BeteSeb Academy

BeteSeb Academy

Share

Photos from BeteSeb Academy's post 14/05/2026

🌍 የAABS 2026 Connect Conference በኢትዮጵያ አዲስ አበባ በይፋ ተከፍቷል፣ ከአፍሪካና ከውጭ አገራት የመጡ የቢዝነስ መሪዎች፣ አካዳሚያኖች፣ ፈጠራ ባለሙያዎች እና ተሳታፊዎችን በአንድ ቦታ አሰባስቦ ስለ የቢዝነስ ትምህርት ወደፊት አቅጣጫ ጠቃሚ ውይይቶችን አካሂዷል።

ኮንፈረንሱ በKibur College — የBeteSeb Academy እህት ድርጅት — አስተናጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የተካሄደ ሲሆን፣ በአፍሪካ የቢዝነስ ትምህርትና የመሪነት ልማት ውስጥ ትብብር፣ ፈጠራ፣ ስነ-ምግባራዊ አመራር እና በአፍሪካውያን የሚመሩ መፍትሄዎች ያላቸውን አስፈላጊነት አጉልቶ አሳይቷል።

በኮንፈረንሱ ውስጥ ስለ ወጣቶች ብቃት ግንባታ፣ ስራ ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂና AI፣ የዩኒቨርሲቲና ኢንዱስትሪ ትስስር እንዲሁም የአፍሪካ ኢኮኖሚ ለውጥ ላይ በርካታ ጠቃሚ ውይይቶች ተካሂደዋል። ✨🌍

📅 ግንቦት 5–7፣ 2018
📍 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Subscribe🔔Like,Comment&Share #ቀን 1 መጋቢት 6 የተጀመረው የመቄዶንያ የገቢ ማሰባሰቢያ MekedoniaFundraising #mekedonia 15/03/2026

ውድ ወላጆች !

ዛሬ መጋቢት 6 የሚጀመረው የመቄዶንያ ገቢ ማሰባሰቢያ ላይ የቤተሰብ አካዳሚ ተማሪዎቻችን እንደ ማዕከሉ አምባሰደርነታቸው መክፈቻው ሲያስጀምሩን በመቄዶንያ ቀጥታ ስርጭት 1:00 ሰዓት መተላለፍ የሚጀምር መሆኑን እየገለፅን ከታች በተቀመጠው ሊንክ ይከታተሉ ዘንድ በአክብሮት እናሳውቃለን።

"ደግነትን በትውልድ መካከል እንዝራ "

Subscribe🔔Like,Comment&Share #ቀን 1 መጋቢት 6 የተጀመረው የመቄዶንያ የገቢ ማሰባሰቢያ MekedoniaFundraising #mekedonia እየተካሄደ ባለው የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት የበኩልዎን ድጋፍ ያድርጉ!Subscribe🔔,Like👍,Comment💬&Share↗ያድርጉበግልዎ፣ በቤተሰብ ስም፣ በልጆችዎ ስም፣ በመኖሪያ መንደር ማህበር ስም፣ በዕድር...

08/03/2026

🌸 መልካም የዓለም የሴቶች ቀን!

ዛሬ የሴቶችን ጥንካሬ፣ ትጋት እና ስኬት እናከብራለን። ሴቶች ቤተሰብን በመገንባት፣ ህፃናትን በማሳደግ እና ማህበረሰብን በማጠናከር እጅግ ታላቅ ሚና ይጫወታሉ።

በትምህርት ቤታችንም ውስጥ ያሉ እናቶች፣ መምህራን፣ ሰራተኞች እና ተማሪዎች የሚያደርጉትን ታላቅ አስተዋጽኦ በክብር እናስታውሳለን እናደንቃለን። ትጋታችሁ፣ ትዕግስታችሁ እና አመራራችሁ ትውልድን የሚያነሳሳ ነው።

ሴቶች ሁሉ እድል እንዲያገኙ አቅማቸውን በሙሉ እንዲጠቀሙ መደገፍ እና ማበረታታት እንቀጥል።

✨ ለሁሉም ድንቅ ሴቶች መልካም የዓለም የሴቶች ቀን!

🌸 Happy International Women’s Day!

18/01/2026

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!
Happy Epiphany!

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
26761