Zebra Communications
11/02/2026
የመዝናኛ ሚዲያው ስኬታማ ፋና ወጊ አርፏል😭😭
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን አባት። የጀርባው ምሰሶ። ቅን፣ ተባባሪ፣ ዘመናዊ ሰው። ተቋም ሰርቶ አለፈ። አማን ለቴሌቪዥን ተመልካቾች የቤተሰብ ጉዳይ፣ ማኅበራዊ ጉዳይ፣ መተዛዘን-መደጋገፍ በፈጠራ እየተከሸነ ትውልድ እንዲሰራበት የራሱን ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቶ አለፈ።
ኢቢኤስ ቴሌቪዥንን በመመስረት፣ በመምራት የቤተሰብ እና የመዝናኛ ቴሌቪዥን ሰጥቶን አለፈ። የማይታወቅ ግን የማይዘነጋ ሰው ነዉ- አማን። ነፍስህን በአፀደ ገነት ያኑርልን። ለወዳጅ ዘመዶችህ ሁሉ መጽናናትን ይስጥልን።
04/02/2026
"ክልሉን በሚመጥን መልኩ በ 6ቱም ማዕከላት የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ በትኩረት ይሰራል"- ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
"የክልሉ መንግስት የክልሉን ሕዝቦች ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና አብሮ የመልማት ትልም ዕውን ለማድረግ ባለፉት ሁለት ዓመታት በበርካታ ዉጤቶች የታጀበ ጉዞ በማድረግ ላይ ይገኛል።
በክልላችን በየማዕከላቱ ታቅደው ተገቢውን ሂደት በማለፍ በግንባታ ላይ የሚገኙት የተቋማት ህንፃ ግንባታዎች፤ በጠንካራ የተቋማት ግንባታ የሕብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ለጀመርናቸዉ ስራዎች አበርክቷቸዉ የጎላ ነዉ።
ፕሮጀክቶቹ የክልሉን የአስፈጻሚ ተቋማት ተቋማዊ አቅም በማጠናከር፤ ለክልላዊ የልማትና የብልጽግና ራዕይ ስኬት የላቀ ሚና የሚጫወቱ በመሆኑ በጥራትና በፍጥነት ከተያዘላቸው ጊዜ ቀድመዉ እንዲጠናቀቁ በልዩ ትኩረት የሚከታተላቸው ይሆናል።"
Click here to claim your Sponsored Listing.
Website
Address
Bole
Addis Ababa