Addis Ababa Science and Technology University

Addis Ababa Science and Technology University

Share

01/06/2026
Photos from Addis Ababa Science and Technology University's post 06/05/2026

የአ.አ.ሳ.ቴ.ዩ ሰራተኞች እና ተማሪዎች የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖን ጎበኙ
ሚያዝያ 28/2018 ዓ.ም
+++++++++++++++++++++++++++
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ማዕከል የሆነው የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና መምህራን በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ የሚገኘውን “የኢትዮጵያ ታምርት” 2018 ኤክስፖን ጎበኙ።
ከሚያዝያ 25 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚቆየው ይህ ብሄራዊ የኢንዱስትሪ ምርቶች ትዕይንት ዩኒቨርሲቲው ካለው “ዩኒቨርሲቲ ለኢንዱስትሪ” መሪ ቃል አንጻር ከዘርፉ ጋር ያለውን ቁርኝት ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ አጋጣሚ ፈጥሯል።
ጉብኝቱ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የቀሰሙትን የንድፈ-ሀሳብ ዕውቀት ከሀገሪቱ ነባራዊ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ጋር እንዲያስተሳስሩ ዕድል የሰጠ መሆኑ ተገልጿል። በኤክስፖው ላይ የተገኘው የዩኒቨርሲቲው ልዑክ በተለይም በአዳዲስ የፈጠራ ስራዎችና ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ሰፊ ተሞክሮ የቀሰመ ሲሆን ይህም ለወደፊት የምርምር ስራዎቻቸው ትልቅ ግብዓት እንደሚያበረክት ተመልክቷል።
በኤክስፖው ወቅት በሀገር በቀል ፋብሪካዎች፣ በኢንቨስተሮች እና በአምራቾች መካከል የታየው ጠንካራ መስተጋብር ለተማሪዎች በአካል ተገኝተው ትልቅ ትምህርት የቀሰሙበት አጋጣሚ ሆኗል። ይህም ተማሪዎች የወደፊት የሥራ ዕድላቸውን አስቀድመው እንዲቃኙና ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ መንገድ የከፈተ ከመሆኑ በዘለለ በሀገራዊ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ተሰማርተው የራሳቸውን አሻራ ለማሳረፍ ከፍተኛ የሞራል መነሳሳትን እንዲያገኙ ረድቷቸዋል።
የኤክስፖው ዋነኛ ዓላማ የኢትዮጵያን ምርት ማበረታታትና ማስተዋወቅ እንደመሆኑ ዩኒቨርሲቲው በዚህ ታሪካዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊ በመሆን ለሀገራዊ ምርትና ምርታማነት ያለውን አጋርነት በተግባር አሳይቷል።
ይህ ጉብኝት ዩኒቨርሲቲው ለኢንዱስትሪው የሚመጥን በዕውቀትና በክህሎት የበለፀገ ጥራት ያለው የሰው ኃይል ለማፍራት የጀመረውን ጉዞ የሚያግዝ መሆኑ ተመላክቷል።
ስለ ዩኒቨርሲቲያችን ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ::
ድረ-ገፅ: https://www.aastu.edu.et
ፌስቡክ: http://facebook.com/aastu.edu.et
ቴሌግራም: t.me/pir2011
ኢሜይል:[email protected]/[email protected]
ዩቲዩብ :youtube.com/
ኤክስ (ትዊተር): x.com/aastu_addis
ሊንክድኢን: https://bit.ly/aastu_officialin

Photos from Addis Ababa Science and Technology University's post 02/05/2026

የሂሳብ ትምህርትን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ምህንድስና (STEM) ማገዝ ለተሻለ ውጤት እንደሚያበቃ ተገለፀ
ሚያዝያ 24/2018 ዓ.ም
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን ለማጠናከር በያዘው ዕቅድ መሰረት፣ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን "የሂሳብ ትምህርትን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ምህንድስና ማገዝ" በሚል ርዕስ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በስኬት ተጠናቋል።
በዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አሳታፊነት ዳይሬክቶሬት ድጋፍ የተደረገለት ይህ ፕሮጀክት በዋና ተመራማሪ ዶ/ር ሽመልስ በቀለ እና በረዳት ተመራማሪ ዶ/ር መላኩ በርሄ የተመራ ነው፡፡ የስልተናው ትኩረቱንም የሂሳብ ትምህርትን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ እና በተግባራዊ ትምህርት የታገዘ ለማድረግ የመምህራንን አቅም ማጎልበት ላይ ያተኮረ ነው፡፡
ለተከታታይ ስምንት ሳምንታት በሳምንቱ መጨረሻ ቀናት (ቅዳሜና እሁድ) ሲሰጥ የቆየው ይህ ስልጠና ከአራት የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ማለትም ከአቃቂ ቃሊቲ፣ ከቦሌ፣ ከንፋስ ስልክ እና ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ መምህራንን ያሳተፈ ነበር። በዚህ መርሃ ግብር ላይ በአጠቃላይ 81 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 24ቱ ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 57 መምህራን ደግሞ ወንዶች መሆናቸው ተገልጿል። ስልጠናው መምህራኑ መደበኛ የስራ ሰዓታቸውን ሳይለቁ በሳምንቱ መጨረሻ ዕረፍታቸው ላይ እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ ታስቦ የተመቻቸ እንደነበርም ታውቋል።
የፕሮጀክቱ ዋና ተመራማሪ ዶ/ር ሽመልስ በቀለ እንደገለጹት ስልጠናው የሂሳብ ትምህርትን ውጤት ለማሻሻል መምህራን ያላቸውን ሚና ማዕከል ያደረገ ነው። መምህራኑ ሂሳብን ከገሃዱ ዓለም ክስተቶች ጋር በማቀናጀት፣ ቴክኖሎጂን በመጠቀምና ከሌሎች የሳይንስ ዘርፎች ጋር በማስተሳሰር ለተማሪዎች ማቅረብ የሚያስችላቸውን አቅም እንዲገነቡ ተደርጓል።
ይህም ተማሪዎች ሂሳብን በንድፈ-ሀሳብ ብቻ ሳይሆን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ክህሎቶች ታግዘው ወደውት እንዲማሩ የሚያስችል መሆኑን ተመራማሪው አስረድተዋል።
በዕለቱ በተከናወነው የማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር አብረሃም ደበበ፣ የማህበረሰብ አሳታፊነት ዳይሬክተር ዶ/ር ቀናቱ አንጋሳ እንዲሁም የአዲስ አበባ ት/ም ቢሮ አመራሮች እና የክፍለ ከተማ ትምህርት ቢሮ ተወካዮች ተገኝተዋል።
በወቅቱም ዶ/ር አብረሃም ደበበ ባስተላለፉት መልዕክት አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር ስራው ጎን ለጎን የምርምር ውጤቶችን እና የማህበረሰብ አሳታፊ የሆኑ ስራዎች ወደ ማህበረሰቡ በማውረድ ረገድ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።
ዶ/ር ቀናቱ አንጋሳ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አሳታፊነት ዳይሬክቶሬት በቀጣይም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማፋጠን የሚረዱ መሰል የድጋፍ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
ሰልጣኝ መምህራን በሰጡት አስተያየት ስልጠናው አዳዲስ የማስተማር ስነ-ዘዴዎችን ያስጨበጣቸውና የሂሳብ ትምህርትን በሳይንስ፤ቴክኖሎጂ እና ምህንድስና የትምህርት ዘርፍ አቀናጅቶ ለመተግበር የሚያስችል ተጨማሪ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን ገልጸዋል።
ስለ ዩኒቨርሲቲያችን ዝርዝር መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ::
ድረ-ገፅ: https://www.aastu.edu.et
ፌስቡክ: http://facebook.com/aastu.edu.et
ቴሌግራም: t.me/pir2011
ኢሜይል:[email protected]/[email protected]
ዩቲዩብ :youtube.com/
ኤክስ (ትዊተር): x.com/aastu_addis
ሊንክድኢን: https://bit.ly/aastu_officialin

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Address


Akaki-kality Sub-city Woreda 9
Addis Ababa
16417