Ethio plus
26/05/2026
ማን ነበረ? የማዉቀዉ መሰለኝ 🤔?
24/05/2026
እናንተ አከባቢ ድባቡ እንዴት ነዉ?
22/05/2026
ሀገር ቤት እያለ በከፍተኛ ትምህርት ተመርቆ ወጣቶችን በደስታና በታማኝነት ሲያስተምር የነበረው ጎበዝ መምህር ቀፀላ፣ የተሻለ ኑሮን ፍለጋ እና ቤተሰቦቹን ለመደገፍ በዲቪ ሎተሪ አማካኝነት ወደ አሜሪካ ያቀናል። ይሁን እንጂ ብዙዎች እንደሚያልሙት የአሜሪካ ህይወት ቀላልና አልጋ በአልጋ አልሆነለትም፤ ይልቁንም ያልታሰቡ ፈተናዎች ቀስ በቀስ ህይወቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ሌላ አቅጣጫ ቀየሩት። የቋንቋ አለመስማማት፣ በድንገት የገጠመው የቆዳ ጤና እክል እና ተደራራቢ የኑሮ ውጣ ውረዶች ስራ መስራት እንዳይችል ክፉኛ አዳከሙት።
ይህንን ተከትሎ የቤት ኪራይ መክፈል ያቃተውና የነበረችውን መኪና በዕዳ የተነጠቀው ወጣቱ ቀፀላ፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት መኖሪያውን ለማድረግ የተገደደው በቨርጂኒያ ግዛት ውስጥ በሚገኝ አንድ ጥቅጥቅ ያለ አስፈሪ ጫካ ውስጥ ነበር። በዚያ በሚያስፈራ ምድረ በዳ፣ በሚቆራርጥ የክረምት ብርድ፣ በበረዶና በከባድ ዝናብ ውስጥ በፌስታልና በሳር በተሰሩ መጠለያዎች ብቻ ተጠልሎ ሁለት ሙሉ ዓመታትን ማሳለፉን መስማት በእጅጉ አንጀት ይበላል። ችግርና ብቸኝነት ሲበዛበት የሰው ፊት መጋፈጥ ከብዶት፣ ወደ ኋላ መመለሻ መንገዱም ጠፍቶበት በዚህ መራራ ህይወት ውስጥ ለመቆየት ተገዷል።
ሆኖም ግን እኛ ኢትዮጵያውያን በችግርና በመከራ ጊዜ ወገናችንን ጥለን የማንወጣ፣ ሁልጊዜም በመተሳሰብና ለሰው በመድረስ የምንታወቅ ኩሩ ህዝቦች ነን። ዛሬ ቀፀላ ከዚህ ከገባበት የጨለማና የብርድ ህይወት ወጥቶ እንደገና የሰው ፊት እንዲያይ፣ ሙቀት ባለው መጠለያ ውስጥ እንዲያድርና ህክምና አግኝቶ ህይወቱን በአዲስ ተስፋ እንዲጀምር የሁላችንንም የድረሱልኝ ጥሪ እየጠየቀ ይገኛል። እሱ የሚፈልገው ትልቅ ነገር ሳይሆን ህክምና አግኝቶ፣ አነስተኛ መኪና ገዝቶ በዴሊቨሪ ስራ ራሱን መቻል ብቻ ነው። ስለዚህ የሰው ልጅ ክቡር ነውና ይህንን ወንድማችንን ከዚህ የጫካ ስቃይ ለመታደግ አቅማችን በፈቀደው መጠን የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ከጎኑ እንድንቆም ጥሪው ቀርቧል፤ ብዙዎችም ለዚህ በጎ ተግባር እየተረባረቡ ይገኛሉ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
4 Kilo
Addis Ababa