Tafari Makonnen Polytechnic College

Tafari Makonnen Polytechnic College

Share

We offer outcome-based training across 11 departments and 40+ occupations, dedicated to be the Nation’s preferred choice for professional skilL.

Photos from Entoto PTC.tms's post 16/03/2026

የተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅን ታሪካዊ ዝና የሚያድስ የ500 ካሬ ሜትር ህንፃ ግንባታ ውል ተፈረመ ።
🇪🇹መጋቢት07/2018 ዓ.ም🇪🇹

የቀድሞ የተፈሪ መኮንን ተማሪዎች ማህበር (Alumni) ለተቋሙ እድገት እያበረከተ ያለውን ታላቅ አስተዋጽኦ በማጠናከር፣ በዛሬው ዕለት የጂ+3 (G+3) ህንፃ እና የአንፊ ቲያትር ግንባታ ውል ስምምነት ከሚሼል ኮንስትራክሽን ጋር በይፋ ተፈራረመ።

በ500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ የሚያርፈውና ከጀርባው ለብቻው የሚቆም ዘመናዊ አንፊ ቲያትር (Amphi-theater) የሚያካትተው ይህ ፕሮጀክት፣ የኮሌጁን ጥንታዊና ታሪካዊ ይዘት በጠበቀ መልኩ እንደሚገነባ ተገልጿል። ግንባታው በ18 ወራት ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት በአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የውጤት ተኮር ተቋማት ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ፣ ማህበሩ እያከናወነ ያለው ስራ ለሌሎች ቴክኒክና ሙያ ተቋማት አርአያ የሚሆን መሆኑን ገልጸዋል። "ማህበሩ ከዚህ በላይ ሰፊ አቅም ያለው በመሆኑ በቀጣይም ብዙ ይጠበቅበታል" ሲሉም አክለዋል።

የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ በመክፈቻ ንግግራቸው የቀድሞ የተፈሪ መኮንን ተማሪዎች ማህበር ለኮሌጁ እያደረገ ያለውን የላቀ ድጋፍ አድንቀዋል። ማህበሩ ለተቋሙ እድገት የቆመ ትልቅ አጋር መሆኑን በመጥቀስ በኮሌጁ ስም ጥልቅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የግንባታ ውሉን የቀድሞ የተፈሪ መኮንን ተማሪዎች ማህበር የካንትሪ ዳይሬክተርና የቦርድ ሴክሬተሪ ወ/ሮ ቆንጂት ተድላ እና የሚሼል ኮንስትራክሽን ባለቤት አቶ ነጋዳር አበሞ በጋራ ፈርመዋል። ማህበሩ በስራና ክህሎት ቢሮ በኩል ለሚደረግለት ድጋፍ ምስጋና አቅርቦ፣ በቀጣይም የተለያዩ የአልሙናይ ፕሮጀክቶችን ለማከናወን እቅድ እንዳለው ጠቁሟል።

ከህንፃ ግንባታው ጎን ለጎን የኮሌጁን የመቶ ዓመት ታሪክ ለትውልድ ለማቆየት የታሪክ መጽሐፍ የማጻፍ ስራ በይፋ ተጀምሯል። ጨረታውን ያሸነፉት የታሪክ መምህሩ ዶክተር አጉቾ አማረ ጥናቱን እንዲያካሂዱ የተለዩ ሲሆን፣ ለስራው መሳካት ኮሌጁ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ በማህበሩ ቀርቧል።

በመጨረሻም በኮሌጁ እና በቀድሞ ተማሪዎች ማህበር መካከል ያለውን አጋርነት ይበልጥ የሚያጠናክር የመግባቢያ ስምምነት (MoU) ተፈርሞ ፕሮጀክቱ በይፋ ተጀምሯል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://vm.tiktok.com
https://t.me/EntotoPtc1917
https://youtube.com/
https://www.facebook.com
ከኮሚኒኬሽን ቡድን

Photos from Entoto PTC.tms's post 16/03/2026

የተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ17ኛው የአዲስ የኪነ-ጥበብ ፌስቲቫል ላይ በድምቀት ተሳተፈ
🇪🇹መጋቢት06/2018 ዓ.ም🇪🇹

“የጥበብ ስጦታ ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አዘጋጅነት በመስቀል አደባባይ የተካሄደው 17ኛው የአዲስ የኪነ-ጥበብ ፌስቲቫል በታላቅ ድምቀት ተጠናቋል። በዚህ ታሪካዊና ጥበብ ተኮር መድረክ ላይ የተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በኤስቴቲክስ (Aesthetics) ስልጠና ዘርፍ አማካኝነት ተቋሙን በመወከል ንቁ ተሳትፎ አድርጓል።

ከመጋቢት 05 እስከ 07 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ የጥበብ ድግስ ላይ፣ ኮሌጁ በስልጠና ክፍሉ የሚያመርታቸውን የፈጠራ ስራዎችና የጥበብ ውጤቶች ለጎብኝዎችና ለጥበብ አፍቃሪያን አቅርቧል። ፌስቲቫሉ የጥበብ ስራዎች ለሀገር ከፍታና ለትውልድ ግንባታ ያላቸውን ፋይዳ ለማጉላት ያለመ ሲሆን፣ ተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅም በዘርፉ ያለውን የማሰልጠን አቅምና የሰልጣኞቹን ክህሎት በተግባር ያሳየበት መድረክ ሆኖለታል።

የኮሌጁ የኤስቴቲክስ ስልጠና ዘርፍ ተወካዮች እንደገለጹት፣ እንዲህ መሰል አህጉራዊና ሀገራዊ ይዘት ያላቸው ፌስቲቫሎች ሰልጣኞች ከገበያውና ከጥበብ ማህበረሰቡ ጋር እንዲተሳሰሩ ትልቅ እድል ይፈጥራሉ። በመስቀል አደባባይ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በቆየው በዚህ መርሃ ግብር ላይ በርካታ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የጥበብ ሰዎችና የአዲስ አበባ ነዋሪዎች መገኘታቸው ታውቋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://vm.tiktok.com
https://t.me/EntotoPtc1917
https://youtube.com/
https://www.facebook.com
ከኮሚኒኬሽን ቡድን

Photos from Entoto PTC.tms's post 09/03/2026

በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ "ለውጥን መቃወም" በሚል ርዕስ የልምድ ልውውጥ ተካሄደ።

🇪🇹30/06/2018 ዓ.ም🇪🇹

በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በየሳምንቱ የሚካሄደው "የወርቃማው ሰኞ" የጋራ የልምድ ልውውጥ መድረክ ለ27ኛ ሳምንት በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል። በዕለቱ የብረታ ብረት የስልጠና ዘርፍ አሰልጣኝ የሆኑት አቶ መኮንን ጣሰው "ለውጥን መቃወም" በሚል ርዕስ ሰፊና ትምህርታዊ ገለጻ ለኮሌጁ ማህበረሰብ አቅርበዋል።

አቶ መኮንን በአቀራረባቸው ለውጥን መቃወም ማለት ሰዎች አዳዲስ ሀሳቦችን፣ ቴክኖሎጂዎችን ወይም አሰራሮችን ለመቀበል የሚያሳዩት የመከላከያ ባህሪ መሆኑን አስረድተዋል። መቃወም በግል፣ በቡድንና በተቋም ደረጃ ሊከሰት እንደሚችል የገለጹት አሰልጣኙ፣ ይህም በስራ ፍጥነት፣ በምርታማነትና በእድገት ላይ የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ በዝርዝር አብራርተዋል።

ይህን ችግር ለመፍታትም የሚከተሉት የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተጠቁመዋል ስለ ለውጡ አስቀድሞ ሰፊ ግንዛቤ መፍጠር፤
ግልጽ የሆነ የኮሙኒኬሽን ወይም የመግባቢያ ስርአት መዘርጋት ፤ ሰራተኞችን በለውጥ ሂደቱ ላይ በንቃት ማሳተፍና ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ ፤ ለውጡን ለተቀበሉ አካላት ማበረታቻዎችን መስጠት።

አሰልጣኙ አክለውም የቴክኖሎጂ፣ የድርጅት አወቃቀር፣ የባህሪ እና የስትራቴጂ ለውጦችን በበጎ መልኩ በመቀበል ራስን፣ ተቋምንና ሀገርን ብቁ ማድረግ እንደሚገባ የራሳቸውን የህይወት ተሞክሮ በማጣቀስ አስገንዝበዋል።

የኮሌጁ የተቋማት ልማት አስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ዲን ዶ/ር ከበደ በሬቻ በአሰልጣኙ የቀረበውን ገለጻ አድንቀው፣ ተቋሙ ካለበት የለውጥ ጉዞ አንጻር ግንዛቤው ወቅታዊና ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ሌሎች የኮሌጁ ሰራተኞች መሰል የልምድ ልውውጦችን በማቅረብ የጋራ እውቀትን እንዲያሳድጉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://vm.tiktok.com
https://t.me/EntotoPtc1917
https://youtube.com/
https://www.facebook.com
ከኮሚኒኬሽን ቡድን

Photos from Entoto PTC.tms's post 05/03/2026

በተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የወንጀል መከላከል እና የጥበቃ ሰራተኛ ስነምግባር ስልጠና ።

🇪🇹26/06/2018 ዓ.ም🇪🇹

የወንጀል መከላከል ሲባል ቅድመ መከላከል ሲሆን የፍተሻ ስርአት ፣ የጥበቃ ስምሪት ፣የመኪና አፈታተሽ ፣ የሰው አፈታተሽ ፣የቀንና የማታ ስምሪት በዝርዝር ያካትታል ።

በተጨማሪም የጥበቃ ስነ ምግባር ምን መሆን እንዳለበት እና ቅንጅታዊ ስራዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋራ ተቀናጅቶ መስራት ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ።

የተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የህንፃ አስተዳደር ዳሬክቶሬት አቶ አላዩ ጉችዬ እንደገለፁት ስልጠናው በመነን ፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ በኩል እየተሰጠ ሲሆን ስልጠናው የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠናዎችን ያካተተ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል ።

ስልጠናው ከዚህ በፊት የተሰጠ መሆኑን አስታውሰው የጥበቃ ሰራተኛ በየጊዜው እራሱን በመፈተሽ እንዲበቃ ታስቦ የተዘጋጀ የማጠናከሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫና የማነቃቂያ ስልጠና እንደሆነ አብራርተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://vm.tiktok.com
https://t.me/EntotoPtc1917
https://youtube.com/
https://www.facebook.com
ከኮሚኒኬሽን ቡድን

Photos from Entoto PTC.tms's post 05/03/2026

የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ በተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ እየተከናወነ የሚገኘውን የማሽነሪዎች ጥገና ተጀመረ።
🇹25/06/2018 ዓ.ም🇪🇹
የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የጥገና ቡድን በተፈሪ መኮንን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የውስጥ አቅምን በመጠቀም እየተከናወነ የሚገኘውን መጠነ-ሰፊ የማሽነሪዎች ጥገና በቦታው ተገኝቶ አስጀመረ።
የጥገናዉ ዋና ዓላማ ከየኮሌጁ በመጡ ባለሙያዎች አማካኝነት ለረጅም ጊዜ አገልግሎት ሳይሰጡ የቆዩና ብልሽት የገጠማቸውን ማሽነሪዎች ወደ ስራ ለማስገባት እየተከናወነ ያለውን ስራ ለማስጀመር እና ለመከታተ እንደሆነ ተገልጿል።
የኮሌጁ እና ከየኮሌጁ በመጡ ባለሙያዎች የራሳቸውን እውቀትና ክህሎት በመጠቀም የጥገና ስራውን እያከናወኑ መሆኑ ከፍተኛ ወጪን እንደሚያድን ተመልክቷል።
ለተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችና ለማምረቻ ስራዎች የሚያገለግሉ ማሽነሪዎች ጥገና ተደርጎላቸው ወደ ስራ ለመመለስ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።
የክህሎት ሽግግር፦ ይህ የጥገና ሂደት ለባለሙያዎቹ ልምድ ከመሆኑ ባለፈ፣ ሰልጣኞችም በተግባር የተደገፈ ስልጠና ለመስጠት እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።

የቢሮው የጥገና ቡድን አባላት በምልከታቸው ወቅት ባስተላለፉት መልእክት፣ ኮሌጁ የቆዩ ማሽኖችን በመጠገን ዳግም ለአገልግሎት እንዲውሉ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታና ለሌሎች ተቋማትም አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ የጥገና ዘመቻ በተቋሙ የሚገኙ የማስተማሪያ ግብዓቶችን ጥራት ከማሻሻሉም ባለፈ፣ ለከተማዋ የኢንዱስትሪ እድገትና ለስራ እድል ፈጠራ የሚሰጠው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተመልክቷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://vm.tiktok.com
https://t.me/EntotoPtc1917
https://youtube.com/
https://www.facebook.com
ከኮሚኒኬሽን ቡድን

Want your university to be the top-listed University in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Gulele
Addis Ababa
1033