ethio 24

ethio 24

Share

05/05/2020

አጫጭር መረጃዎች ፦

- በኒውዚላንድ ለሁለተኛ ቀን በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ዜጋ አልተገኘም ተብሏል። ኒው ዚላንድ ጥላ የነበረውን ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብም እያላላች ትገኛለች -

- በቻይና ባለፉት 24 ሰዓት 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙን ሪፖርት አድርጋለች። በሌላ በኩል በሀገሪቱ ለስምንተኛ ተከታታይ ቀን ሞት አልተመዘገበም።

- በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰዓታት ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዘ ዝቅተኛው የሞት መጠን ተመዝግቧል፤ የሟቾች ቁጥር 1015 ሲሆን ይህም ከአንድ ወር በኋላ ዝቅተኛው ነው -

- ባለፉት 24 ሰዓት በደቡብ ኮሪያ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ ሁሉም ከውጭ ሀገር የገቡ ናቸው (በሀገር ውስጥ ቫይረሱ ሳይገኝ ሁለት ቀን ሆኖታል)

- ካምቦዲያ ባለፉት 3 ሳምንታት በኮቪድ-19 የተያዘ ሰው ስለመኖሩ ሪፖርት አላደረገችም። ካምቦዲያ በቫይረሱ ከተያዙ 122 ሰዎች 120ዎቹ በፍጥነት እንዲያገግሙ በመርዳት አመርቂ ውጤት አስመዝግባለች-

- ደቡብ አፍሪካ በትላንትናው ዕለት ብቻ 437 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጋለች። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 7,220 ደርሷል።

- ናይጄሪያ በአንድ ቀን ከፍተኛ ነው የተባለለትን በኮቪድ-19 የተያዘ የሰው ቁጥር ሪፖርት አድርጋለች፤ ባለፉት 24 ሰዓት 245 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 2,802 ደርሰዋል።

03/05/2020

በአሁኑ ወቅት አገሪቱ 27 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የለይቶ ማቆያ ማዕከል ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ ሲሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያም ገልጸዋል፡፡ በእነዚህም ከ9ሺህ በላይ ዜጎችን በማቆያው ውስጥ መሆናቸውን ነው ያስታወቁት፡፡

በቀጣይ ሁኔታዎች እየታዩ ዩኒቨርሲቲዎቹ 90 ሺህ ሰዎችን በለይቶ ማቆያነት እንዲይዙ ለማስቻል የማዘጋጀት ሥራ መሰራቱንና ከማቆያነት ባሻገርም ጊዜያዊ የመመርመሪያ ጣቢያ ሆነው እንዲያገለግሉ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል
ምንጭ-ENA

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Ethiopia, Addis Abeba
Addis Ababa
1000