Ethio Fact Info
09/07/2026
የተከዳው የፍታው ንጉስ
ከማዴይራ እስከ ስድስተኛው የዓለም ዋንጫ
በእንባ የተሸኘው ንጉስ ፤ CR7 ከማዴይራ እስከ ስድስተኛው የዓለም ዋንጫ #CristianoRonaldo በእንባ የተሸኘው ንጉስCR7 ከማዴይራ እስከ ስድስተኛው የዓለም ዋንጫ ...
14/06/2026
https://youtu.be/lt1uyR8xmYo?si=nj4wnQrg4ytThxnW
ሰበር ሚስጥር፡ ፋኖ፣ ህወኃት እና OLA አዲስ ጥምረት ፈጠሩ? "የኢትዮጵያ ወታደራዊ ካውንስል" ሰበር መረጃ፡ በኢትዮጵያ አዲስ ወታደራዊ ጥምረት?በዚህ ቪዲዮ የምንዳስሳቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦ የቀይ ...
03/06/2026
ታዋቂው የእስልምና ሃይማኖት መምህር ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በምስራቅ አርሲ ዞን በኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የደረሰውን ዘግናኝ ጭፍጨፋ፣ እንዲሁም የመኖሪያ ቤቶች እና የቤተ ክርስቲያን ቃጠሎ አጥብቀው አወገዙ። ኡስታዙ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት ወቅታዊ መልእክት "የንጹሃን ደም መፍሰስ ይብቃ፡ ለዘላቂ ሰላም በጋራ እንምከር!" በማለት ጥሪ አቅርበዋል።
በዚህ መልእክታቸው የፍትህ እጦት ጉዳይን በስፋት ያነሱት ኡስታዝ አህመዲን፣ ባለፉት ዓመታት በንጹሃን ዜጎች፣ በመስጊዶች እና በቤተክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ያደረሱ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተጠያቂ አለመደረጋቸው እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ገልጸዋል። ጥቃቶቹ እየተደጋገሙ ፈጻሚዎቹ ግን ሁልጊዜም "ያልታወቁ" እየተባሉ መፍትሄ አለመገኘቱ፣ ሀገሪቱን ወደ ከፋ አደጋ የሚመራ አካሄድ መሆኑንም በጽኑ አስጠንቅቀዋል።
በተጨማሪም የሰው ልጅ ነፍስ መርከሱ እጅግ አደገኛ መሆኑን የጠቀሱት የሃይማኖት መምህሩ፣ የሰውን ልጅ ህይወት ክቡርነት ከቅዱስ ቁርኣን አል-ማኢዳህ (5:32) ምዕራፍ ዋቢ በማድረግ አስተምረዋል።
በዚህ መለኮታዊ መመሪያ መሰረት አንዲትን ንጹሕ ነፍስ ያለ አግባብ መቅጠፍ መላውን የሰውን ዘር እንደ ማጥፋት የሚቆጠር እጅግ ከባድ ወንጀል መሆኑን አስገንዝበዋል። በአንጻሩ አንዲት ነፍስን ማዳን መላውን የሰው ልጅ እንደማኖር የሚቆጠር ታላቅ ሰብአዊ በጎነት መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህ መመሪያ የሰው ልጅን ህይወት ያለምንም የዘር፣ የሃይማኖትና የብሔር ልዩነት ፍጹም የተከበረ መሆኑን እንደሚያሳይ አብራርተዋል።
ይህንን የጥፋት አዙሪት አስቁሞ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት፣ ማህበረሰቡ ከስሜታዊነት ርቆ ቆም ብሎ ማሰብ፣ ነገሮችን በእርጋታ መመርመር እና በጋራ መምከር እንደሚያስፈልገው ኡስታዝ አህድን አሳስበዋል።
ኡዝታዙ ድርጊቱ ልብን በሀዘን የሚሰብር መሆኑን ጠቅሰው፣ ለሟች ቤተሰቦች እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል። እውነቱ ወጥቶ የንጹሃን ደም አፍሳሾች የፈጸሙት ወንጀል በምድር ዋጋ አግኝተው ለሌሎች መቀጣጫ እንዲሆኑ፣ ፈጣሪን በጸሎት በመጠየቅ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa