Relationship

Relationship

Share

�Education Consultant providing scholarship opportunities for Ethiopian students
APPLY � @marakischolarshipbot
Contact @marakiconsultant
+251989473232 +251960612222
Location:Bole, Getu Commercial C

24/01/2020

#ታስፈልጉኛላችሁ

✅ ሲኖሩ ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌላም
መኖር ግድ ነው ። አስተውል...

✅ ዛፍ የበሰለ ፍሬውን ለራሱ
አይበላም ለኛ ይሰጣል እንጂ ።

✅ የሰማዩ ዝናብ ውሃውን ለኛ
ይለግሳል እንጂ ለራሱ አይጠጣም ።

✅ የነሱ መኖር ለኛም ምክንያት ከሆነ የኛም መኖር ለሌዎች ዋስትና እና የደስታቸው ምንጭ መሆኑን ሁላችንም ልናስተውል ይገባል ።

✅ ያንተ መኖር ለሌሎችም አንድ
ቀን ለሌላ ከለላ ይሆናል ።

✅ ያንተ መቆም አንድ ቀን ሌሎችን ከመውደቅ ይታደጋል ።

✅ ያንተ መኖር ላንተ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም አስፈላጊ ነው ።

✅ ስትኖር ለራስህ ብቻ ሳይሆን
ሌላን ታሳቢ ማድረግም የግድ ነው ።

ያንዱ መኖር ለሌላ ያስፈልጋል ካላችሁ 👍 ወገን ለወገን

join join join join👇👇👇👇
❤️
❤️
👆👆👆👆

03/04/2019

ፍቅርን ያላዎቀ አፍቃሪ ተብየ
--------------------------------
አበው ሲተርቱ እንዲህ ይሉ ነበር ፍቅር
የማያውቅ ሰው አፍቃሪ አያገኝም ይሉ ነበር፡፡
ይገርማል ስላንች ብዙ ፈተናወችን
አስተናግጀ…..ብዙ መከራም ተቀብየ….ሰው
አይችለውም የተባል ነገር ሁሉ ላንች ስል በኔ
ላይ ተረማምዶብኝ ያውቃል፡፡፡ይኅም የሆነው
አንድ እኔ ብቻ አፍቃሪ በመሆኔ ነው፡፡ሆኖም ግን
ፍቅር ማለት ማፍቀር ነው እንጅ መፈቀር
አይደለም፡፡ፍቅር መተሳሰብ እንዳልሆነም ከገባኝ
ሰነባብቶአል፡፡ፍቅር ማለት ግን ማሰብ ብቻ
መሆኑን አውቄአለሁ፡፡ ፍቅር ይህ መሆኑነ ብታቂ
ኑሮ እኔ ብቻ ላፍቅርህ ብለሽ ድብድብ በገጠምን
ነበር…ግና…..በማፍቀሬ
አልተጎዳሁም….ባለማፍቀርሽ አንችም
አልተጠቀምሽም…ዛሬ ይህንን ደብዳቤ
እንዲደርስሽ ተማፅኘ ብእሬን ተደገፍሁት…ስለ
ፍቅር ምንነት ላሳውቅሽ እንጅ….ደግሜ ፍቅሬን
ተቀበይኝ ልልሽ አይደለም…. በአንች አስተሳሰብ
ፍቅር ማለት መቀበል፤ፍቅር ማለት ከ አፍቃሪ
አንድ ነገር መጠበቅ፤ፍቅር ማለት…አፍቃሪን
በፍቅርሽ እሳት እያቃጠሉ ማጨስ…….ፍቅር
ማለት አፍቃሪን መበደል….. ፍቅር ማለት ትንሽ
ነገር ሰጥቶ ብዙ ነገር መቀበል ይመስልሽ ነበር፡፡
ልንገርሽ አይደል ፍቅር ማለት የሚያስብ፤ፍቅር
ማለት የሚሰጥ፤ፍቅር ማልት ለአፍቃሪ መሰዋት
መሆን፤ፍቅር ማለት…….እጅግ ብዙ ነገር ነው፡፡
ግን አንች ፍቅር ይህ መሆኑን
ስለማታውቂ…..አፍቃሪሽን ሳይሆን ራሱን ፍቅርን
ጎዳሽው፤የፍቅርን ምንነት ስለማ ታውቂ ፍቅርን
አጎደፍሸው….ብቻ ብዙ ነገር ስላደረግሽው ፍቅር
ራሱ ተቀይሞሻል….ካሁን በሁአላ ፍቅር ራሱ
አላቅሽም እንደሚልሽ አልጠራጠርም፡፡
— s.h

Want your university to be the top-listed University in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

Address


Bole
Addis Ababa