Fact News
Fact news : Keep watching For All latest updates Of News All over woreld :::::::::::Fact news : Keep watching For All latest updates Of News All over woreld
15/12/2021
ስለ ቶማስ ጀጃው ሞላ
በግንባር በአካል በመገኘት በፋኖ አስተባባሪነት ያለማቋረጥ በትግሉ እየተሳተፉ ካሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች አንዱ Thomas Jejaw Molla ነው። ይህን ወጣት ያወኩት እዚሁ በሶሻል ሚዲያ ሰፈር ነው፤ ከዚህ የዘለለ ትውውቅ የለንም። ቶማስ ስለራሱ ብዙ እንዲነገርለት አይፈልግም...በጣም ትሁት ወጣት ነው። በተደጋጋሚ ከሚፅፋቸው ፅሁፎቹም እንደተረዳሁት ቶማስ በተናጠላዊ ሳይሆን በቡድን ሥራና ውጤት ከሚያምኑት ወገን ነው። ሆኖም በሚዛናዊና በሳል እንዲሁም ስሜት ባልጠለዛቸው ሀገር-ተኮር ፅሁፎቹ የተነሳ ዛሬ በይፋ በገፄ ያደረኩትን ቀደም ሲል በውስጥ ገፅ ከማመስገን ታቅቤ አላውቅም።
ታዲያ ከዕለታት አንድ ቀን ቶማስን በውስጥ መስመር አግኝቼው...አንተ ግንባር እየተፋለምክ ነውና ባለትዳር ከሆንክ ለቤተሰብህ እንኳን የአቅሜን ያህል ድጋፍ እንዳደርግ የባንክ ቁጥራቸውን ላክልኝ... አልኩት። ቶማስ "እኔ ገና ትዳር ያልመሠረትኩ ላጤ ነኝና ምንም አያስፈልገኝም" በማለት መለሰልኝ። በመቀጠልም...እሺ አንዴ አስቤበታለሁና አንተ ግንባር ስለሆንክ ለወላጆችህ እንኳን የተወሰነ ነገር ላድርግ... አልኩት። የቶማስ ምላሹ አሁንም "ወላጆቼ ለራሳቸው የሚበቃ ገቢ ስላላቸው ዕርዳታ አያስፈልገቸውም" በማለት መለሰልኝ። በመጨረሻም ጫናዬ ሲበዛ ለራሱም ለቤተሰቡም የነፈገውን ድጋፍ አጠገቡ ላሉ ፋኖዎች ለሎጂስቲክ አላማ እንዲውል ወስኖ በሐሳቡ ተስማማን።
ከደቂቃዎች በፊት ከቶማስ ጋር ከግንባር ሆኖ በውስጥ መስመር እያወራን እያለ "ለመስመር ሥራ እየወጣሁኝ ነው፣ ለማንኛውም እንበርታ" በሚል በተለመደው የማበረታቻ መልዕክቱ ንግግራችንን አቋርጦ ወደ መስክ ወጥቷል።
እስቲ እኔም መልዕክቴን ከመቋጨቴ በፊት ቶማስ ዛሬ ከግንባር ሆኖ ለኢትዮጵያውያንና ለመንግስት በገፁ ላይ ያስተላለፈውን መልዕክት ላካፍላችሁ፦
"ብዙዎች ለማንነታቸውና ለነፃነታቸው መከበር መተኪያ የሌለውን ወድ ሕይወታቸውን በሁሉም የጦር ግንባሮች እየከፈሉ ባሉበት ሁኔታ ጦርነቱን እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ንግድ ላይ የተሰማሩ የጦር መሳሪያዎችን ከወገን ጦር በተለያዬ መንገድ በመግዛት ወይም እንደሚዋጋ ሰው በልመና በመቀበል ለጠላት(ለሕወሓትና ለኦነግ ሸኔ) በከፍተኛ ገንዘብ በመሸጥ የሚያስታጥቁ፤ እንዋጋለን እያሉ ከግንባር የሚቀበሉትን የጥይት ፍሬን ለጠላት ጭምር አሳልፈው በከፍተኛ ገንዘብ የሚሸጡና በጥይት እጥረት የተነሳ ግን መልሰው መዋጋት እንዳልቻሉ መንግስትን የሚያማርሩ ነውረኞችና ሰነፎች፤ በእየግሮሰሪ አረቂ ቤቱ በየጫት መደቡ ተቀምጠው ግንባር ባለ ፋኖ ሰራዊት ወይም ጀግና ሰው ስም ሀብት ለመፍጠር ለማጭበርበር የሚዳክሩ፤ የወገን ጥምር ጦር በተቆጣጠረባቸው አካባቢዎች የመንግስታዊ መዋቅሩን ድክመት ተመልክተው ዘረፋ የፈፀሙና የሚፈፅሙ በፋኖ ስም የተሰማሩ የግል ጥቅም አራማጅ ወንጀለኞች ያድቡ ዘንድ የግድ በሚመለከተው አካል በትኩረት ሊሰራ ይገባል።
በየትኛውም ግንባር የተሰማራ ወይም ለመዝመት ፍላጎት ያለው ማንኛውም አካል ዲሲፕሊንድ ሊሆን ይገባል። ማንም ለንግድ ወይም በዘፈቀደ እንደልቡ በራሱ ስሜት ግንባር አካባቢ ሊንቀሳቀስ አይገባም። የወገንን ጦር በተቆርቋሪነት ስም ግንባር ድረስ ተገኝቶ በሀሰተኛ መረጃ በማሰራጨት በተለያየ መንገድ መሳሪያና ጥይት በመግዛት ትጥቅ የሚያስፈታ ሰራዊቱን የሚሸረሽርና የሚበትን የጠላት ተልዕኮ በተሸከመ አካል ላይ መንግስት እስካሁን የማያዳግም እርምጃ አለመውሰዱ የሚያሳፍር ቢሆንም አሁንም አልረፈደም። አንዳንድ የደህነት ባለሙያ ነን የሚሉ ሕገ-ውጥ የጦር መሳሪያ ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ለእነሱና ለሌሎቹም ሽፋን የሚሰጡ ባለስልጣናት ከድርጊታቸው ይታረሙ ዘንድ ሌሎችም ፈለጋቸውን እንዳይከተሉ ከታሰበ መቀጣጫ ሊሆኑም ይገባል። ማንም በዚህ የሕልውና ጦርነት በግንባር እየተገኘም ሆነ ከተማ ላይ ሆኖ በወንድሞቻችን መስዋዕትነት ገንዘብ ሊነግድ አይገባም። የሐገር ክህደት ወንጀልም ነው።
ማንነታቸውንና ነፃነታቸውን ለማስከበር ስለ እናት ኢትዮጵያ ሲሉ በክብር የወደቁትን የጀግኖቻችንን ደም እንደጠጣችሁት እንቆጥረዋለን። ጦርነቱን በሚመራው አካል ስር ሆኖ ወደግንባር የማይሰማራ ግለሰብም ሆነ ቡድን ለጠላት ጉልበት ሊፈጥር የሚችል የጥፋት ሃይል ነው። በተቆርቋሪነት ስም ወደግንባር ስንቅ ይዘው በመዝለቅ የወገንን ጦር አሰላለፍ ሁኔታ ለጠላት አሳልፈው የሚሰጡ የአምቡላንስ ሹፌሮችም ሆኑ ሎጅስቲክ የጫኑ ሹፌሮች ላይም ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል። ጦርነቱ እስካልተጠናቀቀ ድረስ በቸልታ ማለፍ አይገባም።
በዚህ የሕልውና ጦርነት የተጧጧፈ ንግድ ውስጥ ያላችሁ ሰዎች የወንድሞቻችንን ደምና አጥንት ሸጣችሁ ለመክበርና ለመብላት እንዳሰባችሁ ሳይሆን እንዳደረጋችሁት ልትቆጥሩት ይገባል። ደግሞም ነው። እንዴት የወንድማችሁ ስጋ ተላምጦና ጥሟችሁ ሊበላችሁ ይችላል? ደሙስ እንዴት ከጉሮሯችሁ ሊወርድላችሁ ይቻላችኋል? ከባድ ነው እኮ። እርም ነው።
ገንዘብ ለትራንስፖርት ለምግብ ለካርድ ለውጊያ ሲገባ መሳሪያ ጥይት መጠየቅና ለማግኘት መሯሯጥ የወግ ነው። ተገቢም ነው። ከዚህ ውጭ ላለ ነገር በሕልውና ጦርነቱ መነገድ ግን ከባድ ሀጢያት አረመኔነትም ነው። ስንት ጀግኖች አንድያ ነብሳቸውን በሁሉም የጦር ግንባር እየሰጡ ንግድ ላይ መሰማራትና ሀብት ለመፍጠሪያ ማሰብ ይቅርታ የማያሰጥ ወንጀል ነው። ከዚህ በላይ አሳፋሪና ጠላትነት ፈፅሞ ሊኖር አይችልም። እናም በዚህ የጥፋት የነውረኝነት እንቅስቃሴ ላይ ያለን ሰዎች ወደቀልባችን እንመለስ። ስንት አመትስ እንዳልተኖረ ነው። ቢበዛ 80 ነው እሱም ለተመረጡት ነው እንዲል መዝሙረኛው ዳዊት።
እንድታሰምሩበትና እንድታውቁት የምንፈልገው ጉዳይ ቢኖር መንግስት አስቸኳይ ኮማንድ ፖስቱ የተለመደውን የጥፋት አላማን እያየና እየሰማ ባላየና ባልሰማ ቢያልፋችሁ እና የለመዳችሁትን አፍራሽ የጥፋት አላማን በነውራችሁ አጊጣችሁ እናስቀጥላለን የምትሉ ከሆነ እኛ ባላየና ባልሰማ ልናልፋችሁ በሁሉም ግንባሮች እንዲሁም አጠገባችንም በክብር የወደቁ የፈሰሰው የጀግኖች ወንድሞቻችን ደም ይፋረደናልና ፈፅሞ አንችልም።ማን ምን መሆኑንና እየሰራ እንደሚገኝ ስለጥፋት አላማችሁ አስረጅ የሆነ ከበቂ በላይ ቴትራ ባይት መረጃ አለን።
ማንንም ለከት የለሽ የደም ነጋዴ አሳማና የትህነግ ጉዳይ አስፈፃሚን አካል መንግስት ያለምህረት የማያዳግም እርምጃ ሊወስድበትና ሕግ ሊያስከብር እንደሚገባው ደጋግመን እናሳስባለን።ግዴታውም ነው። ከሕልውና በላይ ምንስ ነገር ኖሮ ነው? ለእኛ አንዳችስ እንኳን‼️
እኛ የእነዛ ሀገር የገነቡ አኩሪ ታሪክ ሰሪ አይበገሬ አባቶቻችን ልጆች እንጅ የሀገር ሻጮችና አገር አፍራሽ ባንዳና የባንዳ ልጆች አይደለንምና አማራን አንገት ለማስደፋት ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚሰሩ የጥፋት አካላት ጋር ሕብረት ሊኖረን አይገባም‼️
ኢትዮጵያ ማህፀነ ለምለም የእልፍ ጀግኖች መፍለቂ
Getahun heramo
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa