ECLG Church
18/05/2026
እግዚአብሔርን መፈለግ
(2ኛ ዜና 15 :1 - 19)
የእግዚአብሔር መንፈስ በዓዛርያስ ላይ በመጣበት ግዜ ዓዛርያስ ወደ ይሁዳ ንጉስ ወደ አሳ መጣ አሳንም እንዲህ አለው እናንተ የይሁዳና የብንያም ሰዎች እግዚአብሔርን ፈልጉ ከእርሱ ጋር ሁኑ ከእናንተ ጋርም ይሆናል ብትተውት ይተዋችኃል ብትፈልጉትም ይገኝላቸዋል።
እስራኤልም ብዙ ዘመን ያለ እውነተኛ አምላክ ያለ አስተማሪም ካህን፣ ያለ ሕግ ይኖሩ ነበር
በመከራቸው ግዜ ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው በፈለጉት ግዜ አገኙት!
እስራኤል እግዚአብሔርን ባልፈለጉበት ግዜ ለብዙ መከራና ድንጋጤ ለመጨነቅና ሰላም ለማጣት ወገን ከወገን ከተማ ከከተማ ጋር ጦርነት ተላልፈው እንደተሰጡና እንደተዳረጉ እናንተም እንደ እነሱ እንዳትሆኑ እግዚአብሔርን ፈልጉ ለመልካም ሥራችሁ ብድራት አላችሁና ፍለጋችሁን ቀጥሉ በርቱ እጃችሁ አይላላ ብሎ በመንፈስ ሆኖ ብዙ መከራቸው አበረታታቸው እነሱም አሳና ሕዝቡ ሰሙ ለመጣላቸው ትንቢታዊ ድምፅ አዎንታዊ ምላሽ ሰጡ ፀያፉን ነገር ሁሉ ከከተማቸው አስወገዱ በእግዚአብሔር ቤት የነበረውን የእግዚአብሔርን መሠዊያ አደሱ መስዋት አቀረቡ።
ሕዝቡም ሁሉ ተሰብስበው እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ ቃል ኪዳን አደረጉ አዋጅም አወጡ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ሰው ይገደል የሚል ነበር ንጉሡ አሳ እናቱ መዓካ ጣኦት ተክላ የማምለኪያ አፀድ ስለሰራች ከእቴጌነቷ ክብር አወረዳት ጣኦቱንም ቀጥቅጦ አቃጠለው።
እግዚአብሔርም በምላሹ ተገኘላቸው በዙሪያቸው እረፍት ሰጣቸው። እግዚአብሔርን ከልብ ፈለጉት፤ እርሱም ተገኘላቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት ሰጣቸው። (2 ዜና መዋዕል 15:15)
.. የአሳ ልብ በዘመኑ ሁሉ ፈጽሞ ለእግዚአብሔር የተገዛ ነበር። (2 ዜና መዋዕል 15:17-18)
እግዚአብሔርም በምላሹ ከሰልፍና ከጦርነት ነፃ አደረገው አሳረፈው፤ እስከ ሠላሳ አምስተኛው የአሳ ዘመነ መንግሥት ድረስ ምንም ዐይነት ጦርነት አልነበረም። (2 ዜና መዋዕል 15:19)
ከዚህ የምንማራቸው መርሆች፦
መርህ 1፦ አገልጋዮች ልክ እንደ ነብዩ ዓዛርያስ ሕዝቡ ከልብ እግዚአብሔርን እንዲፈለጉ ጥሪ እንዳደረገና እንደመለሰ ትንቢታዊ ጥሪ እንድናደርግና በተለይ በዚህ ግዜ ትውልዱ ነፍሱ በተራቆተችበትና ተቅበዝባዥ በሆነበት ግዜ እንዲያርፍ ብቸኛው መንገድ እግዚአብሔርን መራብና መፈለግ ስለሆነ አበክረን ልናስተምርና ልንመልሰው ይገባል።
በማስታገሻ ቤተክርስቲያን ሳሚ ብቻ አናድርገው ትውልድ ታሟል ይፈወስ ታመናል እንፈወስ መንፈሳዊ ረሃብ ከሌለን መንፈሳዊ ሕመም ታመናልና እግዚአብሔር ይፈውሰን።
መርህ 2፦ መሪዎችና ሕዝቡ እግዚአብሔርን ለመፈለግ ልንሰበሰብ ልንወስን ልንጨክን ፀያፍ የሆነውን ነገር ከሕይወታችን ልናስወግድ ይገባል።
መርህ 3፦ ወደ እግዚአብሔር ቤት ልንሮጥና መሰዊያችንን(ሕብረታችንን፣ ፀሎታችንን አምልኮአችንን) ልናድስ ይገባል።
መርህ 4፦ አሳ በዘመኑ ሁሉ ለእግዚአብሔር እንደተሰጠ እኛም በዘመናችን ሁሉ ልንሰጥ ይገባል።
እነዚህን መርሆዎች መከተል ደግሞ የሚያመጡት ውጤት አለ።
እግዚአብሔር በሁሉም አቅጣጫ ዕረፍት እንደሰጣቸው ለእኛም በሁሉም አቅጣጫ እረፍት ይሆንልናል። አሜን!
ፀሎት
“አንተ ፊቴን ፈልጉ” ባልህ ጊዜ፤
ልቤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ፊትህን እሻለሁ አለች። (መዝሙር 27:8)
አቤቱ አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ አንተን የሚራቡበትን የሚፈልጉበትን መንፈሳዊ ረሃብ እንድተሰጣቸው ለአንተ ፍላጎት(ሃፒታይት) ካሳጣቸው መንፈሳዊ በሽታ በኢየሱስ ሥም ይፈወሱ! አሜን
በአገልጋይ ጌትነት አለሙ
ኤፍታሕ የሕያው እግዚአብሔር ቤ/ክ
02/05/2026
መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ፍላጎት ማጣት የመንፈሳዊ ሕይወት መታመም ምልክት ነው።
የምግብ ፍላጎት መቀነስ የበሽታ አንዱ ምልክት እንደሆነ ሁሉ ለእግዚአብሔርን ቃል ያለን ረሀብ መቀነስ በመንፈሳዊ ህይወት መታመም ምልክት ነው።
ምግብን መመገብ ረሀብን ከማስታገስ ባለፈ የተጎዳ አካልን ለመጠገን፡ አካልን ለማጠንከር፡ እድገትን ለማስቀጠል፡ አይምሮን ለማጠንከር፡ ጤናን ለመጠበቅ፡ ከዚያም ባለፈ በአጠቃላይ፡በሕይወት ለመቆየት ወሳኝ ነገር ነው።
ከዚህ በተሳሳይ ታዲያ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ለማሳደግ፡ ጠንካራ ለመሆን፡ ጤናማ ኑሮ እንዲኖረን፡ በአጠቃላይ ለመንፈሳዊ ሕይወታችን መቀጠል ወሳኝ ነው።
በክርስትና ህይወት ለማደግ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል መመገብ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።
ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በመጀመሪያው መልዕክቱ ምዕራፍ 2፥1-3 የቃሉን ወተት እንደ አዲስ ህጻን እንድንፈልገው የሚነግረን።
በዛሬው ዕለት ኤፍታሕ የሕያው እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የቤት ኅብረት የቃል ጥናት ተጀምሯል።
በዚህ ፕሮግራም ላይ የእግዚአብሔር ቃል ጥናት የተጀመረ ሲሆን መጥታችሁ በጸሎት ቃል በማጥናት ከእኛ ጋር ሕብረት እንድታደርጉ ተጋብዛችኋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the place of worship
Telephone
Website
Address
Bole Ararsa
Addis Ababa