Biblically with Robi

Biblically with Robi

Share

የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል 4/ How to study the bible part 4 13/08/2023

https://youtu.be/i40AtVvoMPc

የመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት ክፍል 4/ How to study the bible part 4 መፅሐፍ ቅዱስን ስናጠና ይሄኛውን(በዚህ ቪድዮ ላይ የተዳሰሰውን) መንገድ ከረሳን የምናጠናበትን አላማ ስተናል ማለት ነው።ወደ ህይወት መተርጎም(Application) የመጨረሻው የመፅሐፍ ቅዱስ ጥና.....

06/08/2023

ፈቃደኛ የሆንን ሁሉ ይህንን ምስል የማህበራዊ ሚዲያዎቻችን አካውንቶች ላይ profile picture በማድረግ ለግብረሰዶማውያን ወንጌልን እናድርስ! መልእክቶችን እና ምስሎችን ስንለጥፍ የሚከተለውን ሀሽታግ ተጠቅመን በመልቀቅ መልእክቱ ብዙዎች ጋር እንዲደርስ እናድርግ።

05/08/2023

ግብረሰዶማዊያን ዛሬም የመዳን ተስፋ አላቸው!

እግዚአብሔር አለምን ሲወድ መልካም ስነምግባር ያላቸውን ብቻ መርጦ አልወደደም። እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ አለምን ሁሉ እንዲሁ(መስፈርቱን ሳናሟላ) ወዶናል። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
— ዮሐንስ 3፥16

ምንም ያህል ሀጢኘተኛ እንደሆናችሁ ቢሰማችሁ እግዚአብሔር ግን ከሀጢአታችሁ ሊያነፃችሁ ፈቃደኛ ነው። አንዳንዶቻችሁ ሳታውቁት በግብረሰዶማውያን የመደፈር ጥቃት ደርሶባችሁ ወደዚህ አፀያፊ ነገር እንድትገቡ ሆናችኋል። አንዳንዶቻችሁ ደግሞ ምክንያቱ ምን እንደሆነ በማታውቁት ሁኔታ ወደ ተመሳሳይ ፆታ የመሳብ ዝንባሌን በራሳችሁ ላይ አይታችሁም ሊሆን ይችላል ወደዚህ ህይወት የገባችሁት። እግዚአብሔር ግን ከዚህ ሁሉ እስራት ነፃ ሊያወጣችሁ ፈቃደኛ ነው።

እኔ በግሌ ሰው በራሱ ይህንን አፀያፊ ተግባር መፈፀም ይችላል ብዬ አላምንም። አጋንንት በሰዎች ውስጥ ሲገቡ ግን ሰው በጤናው የማይያደርገውን ነገር ሁሉ ማድረግ ይጀምራል። ከዚህ እስራት ነፃ ለመውጣት ብቸኛው መንገድ በኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝነት ማመንና ወደ ቤተክርስቲያን መምጣት ነው። ያን ጊዜ እግዚአብሔር ይረዳችኋል።

ኢየሱስ ወደ አለም የመጣው በሀጢአተኞች ፋንታ የሀጢአት መስዋዕት ለመሆን ነው። በከፈለው መስዋዕትነት(የመስቀል ሞት) በእሱ የሚያምኑትን ሁሉ ከሀጢአታቸው አንፅቶ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲያገኙ ምህረትን ያስገኝላቸዋል። የኢየሱስ ደም ከሀጢአት ሁሉ ያነፃል።
"የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።
ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም።
በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።
ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም።" 1ኛ ዮሐንስ 1፥7-10

ኑ ወደ ኢየሱስ! እግዚአብሔር እናንተን ይቅር ለማለት ዛሬም ዝግጁ ሆኖ ይጠብቃችኋል። እግዚአብሔር ይርዳችሁ! እወዳችኋለሁ!

Want your business to be the top-listed Media Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Addis Ababa