AAPPA
21/10/2023
በዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶግራፍ አውደርዕይ ላይ ተሰናድቶ የነበረው የዘወትሯ ኢትዮጵያ ወጎች ዝግጅት በግሩም መልኩ ተጠናቋል። በዝግጅቱ ላይ በርከት ያሉ ታዳሚዎች የተገኙ ሲሆን የዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶ አውደርዕይ በመላው አገሪቷ ያደረገውን ጉዞ እንዲሁም የፎቶግራፍ ጥበብ በማህበረሰብ ትስስር ሂደት ውስጥ ያለው ሚና በሰፊው ተቃኝቷል። ከዚህ በተጨማሪም በዕለቱ የፎቶግራፍ ጥበብን በተመለከተ ከፎቶግራፍ ባለሙያዎቹ ጋር ጥልቀት ያለው ውይይትም ተደርጓል። በዝግጅቱ ላይ ታድማችሁ ሃሳባችሁን ለሰጣችሁ እንዲሁም ስራዎቻችንን ለጎበኛችሁ በሙሉ ምስጋናችን የላቀ ነው!🙌💥📸
የዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶግራፊ አውደርዕይ በአዲስ አበባ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ማህበር (አአፎባማ) ከUSAID እና ግራር፣ የጠቢባን መናኸርያ ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል።
What an incredible experience! Our panel sessions were bursting with energy, inspiration, and passion from the talented photographers we met. Your enthusiasm reignited our love for the art of photography. A heartfelt thank you to everyone who joined us at these amazing events! Your visit meant the world to us!🙌💥📸
Everyday Ethiopia is brought to you by the Addis Abeba Professional Photographers Association (AAPPA) in collaboration with USAID and Gerar - The Creative Hub
#የዘወትሯኢትዮጵያ
#ተጓዥየፎቶግራፍአውደርዕይ
#አአፎባማ
#የአዲስአበባፎቶግራፍባለሙያዎችማኅበር
17/10/2023
📸✨ ሰንበትን ከየሮ ጋር!
ባሳለፍነው እሁድ ፕሮፌሽናል የፎቶግራፍ ባለሙያ ከሆነው የሮ አዱኛ ኢቲቻ ጋር ግሩም ቆይታ አድርገናል። በዕለቱ ጥቁር ሰው በበርሊን የሚለውን ፕሮጀክቱን በጥልቀት ያስቃኘን የሮ የበርሊን ቆይታውን እንዲሁም የፎቶግራፍ ሙያ ጉዞውን አጋርቶናል። በዕለቱ ተገኝታችሁ ይህንን ዝግጅት ለተካፈላችሁ እንዲሁም የሮ አዱኛን ከልብ ልናመሰግን እንወዳለን! 🌟
የዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶግራፍ አውደርዕይ አንድ ቀን ብቻ ቀርቶታል! እንዳያመልጥዎ!🌍📸
📸✨ Last Sunday with Yero!
What an incredible experience! Last Sunday, we had the privilege of spending time with the talented photographer From his adventures in Berlin to his inspiring ‘Black Man in Berlin’ project, he took us on a journey of awe-inspiring visuals and captivating stories. Thank you for such an inspiring session, Yero! 🌟
One last chance to embark on this incredible journey! Join us at Everyday Ethiopia photography exhibition, only 1 day left! 🌍📸
#የዘወትሯኢትዮጵያ
#ተጓዥየፎቶግራፍአውደርዕይ
#አአፎባማ
#የአዲስአበባፎቶግራፍባለሙያዎችማኅበር
16/10/2023
የዘወትሯ ኢትዮጵያ ለሁለት ተከታታይ ወራት ሲያደርግ የነበረውን የፎቶግራፍ አውደርዕይ እያጠናቀቀ ነው!
አውደርዕዩ የአዲስ አበባ ጉዞውን ጥቅምት 2/2016ዓ.ም ላይ በርካታ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ የፎቶግራፍ አፍቃርያንና አዘጋጅ አካላት በተገኙበት ሞቅ ደመቅ አድርጎ ጀምሯል። ተጓዥ የፎቶግራፍ አውደርዕዩ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ በልዩነት ውስጥ ያለውን ውበት አጉልቶ የማሳየትና በመግባባትና አዎንታዊ ግንኙነት ላይ የተመሠረተ ማህበራዊ ትስስር ለመፍጠር ያለመ ነው። እያንዳንዱ ፎቶግራፍ የኢትዮጵያን አስደማሚና ምሉዕ ገጽታ በማውጣት አንድነትንና ትስስር የሚያጎላ ገጽታ አለው።
ዐውደ ርዕዩ ወጣቶች በፈጠራ ሥራዎች በኩል ለሰላምና ለመግባባት እንዲበረቱ ዕድል በመክፈትና እርሾ ኾኖ በማገልገል በመተባበር ሊመጣ የሚችለውን ውጤታማ ህብር የሚያሳይ ሆኖም ያገለግላል።
በዚህ ዝግጅት ላይ የተካፈላችሁትን የሚዲያ ባለሙያዎች በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን ። የዘወትሯ ኢትዮዽያን በሚዲያዎቻችሁ ስለሰጣችሁት ሽፋንና ማበረታቻ አክብሮታችን ላቅ ያለ ነው።
ታሪካዊ የሆነውን ይህንን የፎቶግራፍ አውደርዕይ በቀሩት ቀናት ላይ በመካፈል የዘወትሯን ኢትዮጵያን አብረውን እንዲቃኙ እንጋብዛለን!
📍ቃና ስቱዲዮ
የዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶግራፊ አውደርዕይ በአዲስ አበባ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ማህበር (አአፎባማ) ከUSAID እና ግራር፣ የጠቢባን መናኸርያ ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል።
Celebrating two months of capturing memories and inspiring moments at the Everyday Ethiopia Touring Photo Exhibition!
What an incredible journey it's been! The exhibition has captivated audiences everywhere, from Bahirdar to Dredawa and then Hawassa. Through the lens of 15 photographers, "Everyday Ethiopia" captures poignant moments of authentic daily life, meticulously staged depictions of vibrant cultural celebrations, and bustling scenes from local markets.
We couldn't be more grateful for the media officers and journalists who were part of the press release. We deeply appreciate your support in helping our cause in the Everyday Ethiopia Photography Exhibition! Thank you all for joining us on this artistic adventure!
We wholeheartedly invite you to join us at this extraordinary event as we celebrate the beauty and diversity of Ethiopia in the remaining days! Miss it not, join us now!
📍Kana Studio
Everyday Ethiopia is brought to you by the Addis Abeba Professional Photographers Association (AAPPA) in collaboration with USAID and Gerar - The Creative Hub
NBC EthiopiaFBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)Tikvah-EthiopiaGetu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)ተስፋዬ ለማ - Tesfaye LemmaEBS.TV
#የዘወትሯኢትዮጵያ
#ተጓዥየፎቶግራፍአውደርዕይ
#አአፎባማ
#የአዲስአበባፎቶግራፍባለሙያዎችማኅበር
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the organization
Website
Address
Addis Ababa