Ethio Inform

Ethio Inform

Share

04/10/2021

talented actress ruta mengsteab

Photos from Ethio Inform's post 01/10/2021

ሰሜን ኮሪያ ሐሙስ ዕለት አዲስ የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል ሙከራ ማድረጓን ገለጸች .................................................
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አራተኛ የጦር መሣሪያ ሙከራዋ ሆኖ ተመዝግቧል።
ሰሜን ኮሪያ አዲሱን ሙከራዋን ያደረገችው የኒውክሌር አቅም
እንዳለው የሚታመነውን አዲስ የሃይፐርሶኒክ ሚሳኤል ሙከራ
ካደረገች ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሙከራዎቹ
"አለመረጋጋትን እና አለመተማመንን የበለጠ ይፈጥራሉ"
ብለዋል።
ፒዮንግያንግ የጦር መሣሪያው ራስን ለመከላከል የሚያስፈልጉ
መሆናቸውን በመግለጽ አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያን "ፍትሐዊ
ያልሆነ አቋም ይዘዋል" በማለት ወንጅላለች።
ሙከራዎቹ ምንም እንኳን ጥብቅ ማዕቀቦች ቢኖሩም
ፒዮንግያንግ የጦር መሣሪያ መሥራቷን ለማዘግየት ፍላጎት
እንደሌላት የሚያሳይ ግልፅ ምልክት ተደርገው ተወስደዋል።
በመንግሥታዊው የዜና ማሰራጫ ኬሲኤንኤ መሠረት አዲሱ
የፀረ-አውሮፕላን ሚሳኤል "አስደናቂ አፈፃፀም" ያሳየ ሲሆን
"አዳዲስ ቁልፍ ቴክኖሎጂዎችን" አካቷል ሲል ዘግቧል።
ሙከራው የተደረገው የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ-ኡን
ከደቡብ ኮሪያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ወደነበረበት መመለስ
እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው።
ኪም የአሜሪካን ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎን ከሰዋል። " አሜሪካ
ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በማታለል የጥላቻ ድርጊቱን
ለመደበቅ ሞክራለች" ብለዋል።
አንዳንድ ተንታኞች ፒዮንግያንግ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ግንኙነቷን
በማስቀጠል አሜሪካን በማስወጣት ዋሽንግተን እና ሴኡልን
ለመለያየት እንደምትፈልግ አመላካች ነው ብለው ያምናሉ።
ሆኖም ሰሜን ኮሪያ የማዕቀብ እፎይታን እና ሌሎች ድጋፎችን
አሜሪካ እንድታደርግላት የደቡብ ኮሪያን ድጋፍ ትፈልጋለች።
ሰሜን ኮሪያ ከዓለም ተቆራርጣ ከአንድ ዓመት በላይ
አሳልፋለች።
ወረርሽኙ በተከሰተበት ወቅት ከቅርብ አጋሯ ከቻይና ጋር
አብዛኛውን ንግዶች አቋርጣለች። በዚህም ምክንያት
ኢኮኖሚው በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ በመሆኑ የምግብ እጥረት
አሳሳቢ ነው ተብሎ ይታሰባል።
በመጋቢት ወር አገሪቱ ማዕቀቦችን ወደ ጎን በማለት የባልስቲክ
ሚሳኤሎችን ሞክራለች። ይህም ከአሜሪካ፣ ከጃፓን እና ከደቡብ
ኮሪያ ጠንካራ ወቀሳ አስነስቶባታል።
ባለፈው ወር የተባበሩት መንግሥታት የአቶሚክ ኤጀንሲ ሰሜን
ኮሪያ "በጣም አሳሳቢ" ያለውን ለኒዩክሌር መሣሪያዎች
የሚረዳ ፕሉቶኒየም ማምረት የሚችል ማብላያዋን እንደገና
እንደጀመረች ገልጿል።

Photos from Ethio Inform's post 01/10/2021

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፉ የቴሌኮም
ኮንፈረንስ ለስኬታማነቱ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና
ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለፀ
*******************
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ዓለም አቀፉ የቴሌኮም
ኮንፈረንስ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካንም የሚወክል
በመሆኑ ለስኬታማነቱ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና
ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አህመዲን መሐመድ(ዶ/ር)
አስታወቁ፡፡
የአለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ልማት ጉባኤ አዘጋጅ የኢትዮጵያ
ብሄራዊ ኮሜቴ ዝግጅቱን የተመለከተ ስብባውን አካሂዷል።
በአፍሪካ ለመጀሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ
በስኬት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች
እየተሰሩ መሆናቸውን ኮሚቴው አንስቷል።
የብሄራዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
ዴኤታ አህመዲን መሐመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት
የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኮንፈረንስ ኢትዮጵያን ብቻ
ሳይሆን አፍሪካንም የሚወክል በመሆኑ ለስኬቱ በትኩረት
እየሰራን ነው ብለዋል።
ዓለም አቀፉ የቴሌኮም ኮንፈረንስ በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን
ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከዓለም ሀገራት ልምድ የምንለዋወጥበትና
የኢትዮጵያን ገፅታ የምንገነባበት ይሆናል ያሉት ሚኒስትር
ዴኤታው፣ ለዝግጅቱ በስኬት መጠናቀቅ የሚመለከታቸው ሁሉ
በትብብር እንዲሰሩ አሳስበዋል።
Ebc

Photos from Ethio Inform's post 30/09/2021

ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው
ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)የአማራ ክልል
ትምህርት ቢሮ ሃላፊ የነበሩት ዶክተር ይልቃል ከፍአለ አስረስ
ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተሹመዋል፡፡
የቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኝው ተሻገር
አዲስ ለተመረጡት ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ
የስራ ርክክብ አድርገዋል።
ክልሉን ለአምስት አመታት መምራት የሚችሉ ምክትል ርዕሰ
መስተዳድርን ጨምሮ የቢሮ ሃላፊዎች ሹመት ይሰጣል።
ሹመቱ የስራ ሃላፊዎቹን የትምህርት ዝግጅት የአመራር ብቃት
እንዲሁም አካባቢውን በሚገባ የተረዳ መሆኑን መሰረት ያደረገ
ነው ተብሏል።
ebc

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa