Addufiker

Addufiker

Share

27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች
በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው ታላቁ የኢድ አል አድሃ
(አረፋ) በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ!

ዒድ ሙባረክ!

Photos from Addufiker's post 16/01/2026

ነብስህ በሰላም ትረፍ

02/11/2024

ነፃ ሕክምና
የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ Smile train ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ላለባቸው ሕጻናት እና አዋቂዎች ነፃ የቀዶ ሕክምና አገልግሎት በመደበኛነት ሳምንቱን ሙሉ ይሰጣል::

እንግዲያውስ የከንፈርና ላንቃ ክፍተት ችግር Cleft lip እና Cleft palate ያለባችሁ በመሉ በ 0948898284 በመደወል ወይም ወደ አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመሔድ መመዝገብ ይችላሉ::

ከአዲስ አበባ ውጭ ለሚመጡ ታካሚዎች የትራንስፖርት እና የምግብ አገልግሎት እንዲሁም ለሚያድሩት ;የአልጋ (መኝታ ) ወጪ ይሸፈናል፡፡

09/09/2024

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 36 ሺህ 409 ፈተናውን ማለፋቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 674 ሺህ 823 ተማሪዎች መካከል 36 ሺህ 409 ተማሪዎች ፈተናውን ማለፋቸውን ተናግረዋል።

በዚህም ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች 5 ነጥብ 4 በመቶ አልፈዋል ብለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ 1 ሺህ 363 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ገልጸዋል።

የዘንድሮው ዓመት አጠቃላይ ውጤት ካለፉት ሁለት ዓመታት አንጻር የተሻለ መሆኑንም ተናግረዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከል ከ600 ከታረመው ፈተና ከፍተኛው ውጤት 575 መሆኑን ተናግረዋል።

ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 1 ሺህ 220 የሚሆኑት ከ500 በላይ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጸዋል።

ከነዚህም መካከል 384 ቱ ሴቶች መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

ጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም

Photos from Addufiker's post 26/08/2024

በትወና እና ፊልም ዘርፍ ስመጥር የኾነው አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ/ጣሰው/ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ።
ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጆች፣ ጓደኞች አድናቂዎቹ መፅናናትን እንመኛለን። ነብሱ በሰላም ትረፍ።

Want your business to be the top-listed Shop in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa