CSA_official
በ2012ዓ.ም ቆጠራዉ ይካሄድ ይሆን?
ምርጫዉስ በ 2012 ዓ.ም ይካሄድ ይሆን??
በ2011 ዓ.ም ቆጠራዉ ተካሂዶ ቢሆን ኖሮ እዉነት እንደተባለዉ መቁጠር አስቸጋሪ ይሆን ነበር?
5 የማይሞሉ ፖለቲከኞች ሥለተንጨጩ ቆጠራዉን ማስቀረት ተገቢ ነዉ?
የኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፖለቲከኞች እንደሚያወሩት ሥራ አዋኪ/አስቸጋሪ/ አይደለም፣ከኛ ከማ.ስ.ኤ./CSA/ ሰራተኞች የበለጠ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሚያዉቀዉ ማንም የለም ፣ጠ/ምንስቴሩን ጨምሮ፡፡ኢትዮጵያ ዉስጥ ሰላም የደፈረሰዉ በ2011 ዓ.ም ብቻ ነዉ? በ2008 ዓ.ም በዛ በግርግር ዲ.ኤች.ኤስ./DHS? አልሰራንም? ምንም እንኳን ሳምፕል/sample/ ቢሆንም የስልጠናዉን ጊዜ ጨምሮ ከ6 ወር በላይ በመስክ ስራ ቆይተናል፡፡ታዲያ የዲ.ኤች.ኤስ./DHS/ መረጃ ለምን የተዛባ አልነበረም? ማ.ስ.ኤ./CSA ቆጠራዉን በሃላፊነት ተቀብሎ ቢሰራም ዋናዉ ሞተር ግን በም/ጠቅላይሚኒስቴር የሚመራ እና የፓርላማ ዉሳኔ ይጠበቅ ነበር፡፡ለዛ ነዉ ቆጠራዉ የቀረዉ እኛ ወሳኝ ብንሆን ኖሮማ እንዴት አድርገን መስራት እንደምንችን እናሳያቸዉ ነበር፡፡
በማ.ስ.ኤ. ሰራተኞች ሁሌም እተማመናለሁ/እኮራለሁ !!
ዓሳ መዋኘት በሚያስጠላዉ ዉሃ ዉስጥ ገብተዉ ይሰራሉ
ዝንጀሮ በማይደፍረዉ ገደል ሮጠዉ ይሰራሉ
ቀበሮ በሚፈራበት ጉግጓግ ዉስጥ ተኝተዉ ሲነጋ ወደ ስራ ይሮጠሉ
.
.
.
ሁላቹሁም ጀግና ናቹ በርቱልኝ !!
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
ADDIS ABABA, ADDIS ABABA
Addis Ababa
1143
08/09/2019