Irreecha Finfinnee
28/09/2025
26/09/2024
ኢሬቻ፡- የወንድማማችነትና የአንድነት ተምሳሌት
የኢሬቻ ምንነትና ታሪካዊ አጀማመር፣ የአከባበር ስርዓቱ፣ ሚስጥረ-በዓሉ፣ መቼት፣
ክፍል 1
ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ተቋርጦ የነበረዉ የሆራ ፊንፊኔ እሬቻ በዓል በ2012 ዳግም በድምቀት መከበሩ ይታወቃል። ይህን በዓል ዘንድሮም(2017) የኦሮሞ ህዝብ ከሌሎች ወንድም የኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር ሆኖ በጋራ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት ጀምሯል። በበዓሉ አማካይነትም የዚህ ባህል ዉበትና ጥንካሬ መሆኑንና በኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች መሀከል ያለዉን ወንድማማችነትና አንድነት የሚታደስበትና የጋራ አገር ለመገንባት እየተደረገ ያለዉን አገራዊ ጥረት ወደላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እንደሚሆን ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በየራሳቸዉ ማንነታቸዉንና ባህላቸዉን ጠብቀዉ ያቆዩበት የየራሳቸዉ ባህላዊ እሴቶች አላቸዉ። እያንዳንዳቸዉ ከሌሎች የሚለያቸዉ ባህላዊ መገለጫዎች እንዳላቸዉ ሁሉ ከሌሎች ህዝቦች ጋር የሚጋሩ ብዙ እሴቶች ይኖራቸዋል። የጋራ እሴቶቻችንን በማጉላት በልዩነታችን ዉስጥ አንድነታችንን ማጠናከርና ብዙሀነታችንን ለጋራ አገር ግንባታ ማዋል ጊዜዉ የሚጠይቅ ጉዳይ ነዉ። የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅና እሴቶቹንም አዲስቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት እንደተሞክሮ መዉሰድ የሚቻልበትን ሁኔታዎች ለመዳሰስና በዓሉን ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ ሊያከብሩት በሚቻልበት ሁኔታ የተመቻቸ ነው።
የኦሮሞ ህዝብ አንድም ነዉ፤ ብዙም ነዉ። በብዝሀነት ዉስጥ አንድና ጠንካራ ማንነት--ኦሮሞነትን የፈጠረ ብሔር ነዉ። ኦሮሞ በብዝሀነቱ ዉስጥ ጠንካራ አንድነት ሊመሰርት የቻለዉ ለዘመናት ይዞት በመጣዉ ባህላዊ እሴቶች ላይ ተመርኩዞ ነዉ። እነዚህ ባህላዊ እሴቶችን መለየትና ማብራራት እንደሞዴል ተወስደዉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች አንድ ጠንካራ ኢትዮጵያዊነት ለመገንባት የሚኖረዉ አሰተዋጽኦ ያበረታታል።
በ2017 ዓ.ም በፊንፊኔ ዉስጥ በሚከበረዉ የእሬቻ በዓል ላይ የከተማዉ ነዋሪ ስለበዓሉ ምንነትና አከባበር ስርዓት ላይ አስፈላጊ ግንዛቤ እንዲኖረዉና በዓሉን በጋራ በባለቤትነት መንፈስና በሀላፊነት እንዲያከብር እና በዓሉ በሰላም፣ በፍቅር፣ በወንድማማችነት ስሜትና አገራዊ አንድነትና ገጽታ በሚገነባ ሁኔታ በጋራ ለማክበር ከመንግስትና ከህዝብ እንዲሁም ከተለያዩ አካላት የሚጠበቅ ተግባራት ነዉ።
የእሬቻን በዓል በተመለከተ በአንዳንድ ወገኖች ዘንድ ያለዉን የተሳሳተ ግንዛቤ ለማስተካከል ይህ ጽሁፉ የኢሬቻ ምንነትና ታሪካዊ አጀማመር፣ የአከባበር ስርዓቱ፣ ሚስጥረ-በዓሉ፣ መቼት፣ ለምን፣ እንደሚከበርና በበዓሉ እነማን ከየት መጥተዉ እንደሚሳተፉ ለማሳየት ይሞከራል። እሬቻ ከማንኛዉም የፖለቲካ አመለካከትና ዓላማ ጋር ያልተያያዘና ባህላዊ የህዝብ በዓል መሆኑን ይታወቃል። በተጨማሪም ዋና ዋና እሴቶቹ ምን እንደሆኑ እና በብዝሀነት ዉስጥ ኦሮሞነትን እንዴት እንደገነቡ፤ ኢትዮጵያዊነትንና ህብረ ብሔራዊነትን ለመገንባት ያላቸዉ አስተዋጽኦም አለው።
በዓሉ በፊንፊኔ ከተማ መከበር ለከተማዉ ነዋሪዎች የሚያስገኘዉ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳዎች አሉት።
ኢሬቻ የገዳ ስርዓት መገለጫ ነዉ
• የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ የሰዉ ልጆች የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ሊስት (Representative List Of Intangible Cultural Heritage of Humanity) ዉስጥ “Sirna Gadaa: Sirna Hawaas-Siyaasaa Dimokraatawaa Ummata Oromoo (Gada System: An Indigenous Democratic Socio-Political System of the Orom) በሚል ርዕስ ጥቅምት 21 ቀን 2009 ዓም አለም አቀፍ ዕዉቅና አግኝቶ መመዝገቡ ይታወሳል።
• የጉሚዎች የገዳ ጉባኤዎች የሚካሄዱበት ስፍራዎች፣ ኢሬቻ፣ ሲንቄ፣ ሞጋሳ፣ጉዲፈቻ ጥቂቶቹ ናቸዉ። እነዚ ህባህላዊ ስፍራዎችና ተቋማት፣በዓላትና ስነስርዓቶች የገዳ ስርዓት በተጨባጭ የሚገለጽባቸዉና የስርዓቱም እሴቶችና ዕዉቀት ከትዉልድ ወደ ትዉልድ የሚተላለፉባቸዉ ስፍራዎች፣ ክንዉኖችና ህዝበ በዓላት ናቸዉ። በሌላ አገላለጽ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ ተጨባጭ (Tangible) መገለጫዎች ናቸዉ።
• በዩኔስኮ የሰዉ ልጆች የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስነት በተመዘገበዉ የገዳ ስርዓት ዉስጥ ኢሬቻ ከስርዓቱ ዋና ዋና መገለጫዎች ዉስጥ አንዱ መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነዉ።
ኢሬቻ የምስጋና፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ የእርቅ፣ የይቅርታ በዓል ነዉ
• ኢሬቻ የምስጋናና የምልጃ በዓል ነዉ። የኦሮሞ ህዝብ ሁሉን ነገር ለፈጠረዉ ሰዉን፣እንስሳትን፣ መሬትና ሰማይን፣ ቀንና ሌሊትን፣ ወንዝና ባህርን፣ ብርሀንና ጨለማን፣ዝናብ፣ ዕጽዋት፣ ህይወትና ሞትን ለፈጠረ፣ ሁሉን ነገር ማድረግ ለሚችል ዋቃ (አምላክ) ምስጋናና ክብር የሚያቀርብበት ስርዓተ-በዓል ነዉ። ላገኘዉ ጸጋና በረከት፣ሰላምና ደስታ፣ ጤናና ዕድሜ፣ ፍቅርና ክብር ለሚያምንበት አንድዋቃ (አምላክ) ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነዉ።ከዘመን ወደ ዘመን ከአንድ ወቅት ወደ ሌላ ወቅት በሰላም ያሸጋገረዉን አምላኩን የሚያመሰግንበትና መጪዉን ዘመን የሰላም የደስታ እንዲሆንለት የሚለምንበት ስርዓተ በዓልነዉ።
• በዚህ በዓል ለሰላም፣ በሰዉ ልጅና በተፈጥሮ መሀከል ስላለዉ ግንኙነት፣ ለዉልደት (fertility), ለጤና፣ ለሰብል፣ ለእንስሳትና ለአራዊት፣ ለዝናብና ለአየር፣ ለዕጽዋትና ለተክል፣ ለህጻናት፣ ለቤተሰብ፣ ለጎሳ፣ ለአገር፣ለመላዉ ዓለምና ለመላዉ የሰዉ ልጅ ሰላምና ደህንነት ፈጣሪዉን ያመሰግናል፣ ይማጸናል፣ ይመርቃል።በመሆኑም ኢሬቻ የምርቃት፣የምስጋና፣የተማጽኖ፣የዕርቅ፣የይቅርታ፣የሰላም፣የፍቅር፣የአንድነት፣የወንድማማችነት፣የበረከትና የቃልኪዳን በዓልነዉ።
• ከዚህም ባሻገር ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ የጋራ ባህሉንና ታሪኩን፣አንድነቱንና ወንድማማችነቱን የሚገልጽበት የሚያድስበትና የሚያጠናክርበት መድረክ ነዉ።የጾታ የፖለቲካ አመለካከትና የሀይማኖት ልዩነት ሳይገድበዉ የማንነቱ መገለጫ ባህሉን ታሪኩን የሚያስታዉስበትና የሚዘክርበት በዓል ነዉ።በዚህ ረገድ የማይዳሰስ ባህላዊ ቅርስ የአንድን ህዝብ ማንነት መገለጫና ይህ ማንነት ቀጣይነት እንዲኖረዉ ከትዉልድ ወደትዉልድ ኢንዲተላለፍ የሚያደርግ ለመሆኑ ኢሬቻ ህያዉ ማረጋገጫነዉ።
• ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሚከበሩት ሀይማኖታዊም ሆነ ባህላዊ ህዝበ-በዓላት ዉስጥ በአሳታፊነቱ ኢሬቻ ወደር የለዉም ማለት ይቻላል።
• የኢሬቻ በዓል በተለያዩ ቦታዎች የሚከበር ቢሆንም የኦሮሞ ህዝብ ላለፉት ሁለት አስር ዓመታት በታላቅ ድምቀት በቢሾፍቱ ከተማ ሆራ አርሳዲ ላይ በጋራ ሲያከብር ነበር። ሆራ አርሳዲ ላይ በሚከበረዉ ኢሬቻ ላይ ከመላዉ ኦሮሚያ ከ2 - 4 ሚሊዮን የሚገመት ህዝብ የሚሳተፍበት ክብረ በዓልነዉ።
• ወንድ ፤ሴት ፤ህጻን ፤ሽማግሌ ሳይል የፖለቲካ አመለካከትና የሀይማኖት ልዩነት ሳይወስነዉ በወርሀ መስከረም የመጨረሻ ሳምንት ዉስጥ የሚከበረዉ የሆራ አርሳዲ ኢሬቻ የሁሉም ኦሮሞ ህዝብ ትኩረትነዉ። በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ዉስጥ ከ10 ሚሊዮን የሚሆን የተለያየ ሀይማኖት የሚከተል ህዝብ ለአንድ ዓላማ ለአንድ በዓል በአንድ ጊዜ ወደ አንድመዳረሻ የሚጓጓዝበት ብቸኛ ክስተት ነዉ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Addis Ababa