Addis Zena
27/05/2026
በኢራን እና በአሜሪካ መካከል አዲስ ጦርነት የመቀስቀሱ እድል ጠባብ መሆኑን የኢራን አብዮታዊ ዘብ የባህር ኃይል ባለስልጣን መሐመድ አክባርዛዴህ አስታወቁ።
ይሁን እንጂ የኢራን የጦር ኃይሎች ዝግጁ ሆነው እንደሚጠብቁ አስጠንቅቀዋል።
ማንኛውም ጥቃት የሚሰነዝር ወራሪ ኃይል ካለ የኢራን የባህር ዳርቻ የጠላቶች መቃብር እንደሚሆንም ገልጸዋል።
ይህ መግለጫ የወጣው በኢራን ተፅዕኖ ፈጣሪ በሆነው ታስኒም የዜና ወኪል ነው።
አሜሪካ በቅርቡ በክልሉ የሰነዘረችውን የአየር ጥቃት ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል ከፍተኛ ውጥረት ሰፍኖ ይገኛል።
አሜሪካ የታገደው የሆርሙዝ የባህር በር እንዲከፈት እየጠየቀች ሲሆን ኢራን ደግሞ እገዳውን እንደ ጦርነት ድርጊት ትቆጥራለች።
አሁን ላይ ሁለቱም ወገኖች በሽምግልና ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገልጿል።
Addis Zena
26/05/2026
የአሜሪካ ጦር በትናንትናው ዕለት በደቡባዊ ኢራን ላይ የመከላከያ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የማዕከላዊ ዕዝ (CENTCOM) አስታወቀ።
ቃል አቀባዩ ካፒቴን ቲም ሃውኪንስ እንደገለጹት፥ ጥቃቱ የተሰነዘረው በሆርሙዝ ወሽመጥ አቅራቢያ በሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ የተደቀነን የደህንነት ስጋት ለመቀልበስ ነው።
በባንዳር አባስ የወደብ ከተማ አቅራቢያ በተካሄደው በዚህ እርምጃ፥ ባህር ላይ ፈንጂዎችን ለመቅበር ሲሞክሩ የነበሩ ሁለት የኢራን የጦር ጀልባዎች ሰምጠዋል።
እንዲሁም ሮኬት የተኮሱ ሚሳኤል ማስወንጨፊያ ጣቢያዎች መውደማቸው ተገልጿል።
ይህ ወታደራዊ ግጭት የተከሰተው ሁለቱ ሀገራት በኳታር የሰላም ድርድር እያደረጉ ባሉበት ወቅት ነው።
አሜሪካ በድርድሩ ምክንያት ራሷን እየገታች እንደሆነ ብትገልጽም፥ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን የሰላም ንግግሩ አሁንም በጥሩ ሁኔታ እየቀጠለ መሆኑን ገልጸዋል።
Addis Zena
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Togo Avenue
Addis Ababa
1000