ሸዋ Hub

ሸዋ Hub

Share

17/03/2026

የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ምክትል አዛዥ፣ የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ ወታደራዊ አዛዥ ኮ/ል ማነገረዉ መለስ መዘዞ ከተማ እጁን ለመንግሥት የፀጥታ ሃይሎች ሰጥቷል።

ግለሰቡ በቡድኑ ዉስጥ ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ የነበረ ቡድኑንም ከመሰረቱ ዋነኛዉ ሰዉ ነበር። በአሁኑ ሰዓት በጣርማ በር ወረዳ ጣርማ በር ዋሻዉ ላይ በሰራዊቱ እጅ ይገኛል።

Photos from Multi Ethnic Shoa's post 08/03/2026

#‎አንኮበር

‎ኢትዮጵያ ሀገሬ ሀገረ እግዚአብሔር ፣
‎የማርያም አስራት የነገስታት ሀገር ፣
‎ታሪክሽ ቢወሳ ዝናሽም ቢነገር፣
‎አያልቅም ተጠቅሶ በሰው ልጅ ከናፍር።
‎አባይን በጭልፍ ቢሆንም ታሪክሽ፣
‎ከብዙ አካላትሽ ከብዙ ታሪክሽ፣
‎የነገስታቱን ምድር አንኮበርን ላንሳልሽ።
‎በአብርሃ እና አፅብሃ የተመሰረተች ፣
‎በአፄ ይኩኖአምላክ የተመሰረተች፣
‎የነገስታት ቦታ የታሪክ ጮራ ነች ።
‎እነ መርድ አዝማች እነ አምሀኢየሱስ፣
‎አፅማቸው ያረፈው አንኮበር ጊዮርጊስ ፣
‎ሣህለ ሥላሴ ኢትዮጵያን የገዛው ፣
‎አንኮበር ሚካኤልን በክብር የሳነፀው፣
‎የወለሉን አፈር ከእስራኤል ያስመጣው፣
‎አፅመም በዚያው ቦታ በክብር የሚገኘው ፣
‎ያየጥቁር ንጉሥ እምዬ ምኒልክ ፣
‎የጥቁር ነፃነት የስልጣኔ ልክ፣
‎ጎንደር ውስጥ ያደገው የኢትዮጵያው መሪ ፣
‎ስሙ እንኳን ሲጠራ የሚያሰኘው እሪ፣
‎ያሰው ምኒልክ ነው አንኮበር መስክሪ ።
‎ምን ብዬ ልግለፃት እምዬ አንኮበርን፣
‎ለአንቺማ ፈጣሪ አላዳላም ይሆን?
‎እውነት አምላክ ለአንቺ አላደላም ይሆን ?
‎እንቁ መስህቦችን በብብትሽ የያዝሽ፣
‎ጥቂቱን ልመስክር ጥቂቱን ላንሳልሽ።
‎አንኮበር ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣
‎ሣህለ ሥላሴ ያሳነፀውን፣
‎ገብስ እህል ከሰማይ ያወረደውን፣
‎ምሰሶው እስከ አሁን ደዌ ፈዋሹን፣
‎ሀዋርያዊ መስቀል ምስል የጻድቃን፣
‎ታሪክ የታየበት ጷግሜ ሶስት ቀን።
‎እጅግ ያስደንቃል አንኮበር ውበትሽ፣
‎ብርኩሚት ማርያምን በብብትሽ ይዘሽ፣
‎ተዓምርሽ ብዙ ነው ብርኩሚት ማርያም፣
‎ከጎንሽ አለና መዳኛ ለአለም፣
‎በእቅፍሽ አለና መድሀኔ አለም።
‎አስቲት ላይ ያለችው ኪዳነ ምህረት፣
‎በክብር የሞላት ሰባት መቶ አመት።
‎ቸነፈር ሲበዛ ረሀብ ሲከሰት፣
‎በአምሀ ኢየሱስ ዘመነ መንግስት፣
‎ስንዴ ከሰማይ ላይ የወረደባት፣
‎የመስጫ ማርያምን ምን ብዬ ልርሳት።
‎የዋሻው ገብርኤል ጎርጎ የሚገኘው፣
‎በአምሀ ኢየሱስ የተቦረቦረው።
‎ህዝቅኤል የሰራው ቦታው የሰላም፣
‎ሚጣቅ ተክለ ሀይማኖት አንድነት ገዳም፣
‎የአበዉ ቅዱሳን የጠበል መገኛ፣
‎እውራንን አብሪ የድውይ መዳኛ።
‎የመነኩሴ ዋሻ እመ ምህረት ያለው፣
‎መናኝ ጸሎተኛን አቅፎ የሚይዘው፣
‎ስንቱን ልዘርዝረው ታሪክሽ ብዙ ነወ።
‎እነ ሊቅ ማረፊያ መሀል ወንዝ ያለው፣
‎የተማሩ ሰዎች መቀመጫቸው፣
‎እምዬ ምኒልክ የመሰረተው፣
‎ሀኪሙ ዶክተሩ ጂኦግራፈሩ፣
‎ዋና መቀመጫው እዚያ ነው ሰፈሩ።
‎የጋጀሎ ቦታ ያ የመሀል ወንዙ፣
‎የባሩድ ማንጠሪያ ጥይት ለአፈሙዙ።
‎እምዬ አልዬ አምባ የጉምሩክ ከተማ፣
‎አማራን ከአርጎባ በአንድ የምታስማማ፣
‎ደምቃ የምትታይ በታሪኳ ማማ።
‎የአልዬ መኖሪያ ነጋዴው ሲራራ፣
‎ጥንታዊ መስጊዱ ከሩቅ የሚያበራ።
‎ወፍ ዋሻ ጥቅጥቁ የተፈጥሮው ደን፣
‎በእቅፉ የያዘው እንቁ ሶረኔን።
‎በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ ቦታ ያለሽ፣
‎እጅግ ያስደንቃል አንኮበር ውበትሽ።
‎በዙሪያሽ የያዝሽ እንቁ መስህቦችን፣
‎እውነት አምላክ ለአንቺ አላደላም ይሆን?
‎የታሪክ ባለቤት የነገሥታት ምድር፣
‎ሰዓታት አይበቁም ታሪክሽ ቢነገር፣
‎ከኢትዮጵያ እንብርት ከሸዋዎች መንደር፣
‎አንኮበር አንኮበር አንኮበር አንኮበር ።

‎ገጣሚ፦ ዜና ሸዋበረ (ዜሾ)
‎ ቀን፦ 27/05/2014 ዓ.ም አንኮበር; ኢትዮጵያ

01/03/2026

አለምን ያንቀጠቀጡ ብቸኛ የምድሪቱ ክስተት አፄ ሚኒሊክ ናቸው 💪✅

25/02/2026

ይገርምሃል ሸዋ !

ዳግም አልወለደችም አንድ ነው ለእናቱ።

ሣህለ ማሪያም ፡ ኃይለ መለኮት ፡ ሣህለስላሴ ብርቱ ሠው ነው። ራሱን ሲጠራ አጤ ምኒልክ ንጉሠ ሸዋ (አጤ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘ ኢትዮጵያ ) ብሎ ነው።

በማንም ዘመን ፣ በየትኛውም ግዜ በቆዳ ቀለሙ ፣ በሚናገረው ቋንቋ ፣ በሚስቱ ዘመዶች ፣ በሌላም ሌላም የሠው ፍጡር በሆነ ሠይሞ አያውቅም ። ምናበ ሠፊ ፣ አርቆ ተመልካች ፣ ትኩስ ደግሞ ገር ነው ።

እኔ በእግዝሐር አምሳል የተፈጠርኩ ፣ የእግዝሃር ባሪያ ነኝ ማለት ወጉ ነው ።

ለፈረንጆች አዲስ አይደለም ። አብሯቸው ከታሠረበት ከመቅደላ ጀምሮ ያውቃቸዋል ። ከፈረንጅ በመዋል ስለቆዳ ቀለማቸው ፣ ስለሚናገሩት ቋንቋ ስለሌላም ሌላም ጠይቋቸው፣ ግድ ሠጥቶትም አያውቅም ። በእለት በእለት በደጃፉ ለሚረግጡ አውሮፓውያን የነበረው አንድ ጥያቄ ብቻ ነው ።

" ምን ሙያ አለህ ?" የምትል ብቻ ።

የመሠልጠን ጥም ፣ የዘመናዊነት ህልም ፣ የከፍታ ራእይ ብቻ ነው ያለው ።

በምኒልክ ቤት ሐፍረት አለመቻል ነው ። አለመስራት ። "ወስላታ" - ታሉ በቃ ነው ።

ከፊት ቀድመው ፣ ሀገርን ማስቀደም ፣ ህዝብን መምራት ፣ ያኮረፈውን አባብሎ ፣ የጠገበውን አስተንፍሶ ፣ አቻችሎ መኖር ያውቅበታል ። እሱ የሠተራት ትልቋ ኢትዮጵያ ፣ አይኗን ሳትገልጥ ከፊቷ የተደቀነውን ፈተና ፣ አደዋ ላይ የረታው በዚሁ ጥበቡ ነው ።

አጤ ምኒልክ በአደዋ ድል ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትን በደም አሻራ አተመ ። ይህ ዘልዓለማዊ ማህተም መቼም ላይፋቅ ፣ በሠማየ ሠማያት ፣ ከግሪክ አማልክት ከነዜውስ ፣ አንድሮሜዳ ጋር ፣ ምልክት ተቀምጦለታል ።

የአደዋ ድል - ጥቁር ነን በሚል ውዳቂ ተረት ነጮችን ለመመከት አልወጣም ፣ ከእከሌ ዘር ነኝ በሚል ሌላ ዘር ለመውጋት አልተሠለፈም ፣ በመከፋፈል የሚኖርን ሠው ወለድ ስርዓት ፣ በአንድ በሚያስር መለኮታዊ ዓላማ ስር አስተባብሮ ተዋጋ እንጂ።

ለኢትዮጵያዊ ማንነትህ
ለኢትዮጵያዊት ሚስትህ
ለኢትዮጵያ ምድር
ለኢትዮጵያዊቷ እናትህ
ኢትዮጵያዊ መንግስትህን ሊወጋ የመጣ ጠላት አለና ፣ የመኖርህን አስትናፋስ ፣ ልእለ ህላዌ ከፊት ቀድመህ አስመስክር አለ እንጂ።

መከፋፈልን በአንድነት ፣ ዘረኝነትን በሠብዓዊነት ፣ እብሪትን በጀግንነት ማሸነፍን ላስተማረን ሚኒልክ አባታችን ክብሩ ይስፋ ። ስሙ ዳግም ደግም በትውልዶች ሁሉ ይነሳ ። ከእሱ ጎን የቆሙ ፣ ከኢትዮጵያ ጎን የቆሙ ናቸውና ዳግም ይባረኩ ።

ኢትዮጵያዊነትን አፀና!
የእግዚአብሔር አምሳለ ፍጡርነትን አፀና!

***

#ዓድዋ130

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Website

Address


Addis Ababa
WWW.MULTIETHNICSHOA.COM