KASu//TV

KASu//TV

Share

Photos from KASu//TV's post 15/04/2023

👉👉ዶ/ር ታዘባቸው "ትምህርቱን ከአራተኛ ዓመት እንዲቀጥል" ተወስኖለታል፡፡

ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በህክምና የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው ዶ/ር ታዘባቸው ውዴ፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በማህፀንና ፅንስ ሬዚደንትነት ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቷል፡፡

ዶ/ር ታዘባቸው ስፔሻላይዜሽን ትምህርቱን ለማጠናቀቅ ሁለት ወራት ሲቀረው በአንደኛው አይኑ ላይ ባለበት መንሸዋረር ምክንያት ትምህርቱን እንዲያቆም መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡ ወደሌላ የትምህርት ክፍል ተዘዋውሮ ከአንደኛ ዓመት እንዲጀምር መወሰኑም አይዘነጋም፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ እና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት የባለሙያዎች ቡድን በማቋቋም የዶ/ር ታዘባቸውን ቅሬታ ሲመረምር ቆይቷል፡፡

የባለሙያዎች ቡድን የቀረቡለትን መረጃና ማስረጃዎች ከመረመሩና እንደገና የማጣራት ሥራ ካከናወኑ በኋላ ዶ/ር ታዘባቸው ወደ ትምህርቱ እንዲመለስ የውሳኔ ምክረ ሃሳባቸውን ለዩኒቨርሲቲው ቦርድ አቅርበዋል።

የዩኒቨርስቲው ቦርድም የባለሙያዎቹን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ዶ/ር ታዘባቸው ትምህርቱን ከአራተኛ ዓመት እንዲቀጥል ወስኗል፡፡

ዶ/ር ታዘባቸው ትምህርቱን አቋርጦ በቆየበት ወቅት ድጋፍ ላደረጉለትና ውሳኔውን በመቃወም ለተሟገቱለት አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

12/04/2023

ቴሌግራም 👉 https://t.me/Merejanews

ከኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በ“ከባድ የሙስና ወንጀል” ከተከሰሱት ግለሰቦች ውስጥ አምስቱ በፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ!

ከአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በ“ከባድ የሙስና ወንጀል” ክስ ከተመሰረተባቸው ግለሰቦች ውስጥ የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱን ጨምሮ፤ አምስት ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ ተባሉ።

በዚሁ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንድ ተከሳሽ በሌሉበት ጥፋተኛ ሲባሉ፤ ቀሪ አምስት ተከሳሾች ደግሞ የተከሰሱበት ድንጋጌ ተቀይሮ እንዲከላከሉ በፍርድ ቤቱ በይኗል።

ይህን ብይን የሰጠው ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 4/2015 የዋለው፤ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ችሎት ነው።ችሎቱ አምስት ተከሳሾችን በነጻ ያሰናበተው፤ “ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ፤ ወንጀሉን በበቂ ሁኔታ ባለማስረዳቱ” መሆኑን ገልጿል።

በነጻ ከተሰናበቱት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አብርሃም ሰርሞሎ እና የከተማይቱ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ቢሮ የአይሲቲ ዳይሬክቶሬይትን ሲመሩ የነበሩት ኩምሳ ቶላ እንደሚገኙበት ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

11/04/2023

መምህርትና ጋዜጠኛ መስከረም አበራ ታሰረች



|

Want your organization to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Culinary Team

Attire

Telephone

Address


Addis Ababa
Addis Ababa
1000