Dymans-Eth

Dymans-Eth

Share

Photos from Dymans-Eth's post 23/06/2020

- በሲዳማ ክልል 7 ሰዎች በኮቪድ-19 ተይዘዋል፤ ሁሉም የውጭ ጉዞ ታሪክ የሌላቸውን በቫይረሱ ተያዘ ሰው ጋር ንክክ ያላቸው ናቸው። መኖሪያቸው 1 ሰው ከብላቴ ማዞሪያ፣ 2 ሰዎች ከቦና፣ 1 ሰው ከሸበዲኖ፣ 1 ሰው ከዳሌ፣ 1 ሰው ለዳራራ ፣ 1 ሰው ከአርቤጎና ነው።

- በኦሮሚያ ክልል 7 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። 5 ሰዎች ከሰበታ ፣ 1 ሰው ከሰንዳፋና 1 ሰው ከጉጂ ናቸው። ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ ከአንድ ሰው በቀር ሁሉም ንክኪ ያላቸው ናቸው።

- በትግራይ ክልል 1 ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው።

- በአማራ ክልል ሁለት ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ሁለቱም ከባህር ዳር ናቸው ፤ ሁለቱም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም።

- በአፋር ክልል 86 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በክልል በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 72 ደረሰዋል።

- በጋምቤላ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል፤ አጠቃላይ በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 12 ደርሰዋል።

- በሐረሪ ክልል 1 ሰው በቫይረሱ ተይዟል፤ግለሰቡ የሱማሌ ክልል ነዋሪ ሲሆን ለህክምና ሐረር መጥቶ ናሙና የተወሰደለት ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ከላይ ባሉት ምስሎች ታገኛላችሁ!

Photos 23/06/2020

ዱባይ!

ዱባይ በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት ዘግታ የቆየችውን ከሀገር የመውጣት ዕገዳ ከዛሬ ጀምሮ ዜጎቿ ወደ ተለያዩ ሀገራት መጓዝ እንደሚችሉ በመፍቀድ አንስተዋለች።

ከዚህ በተጨማሪም በውጭ የሚኖሩና ወደ ዱባይ መግባት ለሚችሉ ሰዎች ከሐምሌ ሰባት ጀምሮ ወደ ዱባይ መግባት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ዱባይን ለመጎብኘት የሚመጡ የውጭ ዜጎች በቅርቡ ከኮሮና ቫይረስ ተመርምረው ነፃ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉና በዱባይ አየር መንገድ ውስጥ እንደገና ለመመርመር ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

11/04/2020

በአሜሪካ ኒውዮርክ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል ሃኪም ፣ የሕብረተሰብ ጤና ባለሞያ፣ በኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስተር አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ጽዮን ፍሬው በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ይህን ብለዋል ፦

"ኢትዮጵያ እዚ በቺካጎ ከተፈጠረው እንማር። አንድ በሽታው እንዳላበት ያለወቀ ሰው ለቅሶ እና ከዛም ልደት ግብዣ በመሄዱ16 ሰው ታሞ 3 ሰው ሞቷል። እባካችሁ ግብዣው እና ድግሱን ለሌላ ቀን እናርገው። አለበዚያ ለቅሶው ይበዛል።"

https://www.washingtonpost.com/health/2020/04/08/funeral-birthday-party-hugs-covid-19/

fb.me/dymansethiopia

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa