Afar press

Afar press

Share

𝖢𝖺𝗅𝗐𝖺𝗒 𝗄𝖾𝖾 𝖼𝖾𝗒𝖺𝗁 𝖺𝖽𝖽𝖺𝗍 𝗍𝖺𝗇 𝗊afar u𝗆𝗆𝖺𝗍𝗍𝖺𝗁 𝗑𝗂𝗊𝖺𝖺𝗆𝖺𝗅 𝗑𝗈𝗇𝗀𝗈𝗅𝗈 𝗒𝖺𝗄𝗄𝖾𝖾𝗇𝗂𝗆𝗂𝗁 𝗍akke gicloh gabah agle taallenim kee qokoltaanam ummaan qafar baxal dirki.kinni

28/10/2025

"የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማወቅ አይን፣ አፍንጫ እና ጆሯችሁን ተጠቀሙ" ጠቅላይ ሚኒስትሩ

28/10/2025

ቀይ ባህርን በተመለከተ

የቀይ ባህር ጉዳይ ህጋዊ፣ ታሪካዊ፣ መልከዓ ምድራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ነው ብለን እናምናለን። ይህንን በተረጋጋ መንገድ ማየት ያስፈልጋል። ኢትዮጵያን የቀይ ባህር የማጣት ውሳኔ ማን ወሰነ ብለን ስንፈልግ ተቋማት አልገቡበትም። ይህን የሚያህል የህልውና ጉዳይ ማን እንደወሰነ መጠየቅ ተገቢ ነው። ኢትዮጵያ ተዘግቶባት መኖር አትችልም። ለጎረቤቶቻችን መናገር የምንፈልገው ኢትዮጵያ ስታደግ ለቀጣናውም ልማት ምንጭ ትሆናለች። የምንፈልገው በትብብር ማደግ ነው።

#የጠሚሩምላሾች

Photos from Afar press's post 23/10/2025

"ከቅዳሜ እለት ጀምሮ ከኤርትራ ጋር ውጊያ ገጥመናል

የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አዲስ ኃይል አሰልጥኖ ማስመረቁን ይፋ አድርጓል፡፡

በኢትዮጵያ አፋር ክልል የሚንቀሳቀሰው የሻዕቢያ ተቀናቃኝ የቀይ ባህር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አዲስ ኃይል አሰልጥኖ ማስመረቁን ይፋ አድርጓል፡፡ ሻብያን ለመውጋት የተደራጀው ኃይል መመረቁ የተሰማው ጌታቸው ረዳ እና አምባሳደር ሬድዋን በቡሬ ግንባር በተገኙበት ወቅት ነው፡፡ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ጀነራሎች በቡሬ ግንባር ቅኝነት ባደረጉበት አጋጣሚ፣ የቀይ ባህር አፍር ድርጅት ወታደራዊ አዛዥ ስለ አዲሱ ጦራቸው ሰምሪት መግለጫ አውጥተዋል፡፡ ታጣቂ ኃይሉ ለተከታታይ ሦስት ወራት ያሰለጠናቸውን ኃይል ለስምሪት ዝግጁ ሆኗል ብሏል፡፡ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ የኢሳያስ አፈወርቂን አስተዳደር ለመውጋት የሰለጠነው ኃይል እሰከ መሀል ሀገር ዘለቆ በመግባት ጥቃት መፈጸም የሚችል እንደሆነ ተናግሯል፡፡

የድርጅቱ ወታደራዊ አቅም የፊት ለፊት ውጊያ፣ የሽምቅ ውጊያና ልዩ ኦፕሬሽን መፈጸም እንዲችል ተደርጎ ሰልጥኗል የተባለ ሲሆን፤ በኢሳያስ አፈወርቂ አገዛዝ ተቀምቷል ያለውን የቀይ ባህር አፋር መሬትን ነጻ አወጣለሁ ብሏል፡፡ ወታደራዊ ብቁነቱ ተረጋግጦ ተመርቋል የተባለው የድርጅቱ ኃይል ሻብያን በኃይል ለመገርሰስ የሚያስችል ቁመና አለው ተብሏል፡፡

ድርጅቱ በጀመረው የትጥቅ ትግል የቀይ ባህር አፋር ህዝብ መብት ለማስጠበቅ እና ሙሉ በሙሉ የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል፡፡ የድርጅቱ የራስን በራስ የመወሰን ትግል አስፈላጊ ከሆነ እሰከመገንጠል ይዘልቃል የተባለ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ አፋር ወንድም ሕዝብ ጋርም እተባበራለሁ ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ አፋር ሕዝብና መንግሥት የቀይ ባህ አፋርን ሕዝብ ከመፈናቀልና ብሔር ተኮር ጥቃት ለመከላከል ድጋፍ አድርጓል ያለም ሲሆን፤ የአፋር ክልል መንግሥት እና ሕዝብ አድርጎልኛል ላለው ድጋፍ በይፋ አመስግኗል፡፡ ወደፊትም በትብብር መሥራቱን እንደሚቀጥል ጠቁሟል፡፡

የድርጅቱ ሊቀመንበር ኢብራሂም ሀሩን ቀጣዩ ምዕራፍ የድርጅቱን የባህር ኃይል ማቋቋም ነው ብለዋል፡፡ ድርጅቱ አሁን ባለው የፖለቲካ እና ወታደራዊ መስፈርቶች መሰረት የሰለጠነ እና የታጠቀ የባህር ኃይል ለማቋቋም እየሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል። ሊቀመንበሩ ለመገልበጥ የሚታገሉትን ሻብያን ከቀይ ባህር አፋር አልፎ ለጎረቤት ሀገራትም ጠንቅ ነው ሲሊ ከሰውታል፡፡ ኢብራሂም የኢሳየስ አስተዳደር ለኤርትራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለጎረቤት መንግስታት፣ ለቀይ ባህር እና በአፍሪካ ቀንድ ስጋት ሆኗል ሲሉ ነው የወነጀሉት፡፡

የጎረቤት ሀገራት እና የአለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህንን ስጋት ተገንዝበው የኢሳያስ አፈርቂን አስዳደር ለመገርስ የሚታጉ የኤርትራ ኃይሎች እንዲደግፉ ጠይቀዋል። ድርጅቱ የኤርትራን ጭቆና አገዛዝ በጋራ ለመታገል የሚያስችል ግንባር ለመፍጠር ለኤርትራ የፖለቲካ ኃይሎች ጥሪ አቅርቧል፡፡

Want your public figure to be the top-listed Public Figure in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Address


Addis Ababa