PHARMAhelp
30/06/2023
✍️ #አዲስ #የተወለዱ #ህጻናት #ላይ #የሚከሰት #ስቅታ #ለመከላከል #የሚረዱ #ዘዴዎች
******************************
#ውድ #የዶክተር #አለ #ቤተሰቦች #ከኮሮና #ቫይረስ #እራሶትንም #ቤተሰቦትንም #ለመጠበቅ #ከጤና #ባለሞያዎች #የሚሰጡትን #ምክሮች #በማክበር #ይተግብሩ #እያልን #ዶክተር #አለ #መልእክቱን #ያስተላልፋል፡፡
✅ ስቅታ የሆድ እቃንና ደረትን የሚለየዉና ለመተንፈስ የምንጠቀምበት ዳያፍራም የሚባለዉ ጡንቻ በሚኮማተርበት ጊዜ የሚከሰት ችግር ነዉ፡፡
👉 መከላከያ መንገዶቹ ምንድናቸው?
📌 ልጆ በጣም ከመራቡ በፊት ጡት ማጥባት
📌 ትንሽ ትንሽ ቶሎ ቶሎ ማጥባት
📌 በጡጦ ከሆነ የሚያጠቡት አየር አለመያዙም ያረጋግጡ
📌 ከመጠን በላይ አለማጥባት
📌 ልጆን ካጠቡ በኋላ ማግሳቱን ያረጋግጡ/ከ30 ደቂቃ-1 ሰአት ከፍ አድርገው ይያዙት
📌 በሚጠቡበት ጊዜ ልጆ የጡቶን ጫፍ ሙሉ ለሙሉ መያዙን ያረጋግጡ
#መልካም #የጤና #ጊዜን #ተመኘን!!!
👌👌👌 ከህጻናት አመጋገብ ጋር በተያያዘ እንዲሁም በማንኛውም የጤና ጉዳይ ጋር በተያያዘ ማማከር ከፈለጉ የዶክተር አለ 8809 ሀኪሞች ላይ በመደወል ያማክሩ!! ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 12 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ ሀኪሞች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ!!!
**********************************
👌👌👌ተጨማሪ የጤና መረጃ እንዲደርሶ፦
✅ የዶክተር አለ 8809 የቴሌግራም ገፅ ፦
👉👉👉 T.ME/DOCTORALLE8809
✅ የዶክተር አለ 8809 የፌስቡክ ገፅ፦
👉👉👉 http://tiny.cc/gf606y
( #በጤና #ባለሙያ #ርብቃ)
30/06/2023
የቅድመ ወሊድ ደም መፋሰስ (Antepartum hemorrhage)
የቅድመ ወሊድ ደም መፋሰስ የሚባለው ከ28ኛ ሳምንት የእርግዝና ጊዜ ጀምሮ ጽንሱ ከመወለዱ በፊት (መንታ እና ከዚያ በላይ ከሆኑ የመጨረሻው ጽንስ ከመወለዱ በፊት) ከማህጸን የሚወጣ የደም መፍሰስ ነው ።
ይህ ችግር በወቅቱ ተገቢውን ትኩረት ተሰጥቶት አስፈላጊው ህክምና እና ክትትል ካልተደረገለት የፅንሱን እና የእናትዮዋን ህይወት አደጋ ላይ ሊጥል ስለሚችል በእርግዝና እና ወሊድ ወቅት ከሚያጋጥሞ አደጋወች (obstetrics emergencies) ውስጥ ይመደባል።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት 4% ያህክሉ ነፍሰጡር እናቶች የዚህ ችግር ሰለባ ናቸው ።
የቅድመ ወሊድ ደም መፋሰስ መንስዔዎች ምን ምን ናቸው?
በአጠቃላይ ከእርግዝና እና ወሊድ ጋር የተያያዙ ምክንያቶች (obstetric causes) እና ከእርግዝና እና ወሊድ ጋር ያልተያያዙ (non- obstetric causes) በመባል በሁለት ይከፈላሉ ።
ከእርግዝና እና ወሊድ ጋር የተያያዙ ምክንያቶች ( obstetric causes) የሚባሉት;
- የእንግዴ ልጅ ጽንስ ከመወለዱ ቀድሞ መላቀቅ (placental abruption)
- የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መምጣት (placenta previa)
- የማህጸን መተርተር ( uterine rupture)
- የደም መርጋት ችግር (DIC) ... ወዘተ ዋና ዋናወቹ ሲሆኑ ከእርግዝና እና ወሊድ ጋር ከማይያያዙ መንስዔዎች ውስጥ የማህፀን በር ካንሰር (Cervical cancer) ፣ የማህፀን በር መቆጣት (cervicitis)፣ ከማህፀን በር የሚነሳ ለስለስ ያለ እባጭ (cervical polyp)፣ የብልት መሰንጠቅ (vaginal laceration) ... ወዘተ ዋና ዋናወቹ ናቸው ።
ለዛሬው በእርግዝና ወቅት በብዛት ከሚያጋጥሙት እና የጽንሱን እና የእናትን ህይወት አደጋ ላይ ከሚጥሉት መካከል ዋነኞቹ የሆኑትን የእንግዴ ልጁ ቀድሞ መላቀቅ እና የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መምጣት ምንነት ፣ አጋላጭነትን ስለሚጨምሩ ነገሮች እና ስለሚሰጠው ህክምና ለማንሳት እሞክራለሁ።
1. የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መላቀቅ (placental abruption)
የእንግደ ልጅ ከተጣበቀበት የውስጠኛው የማህጸን ግድግዳ በጤነኛ የእርግዝና እና ወሊድ ጊዜ የሚላቀቀው ጽንስ ከተወለደ በኋላ ነው።
ጽንስ ከመወለዱ በፊት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ከተላቀቀ የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መላቀቅ (placental abruption) እንለዋለን።
1.5% የሚሆኑ ነፍሰጡር እናቶች በእርግዝና ወይም በወሊድ ወቅት ይህ አይነቱ ችግር እንደሚገጥማቸው ጥናቶች ያሳያሉ።
80% የሚሆኑት የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መላቀቅ ችግር የሚገጥማቸው ነፍሰጡር ሴቶች በብልት በኩል ወደ ውጭ የሚወጣ የደም መፍሰስ የሚኖራቸው ሲሆን 20% የሚሆኑት ግን ምንም አይነት ወደ ውጭ የሚወጣ የደም መፍሰስ ላይኖራቸው ይችላል ።
ይህም የሚሆነው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የተላቀቀው የእንግዴ ልጅ ደም በማህጸን ጫፍ በኩል ወደ ውጭ እንዳይወጣ ስለሚያግደው እና የሚፈሰው ደም ወደ ውጭ መውጣቱ ቀርቶ እዚያው ማህጸን ውስጥ ስለሚጠራቀም ነው ።
የእንግዴ ልጅ ቀድሞ የመላቀቅ እድልን የሚጨምሩ ነገሮች (Risk factors) ምን ምን ናቸው?
- የእድሜ መግፋት (increased age)
- ከሁለት እና ከዚያ በላይ ጊዜ መውለድ (multiparity)
- ከእርግዝና በፊት የነበረ ወይም በእርግዝና ጊዜ የሚፈጠር የደም ግፊት (hypertensive disorders of pregnancy)
- የእንሽርት ውሀ ቀድሞ መፍሰስ (premature rupture of membranes)
- መንታ እና ከዚያ በላይ እርግዝና (multiple pregnancy)
- የእንሽርት ውሀ መብዛት (polyhydraminos)
- ሲጋራ ማጨስ እና ኮኬን መጠቀም
- የበፊት እርግዝና ላይ የእንግዴ ልጅ ቀድሞ የመላቀቅ ችግር ከነበረ
- የማህፀን ጡንቻ እጢ (myoma) ... ወዘተ ናቸው ።
የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መላቀቅ እንዴት ይታወቃል?
- ችግሩ የሚታወቀው በዋነኝነት ታካሚዋ በምትሰጠው ግለ ታሪክ (history) እና አካላዊ ምርመራ (physical examination) ነው ።
የአልትራሳውንድ ምርመራ የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መላቀቅ ችግርን ለማወቅ የሚሰጠው ጥቅም እምብዛም ነው ።
- የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መላቀቅ ችግር የገጠማት እናት በአብዛኛው ጠቆር ያለ ከማህፀን የሚወጣ ደም መፋሰስ ይኖራታል ። መለስተኛ የሆድ ቁርጠትም አብሮ ሊኖር ይችላል።
- አካላዋ ምርመራ ላይ የታችኛው የሆድ ክፍል በእጅ በሚነካበት ጊዜ የህመም ስሜት ፣ የፅንስ የልብ ምት አአስተማማኝ አለመሆን እንዲሁም እንደተላቀቀው የእንግዴ ልጅ ክፍል መጠን እና እንደፈሰሰው የደም መጠን የእናት የልብ ምት መጨመር ፣ የደም ግፊት መቀነስ እና የጽንስ ሆድ ውስጥ መጥፋት ሊኖር ይችላል ።
አስፈላጊ ምርመራወች ምን ምን ናቸው?
- ሙሉ የደም ምርመራ
- የኩላሊት እና ጉበት ምርመራ
- የአልትራሳውንድ ምርመራ
- የደም መርጋት ችግር መኖር እና አለመኖሩን ለማወቅ የሚደረጉ ምርመራወች ።
የእንግዴ ልጅ ቀድሞ የመላቀቅ ችግር በእናትየዋ እና በጽንሱ ላይ ምን ምን አይነት ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል?
- የፅንስ የልብ ምት አስተማማኝ አለመሆን
- የደም መርጋት ችግር
- የኩላሊት መጎዳት ወይም ስራ ማቆም
- የድህረ ወሊድ ደም መፋሰስ (post partum hemorrhage)
- እንድሁም እንደ ህመሙ ደረጃ እስከ ፅንስ ሆድ ውስጥ መሞት እና የእናት ሞት ድረስ ሊያደርስ ይችላል ።
ህክምናው እንዴት ይሰጣል?
- ሆስፒታል አልጋ አስይዞ ማስተኛት (in patient management)
- የጽንሱን እና የእናትየዋን የጤንነት ሁኔታ በየጊዜው የተለያዩ ምርመራወችን በማድረግ ክትትል ማድረግ
- የደም ማነስ ክኒን መውሰድ
- የሳምባ ማጠንከርያ መድሀኒት መስጠት ... ወዘተ
እርግዝናውን እስከ ስንት ጊዜ ድረስ መግፋት ይቻላል?
- የእናትየዋን ወይም የጽንሱን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል አንገብጋባቢ እና ድንገተኛ ችግር እስካላጋጠመ ድረስ ከላይ የተዘረዘሩት ህክምናወች እና ክትትል እየተደረገ እስከ 37 የእርግዝና ሳምንት ጊዜ ድረስ ሊገፋ ይችላል ።
- የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መላቀቅ ሌላ በኦፕሬሽን ለመውለድ የሚያስገድድ ምክንያት እስከሌለ ድረስ በራሱ በእፕሬሽን ለመውለድ ምክንያት አይደለም ።
-የሚመረጠውም በምጥ መውለድ ነው።
2. የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መምጣት (placenta previa)
- የእንግዴ ልጅ ቀድሞ መምጣት የምንለው የእንግዴ ልጅ ተጣብቆ መቀመጥ ከነበረበት የላይኛው የማህፀን ክፍል ውጭ ወደ ታች ወርዶ የውስጠኛውን የማህጸን በር ቀዳዳ (internal cervical opening) ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በመዝጋት ተጣብቆ ሲቀመጥ ነው ።
- ስርጭቱ እስከ 0.5% ይደርሳል ።
- 20% የሚሆነው የቅድመ ወሊድ ደም መፋሰስ የሚከሰተው በዚሁ ችግር አማካኝነት ነው ።
የእንግዴ ልጅ ቀድሞ የመምጣት ችግር የመከሰት እድልን የሚጨምሩ ነገሮች;
- የማህፀን ጠባሳ
- 2 ጊዜ እና ከዚያ በላይ መውለድ
- የእድሜ መግፋት
- መንታ እና ከዚያ በላይ እርግዝና
- ሲጋራ ማጨስ
- ከዚህ በፊት በነበር እርግዝና ላይ ችግሩ ከነበረ
- የእንግዴ ልጅ መጠን መተለቅ
- ከፍተኛ ቦታወች ላይ መኖር ...
- የማህፀን መጠረግ ... ወዘተ ናቸው ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa