Nebba
22/03/2026
ሁሉ አለሜ በራ
የምትሉኝ ሰራ
ያ ሳድግ የሚገባኝ
እንዲሆን ሆነና
በኔ ቤት አበራ
በናንተ የተሰራ
እኔ ራሴን ሆንኩኝ
ለእናንተ ምስጋና
📸
Creative director
Cinematographer
እንደኔ የሚበልጠኝ ሙዚቃ ሰርቻለሁ ብዬ አስባለሁ
በኑሪ በፈገግታ አዲስ ምዕራፍ ጀምሬአለሁ ።
ሙሉ ጊዜዬን ሰጥቼ ለ 5 አመት ከ8 ወር ብዙ ዘፈኖች ሰርቻለሁ የተወሰኑትን ወደእናንተ አድርሻለሁ ፤ ኑሪ በፈገግታን ከፃፍኩበት ቀን ጀምሮ ሙዚቃ አዲስ ሆናብኛለች ለዛ ነው በዚ ሙዚቃ መጀመር የፈለኩት።
በነገራችን ላይ እስካሁን ከለቀኳቸው ሙዚቃዎች ሙሉ የዘፈን ፅሁፍ በራሴ የሰራሁት የመጀመርያ ዘፈን ነው 😊
በሙዚቃ አሬንጅመንቱም ላይ ተሳትፌያለሁ 😁🙌🏽
ከተፃፈ 11 ወር የሞላውን ይሄን ሙዚቃ መጀመርያ Live Record አድርጌ ለእናንተ ለማድረስ ነበር ያሰብኩት ፤ ባላሰብኩት መንገድ ሙዚቃውን ራሴ አቀናብሬ የባንድ Rehearsal ስጀምር አቶ በጣም ዘፈኑን እንደወደደው እና የ studio ዘፈን እንዲሆን አጥብቆ ሀሳብ ሰጠኝ የማምነው ሰው ነበርና ሀላፊነቱን ለራሱ ሰጠሁት እጅግ ትክክለኛ ውሳኔ ይመስለኛል ውጤቱን እንደምታዩት ነው ።
ከዛም በዃላ ለሰራናቸው ሙዚቃዎች ጥሩ መሰረት ሆኖናል
እጅግ ላመሰግነው ፈልጋለሁ 😊🙏🏽
ን እግዚአብሄር ሰጠኝ
እግዚአብሄር ያቆይልኝ😊🙏🏽
ሌላ ጊዜ እንዴት እንደተዋወቅን አጫውታችዃለሁ (ካስፈለገ)
የሙዚቃ ቪድዮውን ሀሳብ ስትነግረኝ ድምጿን ፥ የእርግጠኛነቷን ስሜት መቼም አልረሳውም ።
እኔ አዲስ ሙዚቃ ሰርቼ ለሰው ሳብራራ እንደማብራራበት አይነት መንገድ ነበር 😊 የተቀበልኳት ግን ወዲያው አልነበረም😁 አሁን ግን የሄድናቸውን መንገዶች እወዳቸዋለሁ የኑሪ በፈገግታ የሙዚቃ ቪድዮ ይሄ ስነሆነ ትልቅ ደስታ፣ ኩራት ሁላ ይሰማኛል ።
ከዚህ በዃላ የምሰራቸው ፕሮጀክቶች ፣ የሚኖሩኝ እያንዳንዱ የስቱድዮ እና የመድረክ ስራዎች ላይ እዚህ ፕሮጀክት ላይ የነበረኝን የእርካታ ስሜት ደግሜ የማገኘው ከሆነ በዚች ምድር ላይ የማሳልፈውም ጊዜ የደስታ ነው የሚሆነው 😁
አቶ ena ለጊዜው ማናጀሮቼ ናቸው 😁
ምንም ማናጀር እንደሌለኝ እንዲሰማኝ አያደርጉኝም
ሙዚቃ ስራ እንዳይሆንብኝ ነው የሚያደርጉኝ 🫶🏽 የሚገርሙ አርቲስቶች ሳይሆኑ የ ሚገርሙ ሰዎች ናቸው እዚህ ውስጥ ጨምሩልኝ
ቀጥታ ስክት ነው ያለችው ።ጠንካራነቷን ደግሞ ተውኝ 3ቀን ከጠዋት ጀምሮ ከእኛ ጋር ስትቀርፅ ውላ ለሊቱን የራሷን መደበኛ ስራ ሰርታ ከ2 ሰዐት በላይ ሳታርፍ ነበር ለተከታታይ ነበር ስትደክም የነበረው ።የተሰጣትንም ገፀባህሪ በሚገርም ብቃት ነበር የተጫወተችው
ከልቧ እንደ ልባችን ነበር ስትሰራ ነበር ስትሰራ የነበረው
እዚህ ጋር , ጨምሩልኝ 🙏🏽
እግዚአብሄር ይባርካችሁ።
በምድር ላይ ለምንኖርበትን ምክንያት ብዙ ዋጋ የከፈልንበት carrier በማንፈልገው መንገድ መስራት በበጣም የሚያስፈራ ነገር ነው
ትልቅ ሆኖብኝ ከብዶኝ የነበረውን ህልም በዛው እንዳይቀር ይልቅ እውን እንዲሆን እያደረጋችሁ ስለሆነ እጅግ በጣም አመሰግናችዃለሁ
ደክሞኝ ልጥለው ስል ነው እና የደረሳችሁት አመሰግናችዃለሁ
እናንተም ትልቅ support system ነበራችሁ 🙏🏽musiqa
el__
ሙዚቃን በፈለግኩበት ለመስራት ለመስራት ብዙ አመታት ታግዬ አሁን በፍቅር እየሰራሁት ነው
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the public figure
Address
Addis Ababa