Tigst

Tigst

Share

04/04/2026

ራሷን መከላከል በማትችልበት ሁኔታ እና ባለቤቱ በሌለችበት ወቅት የገዛ ልጅን የግብረ ስጋ ድፈረት ወንጀል የፈፀመው አባት

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ቤንች ሸኮ፣ ሲዝ ከተማ በገዛ ልጁ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈጸመ ግለሰብ በ12 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣቱ ከክልሉ ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ጥር 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ነው።ተከሳሹ ዳንኤል ወልዴ የሚባል ሲሆን እድሜዋ 14 ዓመት የሆናትን የገዛ ልጁን...

ራሷን መከላከል በማትችልበት ሁኔታ እና ባለቤቱ በሌለችበት ወቅት ኃይል በመጠቀም የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል መፈጸሙ ተገልጿል።

ዓቃቤ ሕግ ከፖሊስ የተሰበሰቡ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን ለችሎቱ አቅርቧል። የሲዝ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተከሳሹ በቀረበበት የወንጀል ክስ ላይ መከላከል ባለመቻሉ ጥፋተኛ ብሎት በ12 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ይህን ፍጹም ኢሰብዓዊ፣ ኢሞራላዊ የአውሬና የጭካኔ ድርጊት በገዛ ልጁ ላይ የፈጸመውን ወንጀለኛ 12 ዓመት እስራት ብቻ ተፈርዶበታል።

የችሎቱ ዳኛ አማረ ገበየ " ፍርዱ ተከሳሹን የሚያርምና ለሌሎችም ትምህርት የሚሰጥ ውሳኔ " ብለውታል።

ከዚሁ መረጃ ጋር በተያያዘ ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ " የፍርድ ውሳኔው እውነት ማስተማሪያ ነው ? " የሚል ጥያቄና ቅሬታ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ተነስቷል።

በተለያዩ ጊዜ የሚተላለፉ ውሳኔዎች የወንጀሉን ክብደት መመዘን ሲሳናቸው የፍትህ ስርአቱ ላይ ጥያቄ ይነሳል።

የህፃናት ስነልቦና እና የወደፊት ህይወት ላይ የሚደርሰው ጥፋት በዓመታት እስራት ብቻ ሊለካ የማይችል በመሆኑ ቅጣቱ በደሉን ይመጥናል ወይ ? የሚለው በብዙዎች ዘንድ ቁጣን የቀላቀለ ጥያቄ ያስነሳል።

በህፃናት ላይ የሚፈጸሙ መሰል ጥቁር ጠባሳዎች በማህበረሰቡ ዘንድም የሚፈጥሩት ቁስል ጥልቅ ነው።

ግዮን ማለዳ በተከታታይ መሰል የሴቶች ጥቃቶች መረጃዎች የሚጋራው ድርጊት ትኩረት እንዲሰጠውኛ የህግ ማሻሻያ ተደርጎ አስተማሪ የሆነ ቅጣት እንዲሰጥበት ነው።

ህብረተሰቡ ህግን እንደ ጋሻ ማየት የሚፈልገው ወንጀለኞች በድርጊታቸው እንዲጸጸቱ ብቻ ሳይሆን ሌሎች መሰል ሀሳብ ያላቸው ግለሰቦች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የሚያደርግ " #አስፈሪ " ቅጣት ሲኖር ነው።

ለሚፈጸሙ ዘግናኝ ወንጀሎች የሚተላለፉ የቅጣት ውሳኔዎች ወንጀሉን የሚመጥኑ ካልሆነ ተጎጂዎችና ቤተሰቦቻቸው በህግ ጥላ ስር መጠለልን ትተው በዝምታ እንዲሰቃዩ ፤ በፍትህ ስርዓቱ ተስፋ እንዲቆርጡ በር ይከፍታል።

ፍትህ "ተሰጥቷል" ብቻ ሳይሆን " እንደተሰጠ የሚታወቀው" ውሳኔዎቹ የህዝቡን የሞራል ስብራት የሚጠግኑና የወንጀሉን ክፋት የሚመጥኑ ሆነው ሲገኙ ብቻ ነው።

እንደ ግዮኝ ማለዳ የቅጣት ማነስ የሴቶችን አስገድዶ መድፈር እያበባሰ ነው ብለን እናምናለን ! የሴቶች ጥቃት ይቁም !

እናንተ የፍርድቤቱ ቤቱ ውሳኔ አስተማሪ ኘው ብላችሁ ታስባላችሁ ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን እስኪ?

ግዮን ማለዳ

በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች ቴሌግራም ላይ ያገኛሉ👇

https://t.me/GhionMaleda

07/03/2026

#አልመጣም‼️ " ብሏል😭

#ይህ ህፃን ይባላል ዛሬ ጠዋት ትንሽ በእናቱ አኩርፎ አልመለስም እንዳትፈልጉኝ ብሎ ወጥቷል

#ቤተሰብ በጣም ተጨንቀዋል!!
እባካችሁን #ሼር በማድረግ ልጁን እንፈልገው



09 44 08 12 13

09 46 59 58 31

#ሰውን ለመርዳት ትክክለኛው ጊዜ #አሁን ነው

#ዮናስ ደምሴ ( የአይንዬ ልጅ )

Want your business to be the top-listed Business in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Merkto
Addis Ababa