Living Light - ሕያው ብርሃን

Living Light - ሕያው ብርሃን

Share

01/07/2026

💫RHAPSODY OF REALITIES 💫
(Amharic) 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

Wednesday 01, July 2026
ረቡዕ፥ ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም.

📜 ሊሄዱበት በሚገባው መንገድ ምሩአቸው
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

📖 “ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም” (ምሳሌ 22፥6) ።

👤 ፓስተር ክሪስ
════════
ስለ ልጆች አስተዳደግ ከቃሉ የተሰጠ ግልጽ መመሪያ አለ፤ ይህ መመሪያ ደግሞ በግል አስተያየት ወይም በዘመናዊ የማሳደግ ባህል ላይ የተመሠረተ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ "ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው" አለ እንጂ በሚመርጠው መንገድ፣ ማኅበረሰቡ በሚፈልገው መንገድ ወይም እናንተ ራሳችሁ በምትፈልጉት መንገድ ምሯቸው አይልም ነገር ግን ሊሄዱበት በሚገባ መንገድ ምራው። ያ መንገድ ደግሞ በእግዚአብሔር ቃል የተወሰነ ነው።

በዚህ ዘመን አንዳንዶች ልጆቻቸውን ለማሳደግ የተሳሳተ አስተሳሰብ ይዘዋል "እኛ ቤት ሁሉም ሰው የሚፈልገውን ማመን ወይም እግዚአብሔርን በፈለገው መንገድ ለማገልገል መብት አለው" ይላሉ። ይህ የክርስቲያን ቤት አይደልም። ክርስትና የእምነት ዲሞክራሲ አይደለም። የክርስቲያን ቤት ለመስራት ከፈለጋችሁ፣ መመዘኛ አለው፤ ያም መመዘኛ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ "እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት" (ሮሜ 1:28) ብሎ ስለ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ይናገራል። ይህ ሁኔታ በድንገት ሲያድጉ የሚጀምር አይደለም፤ ብዙውን ጊዜ ይህ በልጅነት ዕድሜ ላይ ተገቢው ሥልጠናና መዋቅር ካለመኖሩ የመጣ ነው። ልጆች እግዚአብሔርን ለማገልገል ትክክለኛ መንገድ ካልተማሩ፣ ስለ እግዚአብሔር ያለ ንቃተ ህሊና ሳይኖራቸው ያድጋሉ፤ ይህ መሆኑ ደግሞ ከባድ መንፈሳዊ መዘዝን ሊያስከትል ይችላል።

መንፈሳዊ ሥነ ስርዓትን ከልጅ ጋር ለድርድር አታቀርቡም ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ ስንፍና በልጅ ልብ ውስጥ አለ፣ ተግሣጽ ግን ይህን ለማስወገድ ይረዳል ይላል፦ "ስንፍና በሕፃን ልብ ታስሮአል፤ የተግሣጽ በትር ግን ከእርሱ ያርቃታል።" (ምሳሌ 22፥15)። እንደ ክርስቲያን ወላጆች፣ ልጆቻችሁ ወደ ቤተክርስቲያን ላለመሄድ የሚያመጡትን ሀሳብ በፍጹም አትቀበሉ። ልጆችን በስሜታቸው የሚመሩ አድርጋችሁ አታሳድጉ፤ በእውነት ላይ እንዲመላለሱ አድርጓቸው።

በእግዚአብሔር መንገድ ላይ በቋሚነት፣ በጽናት እና በፍቅር ስትቆሙ፣ መለኮታዊውን መመሪያ እየታዘዛችሁ ነው እንጂ ጨካኝ እየሆናችሁ አይደለም። የዚህም ውጤት የተረጋገጠ ነው በሸመገሉ ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይሉም። ይሄ ስልጠና ምርጫቸውን በማስተካከል እና ሕይወታቸውን በመጠበቅ በውስጣቸው መንፈሳዊ አቅጣጫ ጠቋሚ ይሆናቸዋል።

እግዚአብሔርን የሚያውቁ፣ በመንገዱ የሚመላለሱ እና በእውነት መሠረት ላይ የሚኖሩ ልጆችን እንድታሳድጉ እንጂ፣ ዝም ብለው የሚያድጉ ልጆችን እንድታሳድጉ አልተጠራችሁም። ይህ ኃላፊነት መለኮታዊ ስለሆነ ትኩረት ልትሰጡት የሚገባ ነው።

🙏 ጸሎት
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ውድ አባት ሆይ፣ በሕይወቴ ውስጥ ስለ ሚሠራው ጸጋህና ጥበብህ አመሰግንሃለሁ። እውነትህን በቋሚነት፣ በፍቅርና በጽናት እየተገበርኩ በቃልህ ብርሃን ውስጥ እመላለሳለሁ። ቤቴ በቃልህ ላይ የተመሰረተ ነው፤ በእኔ ስር የሚተዳደሩትን በጽድቅ ኮትኩቼ እና ለአንተ መገኘት ንቃተ ህሊና ይዘው እንዲያድጉ አደርጋለው። በኢየሱስ ስም። አሜን።

📖 ለተጨማሪ ጥናት 📖
├─ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6:4 (አ.መ.ት)
├─2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 3:15 (አ.መ.ት)
├─ኦሪት ዘዳግም 6፥7 (አ.መ.ት)

━━━━//━━━

Want your place of worship to be the top-listed Place Of Worship in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Addis Ababa
1000