Bilal Microfinance

Bilal Microfinance

Share

21/04/2026

ቢላል ማይክሮፋይናንስ የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማውን አካሄደ!
*****
ቢላል ማይክሮፋይናንስ አ.ማ የ2026 ፋይናንስ ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማውን የተቋሙ ሥራ አመራር ቦርድ፣ የዋናው መ/ቤት ሥራ መሪዎች እና የቅርንጫፍ ሥ/አስኪያጆች በተገኙበት አካሂዷል፡፡ በግምገማው የተቋሙ የ9 ወራት አጠቃላይ የኦፕሬሽንና ፋይናንስ አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ተቋሙ በሁሉም ዋና ዋና መለኪያዎች አመርቂ አፈፃፀም ያስመዘገበ መሆኑ እና ወደታለመለት መዳረሻ ለመድረስ በትክክለኛው መስመር ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡ ቢላል ማይክሮፋይናንስ ሥራ በጀመረ በ2 ዓመታት ውስጥ አጠቃላይ ሃብቱን (Total Assets) ወደ 81.7 ሚሊዮን ብር በማድረስ እንዲሁም የተጣራ ተቀማጭ ቁጠባ ሂሳብ (Net Deposit Balance) ብር 50.03 ሚሊዮን በማድረስ እጅግ አመርቂ አፈፃፀም አስመዝግቧል፡፡ አጠቃላይ በ9 ወራት ብር 38.9 ሚሊዮን ፋይናንስ ማድረጉ (ማበደሩ) የተጠቀሰ ሲሆን ተቋሙ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ብር 56.6 ሚሊዮን ለደንበኞች ማቅረቡ (ፋይናንስ ማድረጉ) ተገልፁዋል፡፡ ተቋሙ በጀት ዓመቱን በስኬት እንዲያጠናቅቅ በቀሪዎቹ ወራት ሁሉም የተቋሙ ባለድርሻ አካላት በከፍተኛ ተነሳሽነትና ርብርብ እንዲሰሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ከአደራ ጭምር መልዕክት በማስተላለፍ ግምገማው ተጠናቋል፡፡
*****
ቢላል ማይክሮፋይናንስ፡ ከሁሉም ለሁሉም!
Bilal Microfinance: From All to All!
*****
ለበለጠ መረጃ፡
አድራሻ፡ ዋናው መ/ቤት ቦሌ ደንበል ሲቲ ሴንተር ጀርባ የቀድሞው አድማስ ኮሌጅ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ወይም በ0979777444 ይደውሉ፡፡
*****


!

Photos from Bilal Microfinance's post 19/03/2026
Photos from Bilal Microfinance's post 30/01/2026

ቢላል ማይክሮፋይናንስ አ.ማ እና ራሚስ ባንክ አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ!

ሁለቱም ተቋማት አገልግሎታቸዉንን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እና የፋይናንስ አካታችነትን ለማጎልበት፣ ከቢላል ማይክሮፋይናንስ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርሟል። የፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ፊላሚንጎ በሚገኘው የራሚስ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የተከናወነ ሲሆን፣ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
ቢላል አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ
ከሁሉምለሁሉም!

Want your business to be the top-listed Finance Company in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Telephone

Address


Addis Ababa