PICE

PICE

Share

Photos from PICE's post 21/05/2026

በ16ኛው የቴክኖሎጂ ሳምንት ላቅ ያለ ውጤት ላስመዘገቡ አካላት የምስክር ወረቀት ተበረከተ

አዲስ አበባ —
ግንቦት 2018 ዓ.ም

በ2018 በጀት ዓመት በከተማ አቀፍ በተካሄደው 16ኛው የቴክኖሎጂ ሳምንት ላይ ማዕከሉን ወክለው ተሳትፎ ለነበራቸውና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላሳዩ የማዕከሉ አሰልጣኞች የዕውቅና እና የምስጋና ወረቀት የመበርከት ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ።

በዕለቱ በተከናወነው መርሀግብር ላይ በቴክኖሎጂ ሳምንቱ ላይ የተለያዩ የፈጠራ ፕሮጀክቶችን ለሰሩ እና ላቀረቡ ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት የተበረከተላቸው ሲሆን፣ በተመሳሳይ መልኩ በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ላይ ማዕከሉን በመወከል በውድድሩ ላይ ለተሳተፉና ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም የምስጋና ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

የዕለቱን መርሀግብር በመምራት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቴክኖሎጂ ልማትና ኢንኩቤሽን ም/ዲን አቶ ተስፋዬ ወርቁ ማዕከሉ በቴክኖሎጂ ሳምንት ላይ ባሳየው እጅግ ከፍተኛ ተሳትፎና ባስመዘገበው ውጤት ምክንያት የዋንጫ ሽልማትና የምስክር ወረቀት እንደተበረከተለት ገልጸዋል።

የመርሀግብሩ ማጠቃለያ ላይ የማዕከሉ ዋና ዲን አቶ አድማሱ በቀለ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ይህ ታላቅ ውጤት ሊመዘገብ የቻለው በግለሰብ ጥረት ብቻ ሳይሆን በማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ መላው አካላት በጋራና በህብረት በመስራታቸው መሆኑን አውስተዋል። ዋና ዲኑ አክለውም ይህ ስኬት እንዲመጣ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ የማዕከሉ አባላት በሙሉ ያላቸውን ጥልቅ ምስጋናና አክብሮት አቅርበዋል።

የልህቀት ማዕከሉ የሶሻል ሚዲያ ፕላት ፎርሞችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ

Websit ....
https://pice.sims.aatvetb.edu.et/

Telegram Channel …….PICE (https://t.me/pice1962)

YOUTUBE Channel ……. PICE1962
(https://www.youtube.com/)

Facebook Channel ………….PICE
(https://m.facebook.com/edu.pice.et/)

TikTok Channel ………Pice_1962
(https://www.tiktok.com/)

01/05/2026

የወርቅ ማጣሪያ
16ኛው የቴክኖሎጂ ሳምንት

30/04/2026

16 ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኖሎጂ ሳምንት
የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሀገር ብልፅግና በሚል መሪቃል በልህቀት ማዕከሉ እየተከበረ ይገኛል፡፡

Want your school to be the top-listed School/college in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Https://goo. Gl/maps/pRCrxGcKvqhzPxVB 6
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 02:00 - 17:00
Tuesday 02:00 - 17:00
Wednesday 02:00 - 17:00
Thursday 02:00 - 17:00
Friday 02:00 - 17:00