Kora

Kora

Share

Photos from Kora's post 09/01/2023

የፍቅር ስጦታ ከ ኮራ ትሪፕ። 🎄❤️

“የኮድ 3 ሜትር ታክሲ አሽከርካሪዎች እና ባለንብረቶች ማህበር፣ ከኮራ ትሪፕ በተገኘ ድጋፍ፣ በአሽከርካሪነት የስራ ዘርፍ ላይ ተሰማርተው ህይወታቸው ያለፉትን ቤተሰብ በበአል ስጦታ ጎበኘ”።

ጉብኚቱ የተደረገው የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የኮድ 3 ሜትር ታክሲ አሽከርካሪዎች እና ባለንብረቶች ማህበር ከኮራ ቴክኖሎጂ ጋር በጋራ ያዘጋጁት እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል።

የማህበሩ ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሄኖክ እንደገለጹት በከተማችን በማሽከርከር ሰራ ላይ ተሰማርተው ሳሉ በግፍ ለተገደሉ እና ንብረታቸው ለተወሰደባቸው እዲሁም ለማህበረሰቡ መልካም ተግባር ለፈፀሙ አሽከርካሪዎች የገና በአልን አስመልክቶ የአብሮነትና የፍቅር ስጦታ ኮራ ትሪፕ የተባለ የሜትር ትራንስፖርት ድርጅት ካደረገልን የበግ ፣ የድፎ፣ የዶሮ እና የእንቁላል ድጋፍ በተጨማሪ ከጎናችን በመሆን ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦቻቸው ላደረጉልን ድጋፍ በማህበራችን ስም ከፍ ያለ ምስጋና እያቀረብን በቀጣይም ድጋፍ ካደረገልን ድርጅት ጋር እዲሁም ከዘርፉ ጋር ተያያዥነት ካላቸው ሌሎች ድርጅቶች ጋር በማህበራችን ደንብ ና መመሪያ መሠረት አሽከርካሪውንና ባለንብረቱን መብት እና ጥቅም ባስከበረ እና ባስጠበቀ መልኩ ከአሽከርካሪውና ባለንብረቱ በሚያግባቡን ስራዎች ላይ በጋራ እንደምንሰራ በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሌላ በኩል፣ የኮራ ትሪፕ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ያሲን ዑመር በበኩላቸው እንደገለጹት” ኮራ ቴክኖሎጂ በአሽከርካሪነት የስራ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ አካላት የደስታና ሥራ ብቻ ሳይሆን የሀዘናቸውም ተካፋይ መሆኑን ለመግለጽ የታሰበ ዝግጅት እንደሆነና ድርጅቱ እንዲህ ያሉ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን መወጣት ከተቋቋመባቸውተልዕኮዎች መካከል አንዱ መሆኑን ገልፀዋል።

ኮራ በከተሞች የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ እስካሁን በሜትር ታክሲ አገልግሎት እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት ጨምሮ የማህበረሰቡን ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነት ከፍ የሚያደርግ አዳዲስ አማራጮችን ያካተተ ቴክኖሎጂያዊ መተግበርያ ይዞ የነጥላና ጥምር የሜትር ታክሲ አገልግሎት ለመስጠት በትልቅ ካቲታል ወደ ሥራ እየገባ ያለ ድርጅት ነው።

Want your business to be the top-listed Transport Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Culinary Team

Attire

Telephone

Address


Bole, Woreda 02
Addis Ababa