AGMAS MEDIA

AGMAS MEDIA

Share

01/03/2026

እስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ ጥቃት ከጀመሩ በኋላ፤ ሦስት የአሜሪካ ወታደሮች መገደላቸውን እና አምስት በጽኑ መጎዳታቸውን ፔንታጎን አስታወቀ። አሜሪካ ትላንት ቅዳሜ በተጀመረው ጦርነት ወታደሮቿ መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ይፋ ስታደርግ የመጀመሪያው ነው።
ፔንታጎን ተብሎ የሚታወቀው የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ወታደሮቹ የተገደሉት እና የተጎዱት “በዘመቻ ኤፒክ ፉሪ” በመሳተፍ ላይ ሳሉ እንደሆነ ዛሬ እሁድ ገልጿል። ሌሎች በርካታ ወታደሮች አነስተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ያስታወቀው የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ውጊያ እንደቀጠለ መሆኑን ገልጿል።
ይሁንና የአሜሪካ ወታደሮች የተገደሉበትን እና የተጎዱበትን ሁኔታ በዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥቧል። የኢራን አብዮታዊ ዘብ “ከፍተኛ” ጥቃት እንደሚፈጽም ያሳወቀ ሲሆን በሪያድ፣ ዱባይ፣ አቡ ዳቢ፣ ዶሐ፣ ማናማ እና እየሩሳሌም ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ከእስራኤል ጋር በጥምረት በምታካሒደው ድብደባ 48 የኢራን አመራሮች መገደላቸውን አስታውቀዋል። “እያገኘን ያለውን ስኬት ማንም ማመን አይችልም” ሲሉ ትራምፕ ፎክስ የተባለው የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

https://www.reuters.com/world/us/trump-says-48-leaders-killed-strikes-iran-fox-news-interview-2026-03-01/
via

ዘጋቢ - #ንጉሤ የኔአባት

Pope Francis, groundbreaking Jesuit pontiff, dies aged 88 21/04/2025

#ሰበር ዜና
ፖፕ ፍራንሲስ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።
**********
(አግማስ ሚዲያ)
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል፡፡

ሊቀ ጳጳሱ ባደረባቸው ከፍተኛ የሳንባ ሕመም የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው በዛሬው ዕለት በመኖሪያ ቤታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ቫቲካን አስታውቃለች፡፡

"Pope Francis, groundbreaking Jesuit pontiff, dies aged 88 | Pope Francis | The Guardian" https://www.theguardian.com/world/2025/apr/21/pope-francis-dies
ምንጭ፦ ዘጋርድያን

#በንጉሤ የኔአባት

Pope Francis, groundbreaking Jesuit pontiff, dies aged 88 Death of 267th head of Catholic church triggers period of global mourning and Vatican conclave of cardinals to elect successor

Chinese robots ran against humans in the world’s first humanoid half-marathon. They lost by a mile | CNN 19/04/2025

#ቻይና ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው እና ሮቦትን በግማሽ ማራቶን አወዳደረች።

(አግማስ ሚዲያ)

በቤጂንግ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን የሩጫ ውድድር ላይ 21 ሮቦቶች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሳትፈዋል።

ቲያንግ አልትራ የተሰኘው ሮቦት በ2 ሰዓት ከ40 ደቂቃ በማጠናቀቅ የውድድሩ አሸናፊ ሆኗል።

ሮቦቱን የሰራው የቤጂንግ ፈጠራ ማዕከል ሀላፊ ታንግ ጂያንግ ሮቦቶቹ ሰዎችን አይተው በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲሮጡ የሚያስችል እግር እንደተሰራላቸው ገልፀዋል።

አሸናፊው ሮቦት ውድድሩን እስኪያጠናቅቅ ድረስ ሶስት ጊዜ ባትሪ ተቀይሮለታል።

"ይህ ብዙ ባያኩራራኝም እስከ አሁን ግን በምዕራቡ ዓለም ያልተጀመረ ቴክኖሎጂ ነው" ብለዋል ሀላፊው።

ከሮቦቶቹ ጋር ከተወዳደሩ ወንድ ተወዳዳሪዎች መካከል አሸናፊው ውድድሩን አንድ ሰዓት ከ2 ደቂቃ ውስጥ ማጠናቀቁን ሲኤንኤን ዘግቧል።
https://amp.cnn.com/cnn/2025/04/19/asia/china-first-humanoid-robot-half-marathon-intl-hnk

#ንጉሤ የኔአባት አማረ
መልካም በዓል!

Chinese robots ran against humans in the world’s first humanoid half-marathon. They lost by a mile | CNN More than 20 two-legged robots competed in the world’s first humanoid half-marathon in China on Saturday, and – though technologically impressive – they were far from outrunning their human masters over the long distance.

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Asmara Road
Addis Ababa
1000