Anwar seid
Hasen taju!!!!!!!!!
በኡሁድን ዘመቻ የደረሰዉን ጊዚያዊ መጎሳቆልና ህመም ተከትሎ የወረዱ የቁርአን አንቀጾች 59 (አለ-ዒምራን 21-79) ሲሆኑ ባለፉት ጽሁፎች ያየነዉ ሁለቱን ብቻ ነዉ፡፡ እነርሱም ቢሆኑ ከቀናት በፊት በደረሰብን ስብራት የተጎዱ ስሜቶችን በቁርአን ለመጠገን የተመረጡ ናቸዉ፡፡ በእርግጥ የቁርአን ቅኝት፣ከታሪክ ተነስቶ፣ወቅታዊዉን ሁኔታ አስሶ፣ ዉጫዊዉን የትግል ሜዳ ፈትሾ፣ የነፍስያን የትግል መስክ ሀይሶ የሚያጽናናበት፣ ስብራትን የሚጠግንበትና የሚያስተምርበት መንገድ እጅግ ድንቅና ምሉእ፣እጅግ ማራኪ ከመሆኑ የተነሳ ተደጋግሞ ቢነበብም የማይጠገብ ሁልጊዜም አዲስ ነዉ፡፡ እነዚህን አንቀጾች ከነኋላ ታሪካቸዉ ለዓመታት ደጋግሜ ያነበብኳቸዉ ቢሆንም ዛሬም ለመጀመሪያ ጊዜ ያየኋቸዉ ያህል ያስደምሙኛል፡፡ የቁርአን ነገር ገራሚ ነዉ፡፡ ‹ላየንቀጢዑ ዐጃኢቡሁ›› ተብሎ የለ? አይተዉ የማይሰለቹት፣ ጠጥተዉ የማይጠግቡት፤ ኢማሙል አዕዞም 7000 ጊዜ አንብበዉ፣ ኢማሙ ሻፊዒ በየቀኑ እያኸተሙ ጥማቱ መች ወጣላቸዉ!? የሸኽ ሚስላይን ግጥም ልዋስ፡-
ምን የወጣ መጠጥ ሽታዉ እሚያሳብድ
ቢጠጡት አይሰለች ጥማት አያስወግድ
ከሆድ እማይጠፋ ስለቱ የማይበርድ
አከላት እንደጧፍ አያይዞ እሚያነድ
ላይ በላይ ግለቱ አክሎ እሚጀደድ
ሁሉንም ቢያወጉት ሆድ ባዶ ይቀራል፡፡ ከቁርአን የዑሁድ ቅኝት ከገረሙኝ ነገሮች መካከል ሁለቱን ብቻ አንስቼ ልሰናበት፡-
1. ቅኝቱ ሶስት የትግል መስኮችን ያጠቃለለ ነበር፡፡ የነፍስያን መስክ፣የአዕምሮን መስክና የዉጫዊ ትግል ሜዳን መስክ፡፡ ከሀጢአት ስለመመለስ፣ስለምህረት ልመና፣ስለመመጽወት፣ቁጣን ስለመቆጣጠር፣ስለ ይቅር ባይነትና በጎነት የሚተነትኑት አንቀጽ 130-136 የነፍስያን የትግል ሜዳ ይመለከታሉ፡፡ በዑለሞች ‹‹ትልቁ ጅሀድ›› የተሰኘና ብዙ ጥረት የሚጠይቅ ከባዱ የትግል መስክ ነዉ፡፡ በዚህ መስክ የተሸነፈ በሌላዉ ድል ቢቀናዉ እንኳ ከሳሪ ነዉ፡፡ ስለዚህ ‹‹አትራፊ ድል እንድትጎናጸፉ ወይም ሞታችሁ ዋጋዉ ከፍ ያለ እንዲሆን የነፍስያዉን የትግል ሜዳ ችላ እንዳትሉ›› የሚል መልዕክት ያስተላልፋል፡፡
በአዕምሮዉ የትግል ሜዳ ረገድ ስለአላህና ስለራስ፣ስለህይወትና ስለሞት፣ስለስኬትና ዉድቀት፣ ትግልን ከመሪ ግለሰብ ሳይሆን ከዕሴት ጋር ስለማስተሳሰር፣ ስለመሪና ተመሪ ግንኙነት ባህሪ ወዘተ በመለኮታዊ ጥበብ ግንዛቤ ያስጨብጣል፡፡
በዉጫዊዉ የትግል መስክ ረገድ በኡሁድ ዉሎ ላይ የታዩ ወታደራዊና ታክቲካዊ ግድፈቶችን ይሀይሳል፡፡
እነዚህ ሶስት የትግል መስኮች መሳ ለመሳ መሄድ ያለባቸዉ ናቸዉ፡፡ የነፍስያ ትግል ከተዘነጋ የትኛዉንም ጥረትና ስኬት ዋጋ ያሳጣል፡፡ የአመለካከት እነጻዉ ችላ ከተባለ ለተሳሳቱ ወይም ላልበሰሉ ዉሳኔዎች በመዳረግ ተጋላጭነትን ያስከትላል፡፡ የዉጫዊ ትግል መስክ ጠቀሜታ የታወቀ ስለሆነ ብዙ ማለት አያስፈልገዉም፡፡
2. የቁርአን ትምህርትና ተግሳፅ ዉጤት ያስመዘገበዉ ሳይዉል ሳያድር ነበር፡፡ ሶሀቦችን ከዚያ ሁሉ መጎሳቆል፣ስብራት፣ተስፋ መቁረጥ አዉጥቶ በደማቸዉ ዉስጥ አዲስ ሙቀት ለመርጨት ጊዜ አልወሰደበትም፡፡ ቁስላቸዉ ሳይደርቅ፣የአካል ስብራታቸዉ ሳይጠገን፣ነፍሳቸዉን በጨርቃቸዉ ቋጥረዉ ለአዲስ ተጋድሎ በአስደናቂ ብርታት እንዲሳሱ አደረጋቸዉ፡፡ ይህ ብርታት ይፈተነበትም ከስተት ዕዉን ሆነ፡፡ ይኸዉም ቁረይሾች በድል አድራጊ ስሜት፣ሙስሊሞችም በሽንፈት ስነልቦና ወደየመጡበት እንዲመለሱ ‹‹ሰይዱል ከዉነይን›› (ሰ0.ዐ.ወ) አልፈለጉም ነበርና ጠላትን ከኋላ ለማሳደድ በመወሰን ለተጎሳቆለ ሠራዊታቸዉ ጥሪ ሲያደርጉ ተአምር ታየ፡፡ ሁሉም ወደሞት ተሸቀዳደሙ- (አለዒምራን 172)
الَّذ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the university
Website
Address
Addis Abebe
Addis Ababa