ZER photography

ZER photography

Share

03/06/2022

ይቆለፍ ድንበሩ!!!

ፍቅር ሠላም አለፈ
ሰው ሰውን ጠለፈ
አንዱ አንዱን አንሳፈፈ ቀረፈ።
ሰው ሰውን ሊበላ አሠፈሠፈ
ሚዲያው ሰላም እደሌለን ለፈፈ።

ሰዎች ከቤታቸው ጠፉ
ያ በርሀ ያ ማእበል ክፉ
መቼም ለማይሞላ ኑሮ (ልፉ)2
በማያልቀው ጉዞ ልባቸውን ትፉ።
ባለ ቁርሾች ተስፋፉ
በእብሪት ልባቸውን ነፉ።

ደሞ እሱን ብሎ ሰላም ፍቅር አሣላፊ
ደሞ እሱን ብሎ አክትቪስት ይሄ ለፍላፊ።
ፖለቲካው ከሰው ወደ ሰው ተላላፊ
ሰው ሰውን በልቶ ሁሌ አሸናፊ
ሁሌ ከፊት ተሠላፊ።

ሀይ ባይ ሠው ጠፋ
ኑሮው ከፋ
የንቡ ቀፎ ባዶውን ቀረ ወቶ በተስፋ
አሥታራቂም ጠፋ።
አስመሣዩ በተንኮል ገፋ
እርግጥ
አገር ወዳድም አልጠፋ!
በቃላት እሚያዳፋ!
ተንኮል ጥላቻን እሚገፋ!
ድንበርን ከድንበር እሚሰፋ።

ነይ ሠላምን ዘምሪ ወፌ
ከሁሉ እንዳልቀር ተርፌ
ፍቅርን ርቄ እንዳልቀር ተንከርፍፌ
እንዳልቀር ተቆልፌ
ሠውም እንዳይለኝ ወፈፌ።

ፍቅርና ሠላምን አቅቶኝ ማለፍ
እንደሌላው እንደሌለው አስቤ ትርፍ
መክፈቻውን ሳልጠይቅ ቁልፍ
እንዳልልም እልፋን እልፍ።

ፍቅርና ሠላምን ገምዶና ጠልፎ
ለእንስሣም ይሠጥ ተርፎ
ከሰው ወደ ሠው እሚለውን አልፎ
በመንጋው ይሙላ የንቡም ባዶ ቀፎ
ድንበሩም ይዘጋ ይቅር ተቆልፎ!!!!

ሠውም ካፉ ጥሩ ቃልና ቀና ሀሳብ ካላወጣ ልክ እንደ ድንበሩ አንደበቱ ይቆለፍ። አብሶ በምላስ እየደለሉ አገርን ከፋፍሎና አንዱን ካንዱ አባልቶ በልጦና ከፍ ብሎ ለመታየት ለምትፈልጉ ያገራችን ሹማምንቶች ይሁንልኝ!።!።!........

Photos from ZER photography's post 15/04/2022
28/02/2022

በፍቅር እንጂ.... በፀብማ!!

ኢትዮጵያ ሀገሬ
እኛ ልጆችሽ እስኪ እንቁም ከፊትሽ
ምን አረክሽልኝ ብሎ ማነው እሚወቅስሽ
የሰው ልጅ ሲባል አጥፊ ነውና
ከስህተቱ ተምሮ እስኪሰጥሽ ምስጋና
ክብርሽ በአለም ላይ ይታይ
ያቃጭል ድምፅሽም ይሰማ
እስኪገባው ያለሽ ክብር ሞገስ ግርማ።

ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ምን ማለት
ብለህም አጠይቀኝ እኔም ጠልቄ አላቃት!።
ነገር ግን በትንሹ ልንገርህ
እኔ እማውቃትን ታህል ላጫውትህ
አባቶቼ ያሉኝን በታሪክ
እናት ነችና ሀገርክ
ብትሰበር የለህ ምትክ።
ኢትዮጵያ ማለት በቃ ኢትዮጵያ ናት
ከምንም ዘርፍ ከፋፍለህ እማታያት
በቃ ኢትዮጵያዊነትህን አትመርምራት
በልብህ ቀብረህ አኑራት
እንዲያው እየኮራህባት
ተማፀንላት ጥሩ መና
አምላክህን በልመና።

ትርጉሙ ነው ለካ
በሀገርክ ኩራ ተመካ።!!

ለሀገርህ ሥጥ ያለህን
ሠላም ካለክ ሰላምን
ፍቅር ካለክ ፍቅርህን።

በጠብ ለመጣብክ
ዱላህን ይዘህ ፈትለክ
የጦርህን ጫፍ ሣላት
ጋሻህን ይዘህ ዝመት
አሊያ አርግላት ስለት
ለምቶደው ታቦት።

ካንተ በላይ ያስባት እሡ
ከቀናት በለሡ
ይምጣልን በነጭ ፈረሡ
እንዳድዋው እንደለተ ቀኑ
ዛሬም ነገም ወደኛ ኑ ኑ !።

አሁንም እንደ ድሮው
በኢትዮጵያ በሀገሬ ላይ በዝቶል አንባጒሮው
ብረቱን አንሥቶ
ጠብ መንጃውም በዝቶ
አሁንም ሊገላት
ወደታች ሊጥላት
ይመኛል ሊበላት ሊያጣጥማት
እንዲያው ሀገሬው ጅል መስሎት።

እህ ልጆ መቼ ሠንፎለት
መቼ ደክሞለት
መቼሥ ጆሮው ሠምቶት
ቀድሞው ሠልቅጦት
የበሰበሰን ቆሻሻ ካልነኩት መች ይሸትና
ካላደፈረሱትስ መች ይጠራና
ሀበሻም እንዲያው ነውና
ካልነኩት አይነካ
ጠላት ፊት ፊቱ አይፈካ
አሞተ መራሩ እንዳይበላህ ሆላ
ለፍቅር ለፀብ አለው ቆንጆ መላ።

ዛዲያ ይህ ሁሉ ሲሆን
አልሠምቶም ወይ(2)
እንግዳው ላሣይ በጦር በሜዳው ታንተው ፊት ልታይ
ዘውድዬ ስንቁን ሸክፊ በይ
ለናት ሀገሬ ዘምቼ
ጠላቴን በጣጥሼ
በበላሁት ቊራርሼ
አልተወውም ቀምሼ
እንዲያው ነካክቼ
እጅ እጅ አሥብዬ
ብረቱን አሥጥዬ
ባንቺ በናቴ አስምዬ
ብሎ እንዲል ኢ..ት..ዮ..ጵያን
በፍቅር እንጂ በፀብማ ፈራን።

08/02/2022
Want your business to be the top-listed Photography Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Address


Addis Ababa