Fune Media
17/06/2026
በሰሜን ወሎ ዞን በጫካ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው።
በሰሜን ወሎ ዞን በጫካ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በየጊዜው መንግሥት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ እየተቀበሉ መኾናቸውን የዞኑ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ አስታውቋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኀላፊ ፈለቀ ጌትነት መንግሥት ከማኅበረሰቡ ጋር ባደረጋቸው ውይይቶች ሰላምን ለማረጋገጥ መግባባት ላይ መደረሱን አስታውሰዋል። በዚህ መሠረትም ማኅበረሰቡ የሰላምን አስፈላጊነት እና የግጭትን አስከፊነት ለታጣቂዎች በማስረዳት ወደ ሰላም እንዲመለሱ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
መንግሥት የሰላም ጥሪ ካቀረበ በኋላ በተሳሳተ መንገድ ጫካ ገብተው የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እንደተቀበሉ ተናግረዋል። ከእነዚህ ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ የሚኾኑት የተሃድሶ ሥልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል።
ሥልጠናውን ወስደውም የመንግሥት ሥራ የነበራቸው ወደ ቀድሞ ሥራቸው እንዲመለሱ፣ ያልነበራቸው የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲኾኑ እየተደረገ ነው ብለዋል።
ትግሉ የውጭ ባዕዳን እና የውስጥ ባንዳ እየተጠቀሙበት ያለ ትግል መኾኑን እየተረዱ በርካቶች አሁንም የሰላም አማራጩን እየተቀበሉ እንደሚገኙም ነው የጠቀሱት። ወደ ሰላም የሚመለሱ ታጣቂዎችንም ሥልጠና እንዲያገኙ በማድረግ የልማት እና የሰላም አርበኛ የማድረግ ሥራው ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።
የሰላም አማራጩን የተቀበሉ የቀድሞ ታጣቂዎች ጫካ የሚገኙ ወጣቶችን በማሳመን ሰላም እንዲሰፍን ተጨማሪ አቅም ኾነው እየሠሩ እንደሚገኙም አመላክተዋል።
የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ጫካ የወጡት ታጣቂዎች የሰላም ጥሪውን እንዲቀበሉ ከማድረግ በተጨማሪ ከማኅበረሰቡ ጋር እርቀ ሰላም እንዲፈጽሙ እና የተጣሉ እንዲታረቁ በማድረግ ሰላማዊ ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉ በማድረግ ለዞኑ ሰላም መስፈን ጉልህ ሚና እየተጫወቱ መኾናቸውን ተናግረዋል። ይህንንም አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ነው ያሉት።
በተሳሳተ አመለካከት ጫካ የወጡትን ወጣቶች ወደ ሰላም ለመመለስ የተሠራው ሥራ ውጤት እየተገኘበት ነው ያሉት ምክትል ኀላፊው አሁን ላይ ሰሜን ወሎ ዞን አንፃራዊ ሰላም እየታየበት መኾኑንም ተናግረዋል።
አሚኮ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Addis Ababa