Habeshawi Style
24/05/2024
ዶ/ር አብዬ አህመድ "ዛሬ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) አስጀምሯል።
ይህ ስራ ለዜጎች መሰረታዊ አገልግሎት ለመስጠት ታልሞ የሚከናወነው የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ አካል ነው። የሁሉንም ዘርፎች ምሉዕ አቅም ለማሳካት በዲጂታል ኢትዮጵያ መደገፍ አለባቸው።
ባለፉት ስድስት አመታት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ስርዓት ተሸጋግሯል። የህዝብ ብዛት እየጨመረ ባለበት ከተማችን ንቁ የዜጎች ተሳትፎ እጅግ አስፈላጊ ነው። ዛሬ ወደስራ የገባው መተግበሪያ በapp ስቶር እና playstore የሚገኝ ሲሆን ዜጎች ወንጀልን ለመከላከል በፎቶግራፍ፣ በቪዲዮ፣ በድምፅ፣ በሰነድ ወይም በቀጥታ በመደወል ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያስችላል።
ሁሉም ዜጋ የአካባቢያችንን እና ከተሞቻችንን ደህንነት ለማስጠበቅ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቀርባለው።"
Dr. Abiy Ahmed "Today, the Federal Police Commission, in collaboration with the Artificial Intelligence Institute, launched the EFP Citizen Engagement App.
This initiative is part of the Digital Ethiopia strategy, which aims to deliver essential services to citizens. To achieve its full potential, all sectoral work must be supported by Digital Ethiopia.
Over the past six years, the Federal Police has transitioned from analogue to digital systems. In our increasingly populated city, active citizen engagement is crucial. Available on the App Store and Play Store, this app enables citizens to actively participate in preventing criminal activities by providing tips via photo, video, voice, documents, or direct calls.
I urge all citizens to be proactive in securing our neighborhoods and cities."
via;twitter
18/02/2024
አንጋፋውና ስመጥሩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 271 የህክምና ተማሪዎችን በትናንትናዉ እለት አስመርቋል:: #ኢትዮጲያ | በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙዔል ክፍሌን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።ከተመራቂዎች መካከል 158 ወንዶች ሲሆኑ 113 ደግሞ ሴቶች ናቸው።ከነዚህ ውስጥ ፦በህክምና ትምህርት ዶክትሬት ዲግሪ 240፣ በጥርስ ህክምና ዶክትሬት ዲግሪ 9, በ 'ቢኤስሲ' አኔስቴዥያን ባችለር ዲግሪ 22 ተማሪዎችን አስመርቋል።ከተመራቂዎች መካከል 198 የሚሆኑት በማዕረግ፣ በከፍተኛ ማዕረግ እና በእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ የተመረቁ ናቸው።
መንትዮቹ ዶ/ር ቸርነት ተስፋሁን እና ዶ/ር ብሩክ ተስፋሁን በህክምና ዶክተሬት በ ከፍተኛ ማዕረግ በሌላ በኩል 3.87 GPA ከሴት ተማሪዎች መካከል ዶ/ር ረድኤት ጌቱ ከበደ በህክምና ዶክትሬት በ3.87 በማስመዝገብ ተሸላሚ ሆናለች እንዲሁም ዶ/ር ሚካኤል አዘነ ንጉሴ🥇በህክምና ዶክትሬት 3.93 GPA በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኖል።
Addis Ababa University graduated 271 medical students yesterday. The graduation ceremony was attended nullby other invited guests, including the Minister of State for Health, Dr. Derje Duguma, and the President of Addis Ababa University, Dr. Samuel Kfle. Among the graduates, 158 are men and 113 are women. Doctorate in Medicine 9, Bachelor Degree in 'BSc' Anesthesiology graduated 22 students. Among the graduates, 198 graduated with Honors, Honors and Very Honors.
The twins, Dr. Cherenat Tesfahun and Dr. Brooke Tesfahun, received a doctorate in medicine with a high rank. Among the female students, Dr. Redet Getu Kebede was awarded with a doctorate of medicine with a score of 3.87 and Among the 249 students who graduated from the oldest Addis Ababa University Dr. Michael Azen Nguse was awarded a doctorate of medicine with a 3.93 GPA. He has been awarded a gold medal.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa