Axis Law

Axis Law

Share

11/09/2024
Telegram: Contact @MrYenesewD 14/08/2024

በገበያ ላይ እጥረት ያለበት መሆኑ የተገለፀን የንግድ ዕቃ ወይም ሸቀጥ በማከማቸት ወይም በመደበቅ ወይም በሕገ ወጥ መንገድ በማጓጓዝ የተሳተፈ አሽከርካሪ እስከ ብር 50 ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጣ የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ይደነግጋል።
ተሽከርካሪው የንግድ እቃዎችን ለመደበቅ እንዲያስችል ሆኖ የተሰራ ወይም የተለወጠ ወይም መደበቂያ አካል የተገጠመለት ከሆነ ወይም የተሽከርካሪው ባለቤት የሕገ ወጥ ማጓጓዝ ድርጊቱን እያወቀ እንዳይፈፀም ለመከላከል ወይም ለማስቆም ተገቢውን እርምጃ ሳይወስድ የቀረ እንደሆነ ተሽከርካሪው ከንግድ እቃዎቹ ጋር ይወረሳል።

#መውረስ #ንግድ #ቅጣት #ወንጀል #ሾፌር የሹፌሮች አንደበት #ተሽከርካሪ #ማከማቸት #ህግ #ማሸግ #ጠበቃ

Telegram: Contact @MrYenesewD

05/07/2024

ጉዲፈቻ ምንድን ነው? እንዴትስ ይቋቋማል?
ጉዲፈቻ ማለት ለችግር በተጋለጠና በተፈጥሮአዊ ወላጆቹ ሊያድግ ባልቻለ ህጻንና በጉዲፈቻ አድራጊ ወላጆች መካከል ህግን መሰረት አድርጎ የሚመሰረት ቋሚ የወላጅነትና የልጅነት ግንኙነት ነው።

የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ በአንቀፅ 193 የውጭ ዜጎች በጉዲፈቻ አድራጊነት ሊቀርቡ እንደሚችሉ ገልፆ የነበረ ቢሆንም ይህንኑ አንቀፅ ለመሻር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1070/2010 መሰረት የውጭ ዜጎች በጉዲፈቻ አድራጊነት ሊቀርቡ የሚችሉበትን እድል ዝግ አድርጓል። ሆኖም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሆኖ በዜግነት ግን የሌላ አገር ዜግነት ያለው ቢሆንም ለልጁ ደህንነት እና አስተዳደግ አስተማማኝ ማጣራት ከተደረገ በኋላ ሊፈቀድ እንደሚችል የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ. 189201 አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።

የጉዲፈቻ ግንኙነትን ለማቋቋም ምን ምን ጉዳዮች ሊሟሉ ይገባል?

ስለ ጉዲፈቻ ተደራጊ ህፃናት

§ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህጻናትን እንደየችግራቸው መጠን በሚመለከተው የመንግስት ተቋም በመመዝገብና በመመልመል በቅደም ተከተል መረጃቸው ተደራጅቶ ይቀመጣል።
§ ወላጆቻቸው በህይወት የሌሉ ከሆነ ይህንን የተመለከተ ማስረጃ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ወይም ከማዘጋጃ ቤት፣ ከቀበሌ(ወረዳ)፣ ከእምነት ተቋም ወይም ወላጆች የጠፉ ከሆኑ ከፍርድ ቤቶች መቅረብ ይኖርበታል፡፡
§ የህጻናቱን ጉዲፈቻ በተመለከተ ስምምነት ሊሰጡ የሚገባቸው ወደላይ የሚቆጠሩ አያቶች፣ ወደጎን የሚቆጠሩ አጎትና አክስት በተጨማሪም ስምምነት መስጠት የሚችሉ የህጻናቱ ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ወንድምና እህት ዝምድናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ከሚመለከተው የመንግስት አካል በማቅረብ ስምምነት መስጠት ይችላሉ፡፡
§ በህግ የሞግዚትነት ስልጣን የተሰጣቸው ግለሰቦች፤ የግል ወይም የመንግስት ህጻናት ማቆያና ማሳደጊያ ተቋማት እና የህጻናትን መብትና ደህንነት ለመከታተል ስልጣን የተሰጣቸው አካላት በጉዲፈቻው ላይ ስምምነታቸውን ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
§ ህጻናት ተጥለው ሲገኙ ህጻናቱን ያነሳው የአካባቢው የፖሊስ ጽ/ቤት ተጥለው የተገኙ ስለመሆናቸው ተገቢውን ማስረጃ መስጠት አለበት፡፡
§ ሁለቱም ወላጆቹ በህይወት ያሉ ከሆነ ሁለቱም በማይድን በሽታ የተያዙ መሆኑ በህክምና ማስረጃ መረጋገጥ ወይም ህፃኑን ለመንከባከብ በኢኮኖሚ ብቁ አለመሆናቸውን ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ህጋዊ ማስረጃ በማቅረብ የህጻኑን ደህንነት መጠበቅ የማያስችል ችግር መኖሩ መረጋገጥ አለበት።
§ በህይወት ያለው ወላጅ ልጁን በጉድፈቻ ለመስጠት ሲስማማ ስለ ሌላኛው ወላጅ ግልጽና የማያሻማ ሕጋዊ ማስረጃ ከሚመለከተው የፍትህ አካል ማቅረብ አለበት፡፡
§ ሌላኛው ወላጅ በሕይወት የሌለ ከሆነ ከእምነት ተቋማት፤ ከማዘጋጃ ቤት ወይም ወሳኝ ኩነቶች እንዲሁም ጠፍቶ ከሆነ የፍ/ቤት ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
§ ከጋብቻ ውጭ ስለሚወለዱ ሕፃናት አባታቸው በግልፅ የማይታወቅና እናታቸው ሕፃኑን ለማሳደግ የማትችል መሆኑን የሚገልጽ የህፃናትን ጉዳይ ከሚከታተል የአካባቢው የመንግስት አካል ወይም ከማህበራዊ ፍርድ ቤት የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
§ በህይወት ያለው ወላጅ ህጻኑን ለጉዲፈቻ ለመስጠት የፈለገበት ወይም የተገደደበት ምክንያቶችን የህጻናትን ጉዳይ ለመከታተል ስልጣን የተሰጠው የመንግስት አካል ወይም ከማህበራዊ ፍርድ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሊቀርብ ይገባል፡፡
§ በመጨረሻም ህጻኑን በተመለከተ ስላለበት ችግር፣ ወደ ህጻናት ማሳደጊያ የገቡበት ምክንያት በአካባቢው የሚገኝ የህጻናትን ጉዳይ ለመከታተል ስልጣን የተሰጠው የመንግስት አካል የሰጠው የጽሁፍ ማረጋገጫ መቅረብ አለበት::
አስፈላጊ ሰነዶች
§ ህጋዊነቱ የተረጋገጠ የጉዲፈቻ ውል፤
§ የፓስፖርት መጠን ያለው የህፃኑ አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ
§ የሕፃኑ የሥጋ ዘመዶች ወይም ሞግዚቶች ወይም አሳዳጊዎች ፎቶግራፍ
§ የህጻናት የልደት ማስረጃ፣ አጭር የህይወት ታሪክ፣ የጤና ማስረጃ
§ የጉዲፈቻ አድራጊው/ዋ/ዎች/ የጤና ሁኔታ ማስረጃ
§ የጉዲፈቻ አድራጊው/ዋ/ዎች/ የገቢ ሁኔታ ማስረጃ
§ የጉዲፈቻ አድራጊው/ዋ/ዎች/ ከወንጀል ነፃ የመሆን ማስረጃ
§ የጉዲፈቻ አድራጊው/ዋ/ዎች/ የትዳር ሁኔታ ማስረጃ
§ የጉዲፈቻ አድራጊው/ዋ/ዎች/ የእድሜ ማስረጃ
§ የጉዲፈቻ አድራጊው/ዋ/ዎች/ የስነልቦናና ማህበራዊ መስተጋብር ጥናት ማስረጃ
ዋና ዋና ሂደቶች
§ አስፈላጊ ሰነዶችን አሟልቶ በፍ/ቤት የጉዲፈቻ ፋይል መክፈት
§ ፍ/ቤት ጉዲፈቻውን ካፀደቀው በኋላ በአቅራቢያው ባለው የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ቀርቦ ጉዲፈቻውን ማስመዝገብ

05/07/2024

የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ እስከ ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ
የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ 1320/2016 መውጣቱን ተከትሎ እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዋጁ ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 7/2016 በማውጣት ሰኔ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ ምዝገባ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ በሁሉም ክፍለከተማ እና ወረዳዎች የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ምዝገባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት ከሰኔ1- ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ድረስ 248,469 የኪራይ ውል የተመዘገበ ሲሆን አሁንም ምዝገባው እንደቀጠለ የሚገኝ መሆኑንም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያሳውቃል።
በመሆኑም በርካታ ተመዝጋቢ በመኖሩ ምክንያት ቀኑ እንዲራዘም በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥያቄው በስፋት በመነሳቱ እና ቀሪ ያልተመዘገበው የተከራይ አከራይ ውል እስከ ሰኔ 30/2016 መዝግቦ ለማጠናቀቅ አዳጋች እንደሆነ ተቋሙ የተገነዘበ ስለሆነ በጊዜ ገደቡ ሳይመዘገብ የሚቀር ውል እንዳይኖር ለማስቻል የምዝገባ ጊዜውን ማራዘም በማስፈለጉ የምዝገባ ጊዜው እስከ ሐምሌ 24/2016ዓም መራዘሙን ቢሮው ይገልፃል።
የግል መኖሪያ ቤት አከራይም ሆነ ተከራይ የሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ሳይዘናጉ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሳይጠናቀቅ ጊዜያቸውን ተጠቅመው እንዲመዘገቡ ቢሮው በድጋሚ ያሳስባል።
የውል ምዝገባው ከመደበኛ የስራ ሰአት ውጪ በምሽት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ የሚካሄድ ስለሆነ ተመዝጋቢዎች ሳይጨናነቁ በተመቻቸው ሰአት መሄድ እና መመዝገብ ይችላሉም ተብሏል።

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Bole Medhanialem Church, Abrhams Building, 5th Floor
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 16:00
Tuesday 08:30 - 04:00
Wednesday 08:30 - 16:00
Thursday 08:30 - 16:00
Friday 08:30 - 16:00
Saturday 09:00 - 15:00