Kolfe Media Network
29/08/2024
❤️🇪🇹
💙🇪🇹
for watch more 👆👆👆👆.
❤️
✍️
█▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
┊┊┊▕▔╲▂▂▂╱▔▏
╭━━╮╭┈╮⠀╭┈╮╭━━╮
╰╰╰┃▏╭╮⠀╭╮▕┃╯╯╯
┈┃⠀┃▏┈┈▅┈┈▕┃⠀┃
┈┃⠀┃▏┈╰┻╯┈▕┃⠀┃
┈┃⠀╰█▓▒░M░E░▒▓█
14/03/2024
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አነሳ
******************
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ በሚገኘው 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ጉባዔው የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።
የፍትህ ሚንስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ የምክር ቤት አባሉን ያለመከሰስ መብት መነሳት አስመልክቶ ለህዝብ ተወካዮች ማብራሪያ አቅርበዋል።
በማብራሪያቸውም፤ አቶ ክርስቲያን በአማራ ክልል ሕገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ከሚንቀሳቀሱ አካላት ጋር አብረው ሲሰሩ እንደነበር የፌዴራል ፖሊስ መርምሮ ለአቃቢ ሕግ ልኳል ብለዋል።
ምክር ቤቱም በውሳኔ ቁጥር 9/16 የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አንስቷል።
17/06/2023
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ።
ከግብር እዳ ነጻ መንደር ለመፍጠር እየተሰራ ባለ ስራ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ከ2.1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ።
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሳምንታዊ የገቢ አሰባሰብ አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ ግምገማ ማካሄዱን አስታውቋል።
በክፍለ ከተማው በሁሉም ወረዳዎች የግብር አሰባሰብ ንቅናቄ ያለበትን ደረጃ የክፍለ ከተማው አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ፣የመሬት ልማት አስተዳደር ምክትል ሀላፊ ፣የክፍለ ከተማው ፋይናንስ ጽ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም የወረዳ የገቢ ግብረ ሀይል አመራሮች በየዘርፉ የተሰሩ ስራዎች ሳምንታዊ አጭር ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
ግምገማውን የመሩት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው በሁሉም ወረዳዎች በግምገማው በጥንካሬ እና በድክመት የተቀመጡ ስራዎች በመኖራቸው በቀጣይ የገቢ አሰባሰብ ሂደቱ በታቀደው ልክ እንዲሳካ እንዲሁም ገቢ መሰብሰብ እንዲቻል በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በድክመት እና በጥንካሬ የተሰሩ ስራዎችን በየደረጃው በመለየት በቀጣይ ቀሪ ጊዜያቶች ዕቅዳችንን እናሳካለን ሲሉ የግምገማው ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
እስካሁን በተሰበሰበው የገቢ ግብር 1.45 ቢሊየን እንዲሁም በማዘጋጃቤታዊ ግብር አሰባሰብ 710 ሚሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን በግምገማው ወቅት ተገልጿል ።
ምንጭ:- ኮልፌ ቀራንዮ ኮሙኒኬሽን
True and reliable source of information. Thank you keep up sharing contents.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Bethel
Addis Ababa