Doch HD

Doch HD

Share

Doch HD ገና በጅምር ላይ ያለ የመረጃና የመዝናኛ ሚዲያ ነው። በዚህም መረጃ ሰጪ ቪዲዮ እና ምስል እንዲሁም ፅሁፍ በየቀኑ በየሰዓቱ ከእኛ ይመልከቱ። ዶች

12/05/2026

አላህ ድብድብ አይወድም፤ እናቴም ተው ብላኛለች እናም አልደባደብም ሲል ሴዶ ተናገረ 🔥

በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ይካሄዳል ተብሎ የነበረው ድብልቅ ማርሻል አርት ተሰርዟል። ይህም የሆነው ከ5 ሚሊዮን ጥያቄ እስከ 10 ሚሊዮን ብር እንዲሁም የትኬት ሽያጭና የ5 ሚሊዮን ቀብድ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ሀሳቡን በቀየረው ሴዶ ማርሻል ነው።

ሴዶ ትናንት ምሽት በቲክቶክ ላይቭ ባስተላለፈው መልእክት 'አላህ ድብድብ አይወድም' ሲል ፍልሚያውን ላለመፈለጉ ሃይማኖታዊ ምክንያት ሰጥቷል።

በተጨማሪም 'እናቴ ሰምታለች ተውም ብላኛለች' ያለው ሴዶ ለእናቱ ክብር መስጠት በማሰብም በዚሁ ድብድብ እንደማይሳተፍ በይፋ ተናግሯል።

ሴዶ ይህንን ያለው የሚደግፋቸውን የእስልምና እምነት ተከታይ ብዙ የፍልሚያው ስፖርት ሰዎች እያሞካሸ በተናገረበትና 'ወላሂ አደባደባለሁ' ባለበት በዚያው አንደበት መሆኑ 'ፈሪ' እንዲባል አድርጓል።

ዶች ኤችዲ

12/05/2026

የንቃተ ህሊና በራስ መተማመን እንዲኖረኝ ነው የምፈልገው🔥

11/05/2026

ጆኒ ለማንያዘዋል የ1 ሚሊዮን ብር ክርክር ጥሪ አቀረበ 🔥

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ድብልቅ ማርሻል አርት አሸናፊው ዮሐንስ ስለሺ (ጆኒ) ከአንድ ፖድካስት ጋር ባደረገው ቆይታ በተከታታይ ሲነቅፈው ለነበረው ማንያዘዋል እሸቱ ጥሪ አቅርቧል።

ማንያዘዋል የቢዝነስ ሰው እንዲሁም አነቃቂ እና የስብዕና ማጎልበቻ አሰልጣኝም በመሆን የሚታወቅ ሲሆን በጆኒ አጠራር " የዓመቱ አሽቋላጭ" ተብሎ መጠራቱ ክብረነክ ተብሎ ሲነሳ ቆይቷል።

ጆኒ በዚሁ ሃሳቡ በመፅናት በፖድካስት ቀርቦ በተናገረው ንግግር 'ማንያዘዋል በመረጠው ርዕስ ቦታና ጊዜ ተሰይሞ ተከራክረን ካሸነፈ 1 ሚሊዮን ብር እሰጠዋለሁ" ሲል ስለሚናገራቸው ነገሮች ጥልቅ እውቀት እንደሌለው ለማሳየት ጥረት አድርጓል።

በማንያዘዋል በኩል የተሰጠ ምላሽ ባይኖርም የኬጅ ፍልማያ ያሸነፈው ጆኒ የሃሳብና እውቀት ክርክሩ ይቀናው ይሆን የሚለው በጊዜ ሂደት የሚታይ ሆኗል።

ዶች ኤችዲ

11/05/2026

የሴዶ ማርሻል የቴክቶክ አካውንት ተዘጋ

በኢትዮጵያ ሊደረግ ለታቀደው 2ተኛ ድብልቅ ማርሻል አርት በተደጋጋሚ ጥሪ በማድረግ ተመልካቹን ያሰለቸው ሴዶ ማርሻል አካውንቱን አጥቷል።

ሴዶ ከደቂቃዎች በፊት ባስተላለፈው መልእክት ከ100 በላይ ቪዲዮ ሪፖርት እንደተደረገበት ጠቅሶ በአሁኑ ሰዓት አካውንቱን ማጣቱን ተናግሯል።

አካውንቱ ይመለስ አይመለስ የሚታወቅ ነገር ባይኖርም አዘጋጆች መደራደር እየተቻለ ይህንን አደረጉብኝ ሲል በቀጥታ ከተደራዳሪው ላይ ወቀሳ ቢሰነዝርም እርምጃው ከተሰላቸ ተመልካች እንጂ ከእነሱ ላይሆን ይችላል ተብሏል።

ሴዶ ወደ ፍልሚያ ላለመመለሱ ትናንት በአሜሪካ የተደረገው ውድድር ምክንያት ሆኗል የሚሉም ሰዎች አልጠፉም። በዚህ ውድድር ሴዶ የሚደግፈው ተፋላሚ እስከ መድማት የደረሰ የአካል ጉዳት አስተናግዶ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ መሸነፉ ተጨማሪ የስነልቦና ጫና አድርሶበታል ተብሏል።

ዶች ኤችዲ

Want your business to be the top-listed Advertising & Marketing Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Website

http://t.me/doch_TG, http://youtube.com/@doch_hd, http://youtube.com/@doch_yt

Address


Addis Ababa
1000