Nati Sw
31/12/2023
የመለያየቱ መፍትሔ መወያየት ነው።😂😂😂😀
21/12/2023
1-. አልበርት አንስታይን
አንስታይን ከ1879-1955 የኖረ ታላቅ የሳይንስ ሊቅ ነበር። በተለይ ሁለት ግኝቶቹ የሳይንስ እይታችንን በእጅጉ የቀየሩ ሲሆን አንስታይን ምድራችን ካፈራቻቸው የሳይንስ ሊቆች ውስጥም ሆነ ወደፊት ከሚወለዱት ውስጥ ተወዳዳሪ አይገኝለትም የሚባል ብርቅዬ ሳይንቲስት ነው።
አንስታይን በልጅነቱ ዳይስሌክሊስ (ሲያነቡ ወደ ግራ የሚያነቡ) የነበረ ሲሆን በትምህርቱ ደካማ በመሆኑ አስተማሪዎቹ ደደብ አድርገው ይገምቱት ነበር።
በ15 ዓመቱ ትምህርቱን አቁሞ ከዓመት በኋላ ዙሪክ የሚገኝ አንድ ፖሊ ቴክኒክ ለመግባት አመልክቶ የመግቢያ ፈተናውን ወድቋል።
ይህ ሰው ግን በፊዚክስ ንድፈ ሃሳብ ዓለምን በመቀየሩ የኖቬል ሽልማት ለመሸለም የበቃ ድንቅ ሳይንቲስት ነው።
2- ቤንጃሚን ፍራንክሊን
ይህ ሰው የሂሳብ ትምህርት አይሆነውም ነበር። እናም አባቱ ከትምህርት ቤት አስወጥቶ ሻማና ጧፍ ሲያሰራው አደገ። ነገር ግን ይህ ሰው አሜሪካ ካፈራቻቸው ታላላቅ ሰዎች አንዱ በመሆን ታዋቂ ፖለቲከኛ፣ ሳይንቲስት፣ ጸሐፊ እና የፔንሲልቫኒያ ፕሬዚዳንትና የአሜሪካ መስራች አባት ለመባል የበቃ ሰው ነው።
3- ቻርለስ ዳርዊን
ወጣቱ ዳርዊን በትምህርቱ በመድከሙ አባቱ "አንተ ከአደን እና ውሻ በስተቀር የምትወደው ነገር የለም፤ ስለዚህ ለራስህም ሆነ ለቤተሰብ ውርደት እንዳትሆን" ብሎ ከትምህርት ቤት አስወጣው።
የህክምና ትምህርት ሞከረ አስጠላው። የሃይማኖት ትምህርትም ሞክሮ ነበር አልሆነለትም። ብዙውን ግዜውን ግን ከስፖርተኞች ጋር ነበር የሚያጠፋው።
ይህ ሰው ግን በመጨረሻ አጠቃላይ የስነ-ህይወት ሳይንስን ለመቀየር ችሏል።
4- ሴናተር ኤድዋርድ ኤም ኬኔዲ
ይህ የማሳቹሴትስ ሴናተር በአንድ ወቅት ለአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ሁሉ ተወዳድሯል። ግን ፈተናውን ጓደኛው ሲፈተንለት ተይዞ ከሚማርበት ሃርቫርድ ዩኒቨርስቲ ተባርሮ ነበር።
5- ሰር ዊንስተር ቸርችል
ይህ ሰው ታላቅ እንግሊዛዊ ፖለቲከኛ፣ ገጣሚ፣ ደራሲና ሰዓሊ ሲሆን እንግሊዝን በአንደኛ እና ሁለተኛ የዓለም ጦርነት በተለያየ የመንግስት ስልጣን ደረጃ የመራ ታላቅ የፖለቲካ ሰው ነው። (በአገራችን መዲና አዲስአበባ ጎዳና በስሙ ተሰይሞለታል)
ቸርችል ይህቺ ምድር ካፈራቻቸው ድንቅ የፖለቲካ ሰዎች አንዱ ቢሆንም በትምህቱ ደካማ ስለነበር ሮያል የውትድርና ኮሌጅ ለመግባት ከአንዴም ሁለት ግዜ ተፈትኖ በመውደቁ መግባት አልቻለም ነበር።
6- ቶማስ ኤድሰን
ይህ ታላቅ ፈላስፋ ትምህርት ቤት የሄደው ለሶስት ወራት ብቻ ነበር። ምክንያቱም በስምንት ዓመቱ አስተማሪው "ደደብ" ብሎ ስለሰደበው እናቱ ከትምህርት ቤት አውጥታ ቤት ውስጥ አስተማረችው። በዘጠኝ ዓመቱ ይሞክራቸው የነበሩት ነገሮች ከእናቱ አቅም በላይ ሆኖ ተገኝቷል።
ቶማስ ኤድሰን በህይወት ዘመኑ አንድ ሺህ አዳዲስ ግኝቶችን የፈለሰፈ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ የኤሌክትሪክ ብርሃን እና ሸክላ ማዘፈኛ ሲኖሩበት ያሻሻላቸው ነገሮች ደግሞ ፊልም ማሳያ፣ ቴሌፎን ይገኙበታል።
7- አይዛክ ኒውተን
ይህ ሰው ደካማ ውጤቶች ስለነበሩት ከትሪንቲ ኮሌጅ ሆነ ከካምብሪጅ ዩኒቨርስቲ ሲመረቅ የክብር ወይም የማዕረግ ተመራቂ አልነበረም።
ነገር ግን በታሪክ ከታወቁት ታላላቅ የሳይንስ ፈጣሪዎች አንዱ በመሆን የዘመኑ ሳይንስ በእርሱ ስራዎች ላይ ለመመርኮዝ በቅተዋል።
---------------------------------
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Culinary Team
Attire
Website
Address
Wolaita S**o
Addis Ababa