Teawun
16/06/2020
Muhamedanwar Seid:
*ሰበር ዜና ከተዓውን መረዳጃ*
09/10/12
*በዛሬው እለት 12 ካርቶን ኪታብና ቁርአን ወደ ወሎ ቦረና ገጠር አካባቢ ሊሰራጭ ተላከ👏🌹*
ይህም ማለት 1000 ቃኢዳ ኑራንያ 800 ቃኢደቱ—ልበግዳድያ እና፣ 700 ባለ 3 ጁዝእ ቁርአን በድምሩ 2500 የልጆች መማሪያ ቁርአኖች፤ እንድሁም 350 ባለ 30 ጁዝእ ቁርአኖች 100 የኢማሞች የኹጥባ ኪታቦች፣ 100 የደረሶች የቂርአት ስነ ምግባር መማሪያ ኪታብ(ተእሊመልመተአሊም) እና ወደ 30 የሚሆኑ ቅዱስቁርአን የቁርአን ተፍሲሮች ወደ ወሎ ቦረና ለገጠር መሳጂዶች ተልኳል።
✍✍👏👏✅✅
ይህም ከአባላት በተዋጣ ከ97 ሽህ ብር በላይ ወጭ የተገዛ ሲሆን ግምቱ 34 ሺህ ብር በስጦታ የተበረከተልን መሆኑ ታውቋል።
በዚህ ሰፊ የቁርአን ስርጭት በቦረናና በዙሪያዋ የሚገኙ መሳጂዶችን ተደራሽ ለመሆን ጥረት እንደሚደረግ ይታመናል።
በዚህ ማህበረሰብን በኢስላማዊ እውቀት በማነፅ ወደ ተሻለ የስነ ምግባር ልእልና የማሻገር የተቀደሰ ተግባር የተረባረባችሁ ምግባረ ሰናይ ወገኖች ሁሉ በአላህ ስም ከልብ እናመሰግናለን። ሀያሉ አላህም ምንዳችሁን ይከፍልልን ዘንድ እንለምነዋለን ።
በቀጣይም በመሰል ስራ ና ሁሉን አቀፍ በሆኑ በጎ ተግባሮች ለመሰለፍ ተግተን እንደምንሰራ ማረጋገጥ እወዳለሁ።
በዚህና በመሳሰሉ የበጎ ተግባር ስራዎች በመሳተፍ አስተዋፅኦ ማበርከት ለምትሹ ወገኖች በራች ክፍት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ +251911985768/0913066868
የተዐውን ኮሚቴ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Telephone
Website
Address
Addis Ababa