያቄያቸውን መሠረት አድርጎ እርሱ የመጣበትን ዓላማና የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማሳወቅ ላይ ማተኮሩ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ነው ኒቆዲሞስ ባቀረበለት የውይይት መክፈቻ ላይ ተነስቶ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ የሚሆን ጥርትና ግልጽ ያለ የእግዚአብሔርን ፈቃድና ዓላማ የሚያሳይ መሠረታዊ የዳግም ልደትን አስፈላጊነት የሚያስገነዝብ መልዕክት በማስተላለፍ ገለጻውን ያጠናቀቀው፡፡ በዚህ ክፍል ጌታ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ ‹‹እውነት እውነት እልሃለሁ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን ምስክርነታችንንም አትቀበሉትም፡፡ ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ከሰማይም ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው (ዮሐ 3÷12) በማለት ስለ ማንነቱ እንደ ገለጠለትም እንረዳለን፡፡ ኒቆዲሞስ ቢገባውም ባይገባውም ደግሞም ቢቀበለውም ባይቀበለውም ከሰማይ ስለ መጣሁ የምነግርህ ነገር ሰማያዊ ነው ይህንንም ሊነግርህ የሚችል ከእኔ በቀር ሌላ ማንም የለም፤ እኔም የምነግርህ የሰማሁትንና የማውቀውን ነውና ንግግሬ እውነት ነው እያለ ነው ያስገነዘበው፡፡ ሆኖም ኒቆዲሞስ አሁንም እየተነገረው ያለውን ሊረዳው ስላልቻለ ጌታ ትምህርቱን በመቀጠል ‹‹በምድረ በዳ ሙሴ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ሊሰቀል ይገባዋል፡፡ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና፡፡ ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አላከውምና (ዮሐ 3÷14-17) በማለት እርሱ ከሰማይ የመጣበትን አብም ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን የላከበትን ፈቃዱንና ዓላማውን ሌላ ማስረጃ ተጠቅሞ ሲያብራራለት እንመለከታለን፡፡ ጌታችን በምዕራፍ 4 በያዕቆብ ጉድጓድ ዘንድ ላገኛት ሰማርያዊት ሴት የገለጠላት የከበረ እውነትም ይህንኑ ዘላለማዊ ፈቃድና ዓላማውን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ በትምህርቱ ውስጥ እንደምናገኘው ሴቲቱ ከያዕቆብ ዘር ናት፤ ምንም እንኳ የትና እንዴት እንደሚከናወን ግራ ብትጋባም ለእግዚአብሔር ስግደት (አምልኮ) ሊፈጸምለት እንደሚገባ ታውቃለች፡፡ ክርስቶስ የሚባል መሲህ እንደሚመጣም ግንዛቤ አላት፡፡ ይህች ሴት አለኝ በምትለው ዕውቀቷ ላይ ተመስርታ ነው ኢየሱስን የምትሞግተው፡፡ ሴቲቱ ያዕቆብን ብታውቅና አባታችን እያለች ብትመካም ከዚያም አልፋ ኢየሱስ ይሰጥሽ ነበር እያለ ከሚነግራት የዘላለም ሕይወት ውሃ ይልቅ ያዕቆብና ልጆቹ ከብቶቹም የጠጡት ውሃ ይበልጣል እያለች የእርሷ ውሃ እርሱ ከሚሰጣት የሚሻል እንደ ሆነ ለመግለጽ ብትደክምም ጌታ የዚህችን ሴት ጉድለትና የሚያስፈልጋትን ያውቃልና በትዕግስት ነው ያናገራት፡፡ ምክንያቱም ሴቲቱ አለኝ እያለች የደረደረቻቸው ነገሮች ሁሉ ተደማምረው ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊያደርሷት እንደማይችሉ ያውቃልና ነው፡፡ ሴቲቱ ግን ይህንን አልተገነዘበችም ነበር፡፡ ሴቲቱ በተመካችበት መንገድ ወደ እግዚአብሔር መንግስት መድረስ ቢቻል ኖሮ ክርስቶስ ለዚች ሴት ስለ ሕይወት ውሃ ማውራት አያስፈልገውም ነበር፡፡ እርሷ ተስፋ በምታደርጋቸው መንገዶች ወደ እግዚአብሔር ሃሳብ መድረስ ስለማይቻል ነው ኢየሱስ ግን ጉድለት አለብሽ ይህ ጉድለትሽ የሚሞላው ደግሞ በእኔ ስታምኚ ነው፤ እኔም ይመጣል እያልሽ የምትጠብቂው ክርስቶስ ነኝ፤ እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ለዘላለም አይጠማም፡፡ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘላለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እያለ የነገራት፡፡ ዛሬም ብዙዎች እንደዚች ሰማርያዊት ሴት የሚያስቆጥሩት የዘር ሃረግና የተነገረላቸው የተስፋ ቃል እንኳ ሳይኖራቸው በተረት ተረት የተቀመረ የአይሁድነት ታሪክ እየደረደሩ ለእግዚአብሔር ቅርብ ወዳጆችና የመንግስቱም ባለ መብቶች እንደ ሆኑ የሚናገሩ ሁሉ የዘር ሃረግ ወይም ከኢየሱስ ውጭ የሆነ ዕውቀት ወደ እግዚአብሔር መንግስት ለመግባት ቅንጣት ያህል ጠቀሜታ እንደማይኖራቸው ከሰማርያዊቱ ሴት ሊማሩ ይገባቸዋል፡፡ You can download the full version by clicking the free download button below...... በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው!! Free Download

http://nigat.net/%e1%8b%8b%e1%8a%93-%e1%8b%8b%e1%8a%93-%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%8b%a8%e1%88%b1%e1%88%b5-%e1%8a%a0%e1%88%b5%e1%89%b0%e1%88%9d%e1%88%85%e1%88%ae%e1%8b%8e%e1%89%bd-3/

ዋና ዋና የኢየሱስ አስተምህሮዎች : Missing argument 2 for wptr_supress_title() in /home/nigatcom/public_html/wp-content/plugins/title-remover/title-remover.php on line 16

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


USSR
Addis Ababa