Meri Konjoo

Meri Konjoo

Share

We reject the narratives of division and stand firm in our unity. #EthiopiaFacts #UnitedForEthiopia🇪🇹ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር። 🇪🇹
🙏

11/07/2026

በዱባይ፣ በቻይና፣ በአሜሪካ፣ በፈረንሳይና በኢንግሊዝ ጎርፍ ሲያጋጥም የተፈጥሮ አደጋ ሲባል አዲስ አበባ ላይ ትንሿ ጎርፍ እንደ ፖለቲካ ውድቀት የሚያዩ ተቃዋሚዎች ጤነኛ ናቸው?

ሰሞኑን በሶሻል ሚዲያ ላይ የተወሰኑ የብዕር አርበኞች አዲስ አበባ ውስጥ ለአጭር ጊዜ የታየውን ውሃ ይዘው “ከተማዋ በጎርፍ ተዋጠች፣ ኮሪደሩ አጥለቀለቀን” እያሉ ሲጨፍሩ ታዝበናል። የሚገርመው ግን መንገዱ ገና በግንባታ ሂደት ላይ ያለ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ (Drainage) ቱቦዎቹ ሙሉ በሙሉ ተቀብረው ያልተጠናቀቁበት የኮሪደር ልማት አካባቢ መሆኑ ነው። እንጀራ ገና ሳይጋገር ሊጥ ሆኖ እንደማይበላ ሁሉ፣ ግንባታው ያላለቀን መንገድ ይዞ የፖለቲካ ማጥቂያ ለማድረግ መሞከር የሰነፎች አካሄድ ነው።

ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች የዓለምን እውነታ ያውቁታል? በቴክኖሎጂ የመጠቁትና በቢሊዮን ዶላር መሠረተ ልማት የገነቡት እንደ ዱባይ፣ ኒውዮርክ፣ ሻንጋይ፣ ፓሪስ እና ለንደን ያሉ ኃያላን ከተሞች እንኳ በተፈጥሮ አደጋና በከባድ ዝናብ ወቅት መኪናዎች እስከመዋጥና መንገዶች እስኪዘጉ ድረስ የጎርፍ መጋጠሚያ እንደሚሆኑ አይተናል። በዚያ ሀገር የተፈጥሮ አደጋ የተባለው ነገር፣ እኛ ዘንድ ግንባታ ላይ ባለ መንገድ ላይ ውሃ ለአፍታ ሲቋጥር “የፖለቲካ ውድቀት” ተደርጎ የሚጮኽበት ስሌት ግራ የሚያጋባ ነው።

ልማት በሂደት የሚመጣ እንጂ በአንድ ጀምበር የሚፈጠር ተአምር አይደለም። አዲስ አበባን ውብና ዘመናዊ እያደረጋት ያለው የኮሪደር ልማት ስራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ፣ የውሃ ማስተላለፊያዎቹ ሲስተካከሉ ይሄ አሁን የሚታየው ጊዜያዊ ችግር ታሪክ ሆኖ ይቀራል። እስከዚያው ግን በተጋነነ ወሬና በፎቶ ስፌት የሕዝብን ልብ ለማሸበር የሚሞክሩ የሶሻል ሚዲያ ጀግኖች፣ ከጩኸታቸው በፊት የዓለምን እውነታና የልማቱን ሂደት በቅንነት ቢያዩ ይመረጣል።

11/07/2026

ሰበር ሓበሬታ |Breaking News
# አርሚ 70 ኣልቡርሃን ካብ ዝገዝኦም ነዊሕ ግዜ ኮይኑ ኣሎ : ሎሚ ኣብ ዝተኻየደ ኩናት ኮርሓደ ኣዛዚ ተሰዊኡ 'ሎ(ብስልኪ ደዊልኩም ምርግጋፅ ትኽእሉ ኢኹም ) :ሰለስተ ኮር ኮማንድ ድማ ቆሲሎም ' አለው ካብ ኮር ሓደ : ሰራዊት ትግራይ ከም ንብረት ዶብ ሰገር ብዶላር እንዳተሸጡ ኣብ ዘይዓዱን ዕላምኡን ብድሮናት :ብመካናይዝድ : ደመ ከልቢ ዝኾነ ሞት ይመውት 'ሎ ህዝቢ ትግራይ ደቅኻ ናብ ታዓሊም አይትስደድ ትርፉ ሞት ስለ ዝኾነ ::

#አርሚ 70 አልቡርሃን ከገዛቸው ረጅም ጊዜ ሆኖታል። ዛሬ በተደረገው የኮር አንድ ጦርነት አዛዡ ተሰውቷል (በስልክ ደውላችሁ ማረጋገጥ ትችላላችሁ)። ከኮር አንድ ሶስት የኮር ኮማንደሮች ደግሞ ቆስለዋል። የትግራይ ሰራዊት እንደ ድንበር ተሻጋሪ ንብረት በዶላር እየተሸጡ፣ ባልሆነ ሀገርና ዓላማ በድሮን እና በሜካናይዝድ ከንቱ የሆነ ሞት እየሞቱ ነው። የትግራይ ህዝብ ሆይ! ትርፉ ሞት ብቻ ስለሆነ ልጆችህን ወደ ማሰልጠኛ አትስደድ።

08/07/2026

የኦሎምፒክ ኮከቧ ጋቢ ቶማስ በአዲስ አበባ የነበራት ቆይታ አስደናቂ እንደነበረ ተናገረች

ታዋቂዋ አሜሪካዊት ኮከብ ጋቢ ቶማስ በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የሩጫ ውድድር እና ጎብኝት ያካሄደች ቢሆንም በአዲስ አበባ ከተማ የነበራት ቆይታ እጅግ አስደናቂ እና ልዩ እንደነበረ ገልፃለች፡፡

አትሌቷ ከተማዋን ከጎበኘችና የሩጫ ውድድር ካደረገች በኃላ ለጋዜጠኞች በሰጠችው ቃለ ምልልስ ፤ የመጀመሪያ መዳረሻዋ ስለነበረችው አዲስ አበባ ያላትን ልባዊ አድናቆት በመገልፅ የህዝቡ ሞቅ ያለ አቀባባል እና ተግባቢነት በሩጫ ህይወቷ ካየቻቸው ሀገራት ሁሉ የተለየ እና አስደሳች እንደነበረ በመግለፅ ፤ ቆይታዬ ልዩ እና አስደናቂ እንዲሁም አስደሳች ነበር ብላለች፡፡

አሜሪካዊቷ ጋቢ ቶማስ በሰጠችው ሀሳብ በሚቀጥለው ዓመትም ወደ አዲስ አበባ ለመምጣትና የሩጫ ውድድር ለማድረግ እንዲሁም አስደሳች ጊዜን ለማሳለፍ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ተናግራለች።

አዲስ አበባ የዓለም ኮከቦችን በፍቅር የምትቀበል ለሁሉም ተስማሚ ምቹና ለሁሉም ኩራት መሆኗን እያስመሰከረች ተገኛለች፡፡

07/07/2026
06/07/2026

ታላቅ ዜና ለሃገራችን ኢትዮጵያ! 🇪🇹

በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ማይ 2026 መረጃ መሠረት፣ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ በግዢ አቅም እኩልነት (PPP GDP) ቀዳሚዋ ሃገር ሆናለች! የሃገራችን የኢኮኖሚ መጠን 558.93 ቢሊዮን ዶላር በመድረስ በአንደኝነት ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ይህ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና ውስጥ ያለንን ትልቅ የኢኮኖሚ አቅምና ተስፋ የሚያሳይ ደስ የሚል ውጤት ነው።

የቀጠናው ቀዳሚ 5 ሃገራት በPPP GDP፦

1. 🇪🇹 ኢትዮጵያ – $558.93 Billion
2. 🇰🇪 ኬንያ – $435.21 Billion
3. 🇹🇿 ታንዛኒያ– $320.88 Billion
4. 🇺🇬 ኡጋንዳ– $208.41 Billion
5. 🇸🇩 ሱዳን – $195.42 Billion

ፈጣሪ ሃገራችንን ይባርክ! ወደ ላቀ የኢኮኖሚ እድገትና ብልፅግና ወደፊት!

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Addis Ababa