Health Tips
02/02/2025
የሐዘን መግለጫ
============
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽት እና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊት ሃኪም፣ ተመራማሪ እና መምህር እንዲሁም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ክፍል ዳይሬክተር የነበሩት ዶ/ር አንዷለም ዳኘ ጠብቀው በተወለዱ በ37 አመታቸው በደረሰባቸው ድንገተኛ ሞት የተሰማንን መሪር ሃዘን እየገለፅን ለሟች ቤተሰቦች፣ ጓደኞች፣ የሥራ ባልደረቦች እና ለመላው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መፅናናትን እንመኛለን።
ዶ/ር አንዷለም በዩኒቨርሲቲያችን፣ ብሎም በአገራችን አሉን ከምንላቸው በቁጥር ትንሽ የዘርፉ ሰብ ስፔሻሊስት ሐኪሞቻችን ውስጥ አንዱ የነበሩ ሲሆን ከስራ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ በአጋጠማቸው ግድያ ህይወታቸውን አጥተዋል። በሐኪማችን ላይ ያጋጠመውን ግድያ እና በተደጋጋሚ በዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ያልተገባ መሰል ድርጊት ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በጥብቅ ያወግዛል። በየትኛውም አካል ሊሰነዘር የሚችል ይሄን አይነት መሰል ድርጊትም ለአገርም ሆነ ለወገን አጉዳይ እንጅ አንዳች የሚጨምር ነገር እንደሌለ ሁሉም ሊገነዘበው የሚገባ ጉዳይ ነው።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
01/07/2024
የአዕምሮ ጤና እና የኛ ህብረተሰብ
ህዝባችን (እኔን ጨምሮ) ለአእምሮ ህመም ያለው ግንዛቤ በጣም አናሳ ነው። አንዱ ተነስቶ በጫማ ጥፊ ሴጣንህን ዘረኩት ሲልህ "ና ወንድሜ ታከመው" ማለትህን ትተህ አሜን ትልለታልህ።
እኔ በዓሎችን በራሴ ነው ማከብረው ንግስትም ነኝ ስትልክ "እህቴ ነይ ታከሚው" ከማለት ይልቅ ትከተላታለህ ወይ ቀልደህ ታልፋታለህ።
የፍቅር አምላክ ሁለቴ የተለያየ ቦታ ይፈጥርሃል ሲልህ "ታከመው ወንድሜ" ማለትህን ትተህ ታላግጥበታለህ።
'ችግር' የሚለውን ቃል የፈጠሩት ፊደላት 6ኛ ፊደል ስለሆኑ 666 ነው ሲልህ ታከመው ማለትህን ትተህ "ቃለ ህይወት ያሰማልን" ትላለህ።
እና አንድ እህትህ "ህይወት መሮኛል፣ መኖር ደክሞኛል፣ ደብሮኛል" ስትልህ... አይዞሽ ባክሽ ሁሉም እንደዛው ነው ብለህ ታልፋለህ እንጂ ነይ እስኪ ታይው ታከሚው አትልም። ስለምታውቀው ስለማታውቀው ገጠመኞችህ ዘባርቀህላት፣ "አይዞሽ ፈታ ማለት ነው" ብለህ ታልፋለህ።
ትኩሳት ብታይበት፣ ደም ቢፈሰው፣ እራሱን ቢስት እኮ ይዘህ ወደ ሆስፒታል ትሮጣለህ። የአዕምሮ ህመምን እና ምልክቶቹን ግን የሂወት አጋጣሚ አርጋ እንድትቆጥረው አርገህ ታልፋታለህ ወይም "ሴት ወዶ ኮ ነው እንዲህ የሆነው" ወይንም "አስደግመውባት ኮ ነው እንዲ ምታረገው" ብለህ ከንፈርህን ትመጣለህ እንጂ ታከሚው እናሳክማት አትልም።
በዚህም ምክንያት ለሚመጡ መዘሶችም ሁሉ በማወቅም ባለማወቅም፣ በቸልተኝነትም ባለመገንዘብም ተጠያቂ አንተ እራስህ፣ እኔ እራሴ፣ እኛ ሁላችንም ነን።
ለአዕምሮ ህመም ክብደት እንስጠው፣ ግንዛቤ ይኑረን፣ አደገኛ እንደሆኑ እንገንዘብ! በጓደኞቻችን፣ በቤተሰብ አባሎቻችን የምናየውን የባህሪ ለውጦችን እንደቀላል ነገር ችላ አንበል። እንታከም! እናሳክም! ስቃያቸውን እናስታግስላቸው!
ያለ አዕምሮ ጤና ጤና የለም!
ስለአዕምሮ ህመም ጥልቅ ግንዛቤን ለማግኘት በባለሙያዎች የሚተላለፉልንን እንደ ' Mental wellness የአእምሮ ጤና ' የመሳሰሉ ገፆች እንከታተል!
ዶ/ር መላኩ አባይ የስነ ደዌ ስፔሻሊስት
01/07/2024
Wiixataa hanga Sanbata xiqqaa!
Magaalaa Jimmaa
Hoteela Boonii Cinaa!
01/07/2024
የመጀመሪያው ኢትዮጲያዊ የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ፍቅሬ ወርቅነህ
01/07/2024
በህጻናት ላይ ምልክቶች ምንድን ናቸው?
1.በጎን እና በጎን ያለ ህመም (flank pain)
2.የሽንት ከለር ቀይ መሆን
3.የሽንት መጠን መቀነስ ወይም አለመኖር
4.የሰውነት ማበጥ __በተለይ ከፊት የጀመረ እብጠት
5.በጎን በኩል የሚዳሰስ እብጠት( flank mass)
6.የደም ግፊት መጨመር
እኒህን የመስሉ የህመም ምልክቶች ሲያዩ የህጻናት ሀኪም ያማክሩ
የቴሌግራም ቻናላችንን በዚህ https://t.me/+vG_CAkvv7mQ0NWZk ያገኛሉ
11/06/2024
ሰላም ፤ ዛሬ በተለምዶ ጭርት (Tinea corporis) ስለሚባለው በሽታ ይዤላቹ ቀርቢያለሁ
ጭርት ምንድን ነው?
- ጭርት (tinea corporis) የምንለው በፈንገስ አማካኝነት የሚመጣ፣ በሁሉም የእድሜ ክልል የሚከሰት ሲሆን ከሰው ወደ ሰው፣ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ፣ በንክኪ የሚተላለፍ የላይኛውን የቆዳ ክፍል የሚያጠቃ በሽታ ነው።
ከየት ሊይዘን ይችላል?
-በበሽታው ከተያዙ ሰዎች፣ከተለያዩ የቤት እና የዱር እንስሳቶች፣ ከአፈር ሊሆን ይችላል። በተለይ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በበሽታው የተጠቀመበትን እንደ ፎጣ፣ አልጋ ልብስ፣ ካልሲ፣ የፀጉር ማበጠሪያ በጋራ መጠቀም እና ንክኪ መፍጠር ዋነኛ መተላለፊያ መንገዶች ናቸው።
አጋላጭ ምክንያቶቹስ ምንድን ናቸው?
-ሞቃታማ እና እርጥበታማ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎች፣ ሰውነትን የሚያጣብቁ ልብሶችን መልበስ፣ ደካማ የበሽታ የመከላከል አቅም ያላቸው ሰዎች፣ የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች፣ ከመጠን በላይ ላብ የሚያልባቸው ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ።
ምልክቶቹስ?
-አንድ ሰው ተጋላጭ ከሆነ በዃላ ከ4-14 ቀን ምልክት ሊያሳይ ይችላል። በሰውነት ላይ ክብ ክብ የሆነ ፣ ጠርዝ ጠርዙ ቀላ ያለ (erythematous)፣ የማሳከክ ስሜት ሊኖረው የሚችል እየሰፋ የሚሄድ እንደ ቅርፊት (scaly)፣ የተሰነጠቀ (cracked) የሚመሰስል ነገር ሊወጣ ይችላል።
ምርመራዎቹስ
-የህክምና ባለሙያው በቆዳ ላይ የወጣውን ነገር አይቶ እንደ አስፈላጊነቱ ከቆዳ ላይ ናሙና በመውሰድ በቤተ ሙከራ በmicroscope በመታገዝ ፈንገስ መኖር አለመኖሩን ሊያረጋግጥ ይችላል።
የሚያመጣውስ መዘዝ?
-በተለይ ደካማ ዠበሽታ የመከላከል አቅም ያላቸው ሰዎች ለምሳሌ (HIV ህመምተኞች፣ የካንሰር ህክምና የሚወስዱ) በቶሎ በሽታውን ለማስወገድ ሊቸገሩ ይችላል።
-የሚያሳክክ፣ የተቆጣ እና የቆዳ መሰንጠቅ ሲኖር ለሌላ ባክቴሪያ ኢንፌክሽን (secondary bacterial infection) ሊጋለጡ ይችላሉ።
አእዴት መከላከል እንችላለን?
-የግል እና የአካባቢ ንፅህናን መጠበቅ
-ሰውነታችነንን ከታጠብን በዃላ በንፁህ ፎጣ ወይም ጨርቅ በደንብ ማድረቅ
-የግል መጠቀም ያልብንን ነገሮች በጋራ አለመጠቀም
-በተቻለ መጠን በዚህ በሽታ ከተበከሉ እንስሳት ንክኪ አለመፍጠር፣ በአካባቢያችን የታመሙም እንስሳት ካሉ የእንስሳት ሀኪም ጋር በመውሰድ ማሳከም ተገቢ ነው።
ህክምናውስ?
-እነደ ወጣበት ቦታ እና ስፋት የሚወሰን ሲሆን በቦታው ላይ የሚቀባ ፀረ ፈንገስ ወይም የሚዋጥ ፀረ ፈንገስ በሀኪም ሊታዘዝ ይችላል።
ለወገንዎ ያጋሩ ፤ ጤና ይብዛላቹ
ዶ/ር ኤርሚያስ ማሞ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa