Hirnoye
Hirnooyyeen Garee dhalattootaafi jiraattoota Hirna turanfi ta'an itti walargan, hariiroo isaanii cimsan, walgargaaran, muuxannoo waljijjiiran, garee amataa fi siyaasaa kamuu irraa bilisa ta'eedha. Muuxannoo, beekumsa, baruumsa, qabeenya, beekkamtii fi maallaqa arganneen Hirnaafi hawaasa deeggaruudha. Hirna sadarkaa magaaloota biroo argine waliin walqixxeessuuf hojjata. Kanaafu, guddina Hirnaafi hawaasa gargaaruf hirmaannaan keessan barbaachisaadha.
05/07/2026
አንጋፋዉ የ ኬሚስትሪ ምሁር ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኘ
ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኘ ሰኔ 1 ቀን 1936 ዓ.ም በሀረርጌ ክፋለሀገር ተወለዱ። ፕሮፌሰር ኤርሚያስ በ1960 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ በ1966 ዓ.ም ደግሞ አሜሪካን ሀገር ከሚገኘው ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ (ሳንፍራንሲስኮ) የፒ ኤች ዲ ዲግሪ አግኝተዋል።
ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኜ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኦርጋኒክ ኬሚስትሪ መምህር እና ተመራማሪ ናቸው። ከ75 በላይ ሳይንሳዊ ጽሑፎችን በታዋቂ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ አሳትመዋል። እ.ኤ.አ. ከ1977-78 የኢትዮጵያ ጆርናል ኦፍ ሳይንስ መስራች አዘጋጅ እና ከ1984-1996 የተፈጥሮ ምርቶች ምርምር መረብ ለምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ ዋና ፀሀፊ ነበሩ። እ.ኤ.አ. በ1997 የ IFS/Danida ሽልማት ተሸላሚ ነበሩ። በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ የተፈጥሮ ምርቶች ላቦራቶሪ መሪ፣ የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር ሶሳይቲ የክብር ፕሬዝዳንት እና የሁለት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች( Getachew Bolodia Foundation and the Lucy Mother and Child Care) ሊቀ-መንበር ነበሩ።
የተለያዩ የትምህርትና ምርምር _ ሽልማቶችን ከታዋቂ ተቋማት አግኝተዋል። ከነዚህም ከቀዳማዊ ሀይለስላሴ ሽልማት ድርጅት ለኣራት ዓመት እስኮላርሺፕ ከካሊፎርኒያ ዮኒቨርሲቲ የፒኤች ዲ ትምህርት ድጋፍ ፡ ከጀርመን አገር የሁለት ዓመት የሁምቦልት የምርምር ፌሎሺፕ፤ _ ከአሜሪካን አገር የፉልብራይት የምርምር ፌሎሺፕ ተጠቃሽ ናቸው። እንዲሁም በተፈጥሮ ውጤቶች ላይ ምርምር ለማካሄድ ከስዊድን የሲዳ ሳሬክ እና ከሌሎች ድርጅቶች የምርምር ድጋፍ ለማግኘት ችለዋል።
የበጎ ሰው ሽልማት ጳጉሜ 5 ቀን 2015 ዓ.ም ለ11ኛ ጊዜ ባካሄደዉ የእዉቅና መርሃግብር ከተሸለሙ እዉቅ ኢትዮዽያዉያን መካከል ኤሜሪተስ ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኘ አንዱ ናቸዉ።
ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ የሚከተሉትን ስራዎችም አከናውነዋል፣ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ዲግሪ (Masters and PhD) የአገር ውስጥና የውጭ አገር ተማሪዎችን በማስተማርና በማማከር ፣SNEI በመባል የሚታወቀውን የኢትዮጵያ የሳይንስ ጆርናል የመጀመሪያ አዘጋጅ በመሆን፣ Natural Products Research Network for Eastern and Central Africa NAPPECA) በምስራቅ እና በመካከለኛው አፍሪካ በተፈጥሮ ውጤቶች ጥናትና ምርቶች ላይ ያተኮረ የእውቀት ትስስር ተቋም በዋና ፀሀፊነት ለ12 ዐመት በመምራት ፣ Science and tchnology toms translation project ( የሳይንሳዊ ቃላት ስያሜና ትርጉም መርሀ ግብር) ለ6 ዓመት በመሳተፍ የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ፍላጉት እና አቅም ቅኝት ፕሮጀክት (University Industry Needs and Capabilities Survey Project) - ለሁለት ዐመት በመሳተፍ " የጌታቸው ቦሎዲያ ተቋም (foundation) ለ12 ዐመት መምራት ፣ African Laboratory for Natural Products (ALNAP) የተባለውን ኔትወርክ ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ መመስረትና መምራት ፣ .com የተባለውን ከ5000 በላይ አገር በቀልና የአፍሪካ እፅዋትን ዝርዝር እና ጥቅም የያዘ ዳታቤዝ በመፍጠር ፣ በዘርፉ የሚሰማሩ ተመራማሪዎች እንዲሁም ማንኛውም ሰው የእፅዋቶችን ሣይንሳዊ ስምና ሌላ መረጃ- ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ከ15 በላይ _ የዓለም - አቀፍ : የውይይትና የልምድ : እና በቀላሉ እንዲያገኝ አድርገዋል፣ የመማማሪያ መድረኮች ላይ ተሳትፈዋል፤ ልምዳቸውንም አካፍለዋል ፤ አራት የሚሆኑ የሙያ ማህበራት አባል ሲሆኑ ናቸው፤ ማህበራቶቹን በማቋቋምም እረድተዋል እና ከ100 በላይ ላይ አሳትመዋል።ሳይንሳዊ የምርምር ጽሁፎችን በአለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ጆርናሎች
ፕሮፌሰር ኤርሚያስ የምርምር ጥናቶችና ውጤቶችን ወደተግባር ቀይረው፣ ሀገር በቀል ተክሎችን ግብአቶችን በመጠቀም በኢትዮጵያ እና ከኢትዬጵያ ውጭ የማህበረሰብ ጤና እና ደህንነት እንዲሻሻል፣ ሰፊ አበርክቶ አላቸው። ለዚህም ዋነኛ ተጠቃሽ የሆነው በ1992 ዓ.ም በእርሳቸውና በቤተሰባቸው የተቋቋመው አሪቲ የመዓዛማ ዕፅዋት ምርቶች ተብሎ የሚታወቀው ድርጅት ነው፡፡ አሪቲ ለውበት እና ለጤንነት መጠበቂያ የሚሆኑትንና እና ጥሩ መአዛ ያላቸውን ውጤቶችን ከሀገር በቀል እና መጤ እፅዋት ሳይንሳዊ ዘዴዎችን በመጠቀም በማምረት እና ለገበያ በማቅረብ ይታወቃል፡፡
ምርቶቹም በዲስቲሌሽን ከተለያዩ እፅዋት መዐዛማ ዘይትን በማውጣት፤ እንደባህሪያቸው በመቀመም ለጤና እና ውበት መጠበቂያ፤ ለጥሩ የቤት ውስጥ ጠረን እንዲሆን ተደርጎ እየተዘጋጁ : በሀገር ውስጥ እና ውጭ ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ። እነዚህ ምርቶች በሀገር ውስጥ ለግል ተጠቃሚዎች፤ ሆቴሎች፤ ሎጆች እና የተለያዩ የጤና እና የውበት መንከባከቢያ ቦታዎች (SPA) በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ በማድረግ፣ ለውጭ ገበያ ሲቀርቡ ደግሞ የውጭ ምንዛሪ በማምጣት እየጠቀሙ ይገኛሉ።
ከላይ ለተጠቀሱት ምርቶች ግብአት የሚሆኑት እፅዋት ከግል እርሻ እና ከተለያየ አካባቢ ገበሬዎች ይወሰዳሉ፡፡ በዚህም ምክንያት አሪቲ ከኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት ጋር የአርክቦት _ ውል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ (Agreement on Access to, and Benefit Sharing)። ፕሮፌሰር ኤርሚያስ ዳኜ ባለትዳር እና የሁለት ሴት ልጆች አባትና የአራት ልጅ ልጆች አያት ናቸው።
ገመቺስ፣ ምዕራብ ሀረርጌ፣ ኦሮሚያ
Gammachiis, Harargee Lixaa, Oromiyaa Part 7
ገመቺስ፣ ምዕራብ ሀረርጌ፣ ኦሮሚያ
Gammachiis, Harargee Lixaa, Oromiyaa Part 6
ገመቺስ፣ ምዕራብ ሀረርጌ፣ ኦሮሚያ
Gammachiis, Harargee Lixaa, Oromiyaa Part 5
Click here to claim your Sponsored Listing.
Contact the organization
Telephone
Address
Hirnoye
Addis Ababa
2957