Addis Home Care
እራሳችንን ከተለያዩ አደንዛዥ ዕፅዎች በመጠበቅ የህይወት ግቦቻችንን እናሳካ!
12/04/2022
ሲጋራን /ትንባሆን ልክ እንደዚ ለስነ-ውበት መጠቀም እየቻልን ለምንድን ነው ወደ ሳንባችን እያስገባን እድሜያችንን በግማሽ ምናሳጥረው??? 🤔🤔🤔
04/04/2022
የጡት ማጥባት 12 ጥቅሞች
የጡት ወተት ለህፃናት ከምግብነት ባለፈ የሚሰጠው ጥቅምና አንዲት እናት በማጥባቷ ብቻ የምታገኛቸውን ጥቅሞች እናያለን።
ጡት ማጥባት ለልጅሽ
1. ከብዙ ኢንፌክሽኖች ይከላከላል። ለምሳሌ; የሳንባና የጆሮ ኢንፌክሽን፣ የማጅራት ገትር፣ የሆድ ቫይረስ
2. ከአለረጂክ ይከላከላል።
3. ብሩህ አዕምሮ እዲኖራቸው ያደርጋል
4. ከመጠን በላይ ውፍረትን በመከላከል አስተማማኝ እድገት እንዲኖራቸው ያደርጋል
5. በህፃናት ላይ የሚከሰትን ካንሰር መጠንን ይቀንሳል
6. ድንገተኛ የሆነ የጨቅላ ህፃናትን ሞት ይቀንሳል
ጡት ማጥባት ላንቺ
7. በእርግዝና ወቅት ያደገው ማህጸን ቶሎ ወደቦታው ስለሚመለስ የሚፈሰው የደም መጠን ይቀንሳል
8. ከልጅሽ ጋር የሚኖረው ፍቅር ይጨምራል
9. ከወሊድ በኃላ ቶሎ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል
10. እድሜ ሲገፋ የሚፈጠረውን የስኳር በሽታ ይቀንሳል
11. ከጡት እና ከእንቁላል ማምረቻ ካንሰር ይከላከላል
12. ወጪ ቆጣቢ ነው።
(በዶ/ር ቤቴል ደረጀ- የማህጸን እና የጽንስ ስፔሺያሊስት)
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
0001